Get Mystery Box with random crypto!

#ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለአዲስ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት አቆ | Free Education Ethiopia ✔️︎

#ETA

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለአዲስ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት አቆመ።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማትና ተቋማቱን የሚከፍቱ ባለሀብቶች ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎችን እያዘጋጀ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በዚህም ከኅዳር 30/2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈቃድ መስጠት ማቆሙን በተቋሙ የፈቃድ እና ጥራት ኦዲት ም/ዋ/ዳይሬክተር ውብሸት ታደለ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

አዲስ ለሚከፈቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት በማቆም ያሉትን የማጥራት ሥራዎች ላይ ትኩረት መደረጉን ኃላፊው ይገልጸዋል።

በተያዘው ዓመት አዲስ ፈቃድ የመስጠት ሥራ ይጀምራል የሚል እምነት እንደሌላቸው ኃላፊው ጠቁመዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!