Get Mystery Box with random crypto!

  የሚጨመሩና የሚቀነሱ የትምህርት አይነቶች ይኖራሉ በ አዲሱ የሥርዓተ-ትምህርት በአዲሱ  የሥርዓ | Free Education Ethiopia ✔️︎

  የሚጨመሩና የሚቀነሱ የትምህርት አይነቶች ይኖራሉ በ አዲሱ የሥርዓተ-ትምህርት

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸው ተገለጸ።የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል  ኃላፊ አድማሱ ደቻሳ እንደገለጹት አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2015 የትምህርት ዘመን በከፊል በተወሰኑ በቅድመ አንደኛ ደረጃ እና በአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤቶች ላይ ይተገበራል።

በአዲሱ  የሥርዓተ-ትምህርት ትግበራ  ከአንደኛ ደረጃ እስከ መሰናዶ ትምህርት ቤት ያሉ ትምህርቶች ላይ የሚቀነሱ እና እንደ አዲስ የሚጨመሩ የትምህርት አይነቶች መኖራቸውን ተናግረዋል።በ7ኛ እና 8ኛ ክፍሎች ላይ ከዚህ በፊት ሦስቱ ሳይንሶች ተብለው ይሰጡ የነበሩት (ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስና ባዮሎጂ) አሁን  አጠቃላይ ሳይንስ ተብለው በአንድ ይሰጣሉ ብለዋል።

  በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል የኢኮኖሚክስ ትምህርት አሁን ላይ “ፐርፎርም ኤንድ ቪዥዋል አርት” በሚል መተካቱንም ጠቁመዋል።በተመሳሳይ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍል በድጋሚ ከሚሰጡ የትምህርት አይነቶች በተጨማሪ ሥራና ቴክኒክ ላይ የሚያተኩሩ የማኑፋክቸሪንግና ኮንስትራክሽን  የትምህርት አይነቶች በየደረጃው ተለይተው መጨመራቸውን ገልጸዋል።
  
   በ2015 የትምህርት ዘመን የተማሪ ዩኒፎርሞችና የመማሪያ ቁሳቁሶች በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅት የተደረገ ሲሆን የትምህርት ቤቶችን አካባቢ ከአዋኪ ነገሮች ነፃ ማድረግም ትኩረት ተሰጥቶታል ተብሏል።ለአዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት ስኬታማነት ከወላጆችና አጠቃላይ ከትምህርት ማኅበረሰቡ ጋር እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ስኬታማነት በትምህርት ቢሮ በኩል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ነው የገለጹት።በየደረጃው ካሉ የወላጅ ኮሚቴዎች፣ የትምህርት አመራሮችና የግል ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር ሰፊ ውይይት ስለመደረጉም አብራርተዋል። አዲሱ ሥርዓተ-ትምህርት በ2016 ዓ.ም ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ መሆኑም ታውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!