Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ለተማሪዎች በነፃ የሚያከፋፍላቸዉ ደብተሮች በህገወጥ መንገድ በሱቆች | Free Education Ethiopia ✔️︎

የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር ለተማሪዎች በነፃ የሚያከፋፍላቸዉ ደብተሮች በህገወጥ መንገድ በሱቆች በመሸጥ ላይ ናቸዉ

የአዲስአበባ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ ወላጆች ለህግ አካላት ጥቆማ ያድርሱ ብሏል

የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የሚያሳትማቸዉ ደብተሮች በሱቆች በመሸጥ ላይ መሆናቸዉን ብስራት ራዲዮ ተመልክቷል። ደብተሮቹ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በነፃ የሚከፋፈሉ ቢሆንም ፤ በአሁኑ ሰዓት እስከ 50 ብር ድረስ በሱቆች በመሸጥ ላይ ናቸዉ።

ብስራት ራዲዮ ጉዳዩን በሚመለከት የአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር የትምህርት ቢሮን ያነጋገረ ሲሆን ድርጊቱ ህገወጥ ከመሆኑ በተጨማሪ ይህን በሚያደርጉ የንግድ መደብሮች ላይ ወላጆች ጥቆማ ይስጡኝ ብሏል።

የከተማ መስተዳደሩ ምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አንቺነሽ ተስፋዬ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ፤ መስተዳድሩ በከፍተኛ በጀት የሚያሳትማቸዉ እኚህ ደብተሮች ለተማሪዎች በነፃ የሚከፋፈሉ እንጂ ለንግድ የሚዉሉ ባለመሆናቸዉ በድርጊቱ የሚሳተፉ አካላትን አስጠንቅቀዋል። እንደ ኃላፊዋ ገለፃ እያንዳንዱ ደብተር ከበስተጀርባው የራሱ የሆነ መለያ ቁጥር ያለዉ በመሆኑ በየትኛው አምራች የተመረቱት ደብተሮች በገበያዉ ላይ አሉ የሚለዉን እናጣራለን ብለዋል።

አሁን በገበያዉ ላይ ያሉ ደብተሮች፤ ከዚህ ቀደም ለከተማ መስተዳድሩ ደብተሮቹን ለማቅረብ ተስማምተው ከጥራት በታች ናቸዉ ተብለዉ ከጨረታዉ የታገዱ እና ህጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸዉ ሊሆኑ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

ኃላፊዋ አክለዉም ትምህርት ቢሮዉ ፤ ለተማሪዎች ተብለዉ የሚመጡ ደብተሮችን የሚሸጥም ሆነ የሚያዘዋዉር እንዲሁም የሚገዛ አካል በህግ የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል።

በተያዘዉ ዓመት ደብተር እስካሁን ያልደረሳቸዉ ተማሪዎች እንዳሉ ለኃላፊዋ ጥያቄ ያነሳን ሲሆን ፤ አቅርቦቱ ከዉጭ ሀገር በመሆኑ እና የዘንድሮው የትምህርት ዘመን ጅማሮ ከተያዘው የግዜ ሰሌዳ የፈጠነ በመሆኑ መጓተቱ ከዚህ የመነጨ ነው ብለዋል። በቀጣይ አንድ ሳምንት ዉስጥ ችግሩ እንፈሚቀረፍ እና ለሁሉም ተማሪዎች ደብተር እንደሚከፋፈል ወ/ሮ አንቺነሽ ተስፋዬ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!