Get Mystery Box with random crypto!

#NationalExam ' ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም ' - የትምህ | Free Education Ethiopia ✔️︎

#NationalExam

" ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን አይፈተንም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015 ዓ.ም እንደሚከናወን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ አማካይነት እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።

የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንዳይፈጠር ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ እና የማታው ክፍለ ጊዜ ተማሪዎች ምዝገባ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የተጠቀሰ ሲሆን ተማሪዎች የምዝገባ ሂደቱን ለማካሄድ በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

የድጋሚ ተፈታኞች እና የርቀት ተማሪዎች ምዝገባ ደግሞ በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች ይካሄዳል።

የምዝገባ ሂደቱ በተጠቀሱት ቀናት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከናወን ሲሆን ምዝገባውን ያላደረገ ተማሪ የመልቀቂያ ፈተናውን እንደማይፈተን አገልግሎቱ አሳውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ለምዝገባ ምን ያስፈልጋል / ተማሪዎች ምን ማሟላት አለባቸው ?

- መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ9 - 12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

- የማታ እና የርቀት ተማሪዎች የ11ኛ ክፍል ሶስት ሴሚስተር እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል የሁለት ሴሚስተር የትምህርት ማስረጃ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- ድጋሜ ተፈታኞች ከዚህ ቀደም የተፈተኑበትን የትምህርት ማስረጃ በመያዝ መመዝገብ አለባቸው።

- ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናው መቼ እና የት ይሰጣል ?

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

Via MoE
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!