Get Mystery Box with random crypto!

Free Education Ethiopia ✔️︎

የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎
የሰርጥ አድራሻ: @free_education_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 39.06K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Student’s Center
Our groups different grades
@EthioGrade6
@EthioGrade7
@EthioGrade8
@EthioGrade9
@EthioGrade10
@EthioGrade11
@EthioGrade12
Online school bot
@Education_Ethiopia_Bot
📮For paid promotion @Free_Education_Ethiopia_Bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-20 18:41:41


እንኳን ለ1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የዒድ አልፈጥር በዓል #ነገ መሆኑ ታውቋል።

የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረቢያ በቱሚናር እና ሱዳይር ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ ጁምዓ / አርብ ይውላል።



@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
19.8K viewsπ, 15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:28:49


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!

መልካም የትንሣኤ በዓል !



@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
18.5K viewsπ, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 22:37:35
#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለአዲስ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት አቆመ።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማትና ተቋማቱን የሚከፍቱ ባለሀብቶች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎችን እያዘጋጀ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በዚህም ከኅዳር 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙን በተቋሙ የፈቃድ እና ጥራት ኦዲት ም/ዋ/ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

አዲስ ለሚከፈቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት በማቆም ያሉትን የማጥራት ሥራዎች ላይ ትኩረት መደረጉን ኃላፊው ይገልጸዋል።

በተያዘው ዓመት አዲስ ፈቃድ የመስጠት ሥራ ይጀምራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ኃላፊው ጠቁመዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
17.9K viewsπ, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 21:50:06
የነጻ ትምህርት ዕድል !

በሰዎች ለሰዎች ድርጅት ወይንም Menschen für Menschen Foundation ስር የሚተዳደረው የሐረር ቴክኖሎጂ ኮሌጅ በ2015 የትምህርት ዘመን ብቁ የሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዲግሪ መርሐግብር ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

የዚህ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትፈልጉ ተማሪዎች ከመጋቢተ 18 - 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት የስራ ቀናት በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦ ትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ዓ.ም. ያወጣውን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ ወይንም በአገር አቀፍ ፈተና 50% እና ከዚያ በላይ ያመጡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፡፡ 

የምዝገባ ቦታዎች በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ በሚገኘው የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ዋና መ/ቤት፤ ሐረር  በኮሌጁ ቅጥር ግቢ፤ የድርጅቱ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች በሚገኙባችው በተጨማሪም በድረ-ገጻችን http://www.mfmattc.edu.et ላይም መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0256663738/1139 ወይም 0114714579 ደውሎ ማንጋገር ይቻላል፡፡ 

(ሰዎች ለሰዎች ድርጅት Menschen für Menschen Foundation)

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
21.3K viewsπ, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 15:14:59
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ነገ መጋቢት 20/2015 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል፡፡

በበይነ መረብ አማካይነት በሚደረገው ምዝገባ፤ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች 850 ሺህ የሚጠጉ እንዲሁም በግል 200 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ ይጠበቃል፡፡

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20/2015 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለጹ ይታወቃል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
18.7K viewsπ, 12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:12:24 #NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

Via MoE
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
17.2K viewsπ, 16:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 12:14:44 #ExitExam

ምን ያህል ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ?

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ አመለወቅር ህዝቅኤል በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ፣ ዝግጅት እና ፈተናውን ማለፍ የማይችሉ ተማሪዎችን በተመለከተ) ከሰሞኑን ለቪኦኤ ሬድዮ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

ወ/ሮ አመለወርቅ እዝቅኤል ፦

" አሁን የለየናቸው አሉ ፤ የደረሰን መረጃ አለ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎች ናቸው እጃችን ላይ ያሉት።

ነገር ግን ጥር ላይ በተለያየ ምክንያት ያላጠናቀቁ ልጆች በአንደኛ ሴሚስተር የሚያጠናቅቁና ወደ ምዘናው ሊመጡ የሚችሉ ልጆች ሊኖሩ ይችላሉ።

ከዛ ባሻገር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዚህ System ውስጥ የሚያልፉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የደረሱን መረጃዎች አሉ።

አሁን በቁጥር ነው የተቀበልነው ልክ እንደ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በስም እያንዳንዱ ስም በሚመጣ ሰዓት የተወሰነ የቁጥር ለውጥ ሊኖረው ይችላል አሁን ባለንበት ሁኔታ ወደ 240 ሺህ ተማሪዎችን እንፈትናለን ብለን እናስባለን።

ከመጀመሪያው ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እየተሰራ ነው የሚገኘው። ከዛ ባሻገር አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ሞዴል ፈተናዎች እንዲፈተኑ በማድረግ፣ Sociologically እንዲዘጋጁ እንዲያጠኑ እየተሰራ ነው ተማሪዎችን በዛ ልክ አውቀው እየሰሩ ነው።

ፈተናው እንዴት manage ይደረጋል በሚለው ላይ የተለያዩ ማስፈፀሚያዎች ወደ ታች ወርደዋል በዚያ መሰረት ቅድመ ዝግጅቶች እየተደርጉ ነው የሚገኙት። "

የመጀመሪያውን ፈተና የማያልፉ ተማሪዎች ዕጣ ፋንታ ምንድነው ?

" ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎች መልሰው መላልሰው የሚወስዱበት ዕድል አለ።

ይሄ የሚሆነው እንዴት ነው የመጀመሪያው ዙር መንግሥት በራሱ መንገድ የሚያስኬደው ነው ከዛ በኃላ ልክ 12ኛ ክፍል Private እንደሚፈተነው ሁሉ መውጫ ፈተና ላይም ዝግጁ ነን በሚሉ ሰዓት በተዘጋጁ እና ይሄን ፈተና አልፋለሁ ብለው እራሳቸውን አብቅተው በሚመጡበት ሰዓት መፈተን ይችላሉ። ተፈትነው ሲያልፉ ዲግሪያቸውን የሚወስዱበት አሰራር አለ።

እስከዛ ድረስ ደግሞ ለምሳሌ የመውጫ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ የሚያስገኘውን ፈተና ማለፍ ባይችሉ እንኳን ዝቅ ባሉ ደረጃዎች በLevel ደረጃ ባሉት (ከዲግሪ በታች ባሉ መመዘኛዎች) ተፈትነው ልክ COC እንደሚፈተነቱ ተፈትነው ማለፍ የቻሉበት ደረጃ ላይ Certify ይደረጋሉ በዛ ስራ ማግኘት የሚችሉበት አማራጭ ይኖራቸዋል። "

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
14.3K viewsπ, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 13:11:26 የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና

" ከ75 ሺ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን የሚኒስትሪ ፈተና ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው " - የአ/አ ትምህርት ቢሮ

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሰጠውን የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ፈተና ተማሪዎችን ለማስፈተን የዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋቃ።

የቢሮው የፈተና ዝግጅት እና አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የሠጡት ቃል ፦

- በአዲስ አበባ ከተማ በግል እና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ ከ75 ሺህ በላይ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለማስፈተን ዝግጅት እየተደረገ ነው።

- ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ድረስ ተማሪዎቹን ለፈተና የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

- ተማሪዎች የሚኒስትሪ ፈተና ከመፈተናቸው አስቀድሞ የተለያዩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሞዴል ፈተናዎችን በማዘጋጀት በወሩ እንዲወስዱ ተደርጓል። ለፈተናው የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትንም አንብበው እንዲዘጋጁ እና እንዲፈተኑ እየተደረገ ነው።

- በአማርኛ ቋንቋ የሚፈተኑ አራት እንዲሁም በአፋን ኦሮሞ የሚፈተኑ አምስት የትምህርት ዓይነት ፈተናዎች የሚወስዱ ይሆናል። በዚህ መሠረትም ፦
የሒሳብ፣
የአካባቢ ሳይንስ፣
አማርኛ፣
አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዝኛ የትምህርት ዓይነቶች ይሰጣሉ።

- ምዝገባው የሚካሄደው በኦንላይን ሲሆን የተመዘገቡ ተማሪዎች የተመዘገቡበትን የስም እና ዕድሜ ስህተት እንዳይኖር ማረጋገጥ እና ማስተካከል ይችላሉ።

- በየክላስተሩ ላሉ ትምህርት ቤቶች ወጥ በሆነ መልኩ ስልጠና በመስጠት ትምህርት ቤቶች ራሳቸው ፈተናዎችን እንዲያወጡ እና እንዲፈተኑ ይደርጋል።

- በአዲሱ ሥርዓት ትምህርት በየምዕራፉ ማጠናቀቂያ ላይ ለተማሪዎች ፈተና ይሰጣል። ለዚህም አንደኛ ምዕራፍ የሚባለው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍል ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሲሆን ሁለተኛ ምዕራፍ የሚባለው ከሰባት እስከ ስምንተኛ ክፍል ነው።

- የመጀመሪያ ምዕራፍ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያጠናቅቁት ስድስተኛ ክፍል ላይ ስለሆነ የሚኒስትሪ ፈተናው ተማሪዎች ከታች ጀምረው ራሳቸውን እያነጹ እንዲመጡ የሚያደርግ ነው። የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም አለው።

- የመማሪያ መጽሐፍት በሚፈለገው ልክ ሀገር ውስጥ አለመገኘት እና በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ከውጭ የሚመጡ መጽሐፍት የመዘግየት ሁኔታ አለ።

- የሚኒስትሪ ፈተና የሚሰጥበት ቀናት የሚወሰነው በአገር አቀፍ ደረጃ ቢሆንም እንደ ቢሮ #ከሰኔ አጋማሽ በኋላ ለመስጠት ዝግጁ ነን።

#ኢፕድ
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
15.3K viewsπ, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-29 16:46:19
ለ12 ክፍል ተፈታኞች!!

በኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ላይ

1) ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች ምንድናቸው?

2) የተፈታኞች መብቶች ምንድን ናቸው?

3) የተፈታኞች ግዴታ ምንድንነው?

 
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe
2.7K viewsRBST, edited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-28 21:34:21
#AD
ለ12ተኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና መለማመጃ መተግበሪያ ለተፈታኞች

ስቴም ፓወር ከቪዛ እንዲሁም ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ተሳታፊ በነበሩ ወጣቶች የተሰራ ሥራ እናስተዋውቃችሁ።

#ThinkHubInnovations ይሰኛሉ ለ12ተኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የሚያገለግል "Exam Time" የተባለ መለማመጃ የሞባይል መተግበራያ በአገልግሎት ላይ አውለዋል።

ይህም መተግበሪያ ተፈታኞች ከጥናት ሳይዘናጉ ባላቸዉ ቀሪ ጊዜ ራሳቸዉን ለመመዘን የሚያስችል መተግበሪያ ነው። እናም ይህን መተግበሪያ በቀላሉ ከplaystore ላይ ተማሪዎች ማግኘት ይችላሉ።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.exam_time.exam
1.9K viewsRBST, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ