Get Mystery Box with random crypto!

Free Education Ethiopia ✔️︎

የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ free_education_ethiopia — Free Education Ethiopia ✔️︎
የሰርጥ አድራሻ: @free_education_ethiopia
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 38.83K
የሰርጥ መግለጫ

Ethiopian Student’s Center
Our groups different grades
@EthioGrade6
@EthioGrade7
@EthioGrade8
@EthioGrade9
@EthioGrade10
@EthioGrade11
@EthioGrade12
Online school bot
@Education_Ethiopia_Bot
📮For paid promotion @Free_Education_Ethiopia_Bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-06-16 22:48:55
#የትምህርት_ምዘናና_ፈተናዎች_አገልግሎት_ሹመት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አዲስ ዋና ዳይሬክተር ተሹሞለታል።

እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ከሰኔ 02/2014 ዓ.ም ጀምሮ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን ሰኔ 08/2014 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተፈርሞ የወጣ የሹመት ደብዳቤ ያሳያል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው መመደባቸውን ተከትሎ ተቋሙ በምክትል ዋና ዳይሬክተር ሲመራ ቆይቷል።

የቀድሞ መጠሪያው ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የነበረው አገልግሎቱ፤ ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መሠረቅና ውጤት ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ሲነሱበት መቆየቱ አይዘነጋም።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
1.7K viewsπ, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 17:59:46
#MinistryOfEducation

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አዲስ ከተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቦርድ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በትምህርት ዘርፍ የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እና የቦርድ አባላቱ ኃላፊነታቸውን በባለቤትነትና በእውቀት እንዲመሩ ለማስቻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ የተመደቡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቦርድ አመራሮች በትምህርት ዘርፍ የተጀመረውን ሪፎርም ለማሳካት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በአዲሱ ሪፎርም የስርዓተ ትምህርት ለውጥ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ነጻነት፣ የዩኒቨርስቲ የመስክ ልየታ እንዲሁም ለተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መስጠት የተካተቱ መሆኑ ተገልጿል።

በቀጣይ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራት፣ የሀብት ብክነት መከላከል እና የዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ነጻነት ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ ገቢራዊ መሆን የጀመረ አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ምደባ ለመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ማድረጉ ይታወቃል።

#edu_news
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.6K viewsπ, 14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 12:35:03
#Update

ህፃን ማርኮን እስካሁን አልተገኘም።

በአዲስ አበባ ከተማ በጎርፍ የተወሰደው ማርኮን ይገረም እስካሁን አለመገኘቱ ታውቋል።

ዛሬ 7ኛ ቀን ነው።

አሁንም ፍለጋ መቀጠሉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የላዛርስት አከባቢ ልጆች በጎርፍ አደጋ በጠፋው ህፃን ማርኮን ሀዘናቸውን ገልፀው ከምሽቱ 12 ሰዓት (ዛሬ) በላዛርስት ት/ቤት በር ላይ የፀሎት እና የሻማ ማብራት ፕሮግራም ይካሄዳል ብለዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
3.3K viewsπ, 09:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 08:56:56
#DebarkUniversity

የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ሰኔ 08 እና 09/2014 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።

ዩኒቨርሲቲው በተገለጹት ቀናት ከጎንደር እስከ ደባርቅ የትራንስፖርት አገልግሎት ማዘጋጀቱን ገልጿል።

በተገለጹት ቀናት በጎንደር ፒያሳ መስቀል አደባባይ እና አዘዞ አይራ መገንጠያ በመገኘት አገልግሎቱን መጠቀም ይቻላል ተብሏል።
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
3.5K viewsRBST, edited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 15:36:11
#ወላጆች_ለልጆች_ጥንቃቄ_እንዲያደርጉ_አሳስቧቸው !

ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተሰምቷል።

የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመልክቷል።

ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው ትላንት 9 ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የገለፀው ኮሚኒኬሽኑ በጎርፉ የተወሰደው ተማሪ በትምህርት መውጫ ሠዓት ላይ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት እየሄዱ እንደነበርም አስረድቷል።

እስከዛሬ ጠዋት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሠራተኞቹ ከኅብረተስቡ ጋር በመሆን ተማሪውን የመፈለጉን ሥራ ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ወላጆች በክረምቱ ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት ሲልኩ ሆነ ሲቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉላቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ማሳሰቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ኤፍቢሲ

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.7K viewsπ, 12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 19:58:50
iCog-ACC ልጆችን በለጋ እድሜያቸዉ መሠረታዊ የኮምፒዉተር እና ኮዲንግ ስልጠና በመሰጠት ለወደፊት ለሚጠብቃቸዉ በዲጂታል የጎለበተ አለም ዝግጁ ያደርጋቸዋል፡፡

በአሜሪካ፥ ካናዳ እና በአዲስ አበባ ብቻ ሲሰጥ የነበረው ይህ የክረምት ፕሮግራም አሁን ደግሞ በባህር ዳር፣ ሃዋሳ፣ ጅማ እና ሐረር ይሰጣል ፡፡

ልጆቻችሁን በዚህ ፕሮግራም እንዲሳተፉ የምትፈልጉ ወላጆች በስልክ ቁጥራችን +251904262728 በመደወል ይህንን ቦት @iCogACCBot ወይም ይህንንማስፈንጠሪያ በመጠቀም ከዛሬ ጅምሮ ማስመዝገብ ትችላላችሁ https://icogacc.com/register/summer+camp+program+2022

#icog
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.0K viewsπ, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 15:23:58
የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ነጻ ሆኖ የመመራት መብት የሚሰጥበት የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄዷል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ውጪ በመሆን ነጻ ተቋም እንዲሆን የተወሰነውም መንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በራስ ገዝ አስተዳደር እንዲተዳደሩ የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ መሆኑን መግለፃቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#MoE

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
3.3K viewsπ, 12:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 20:55:11
ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና የሰጠው ት/ቤት !

በሀገር ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የኦንላይን (Online) ሙከራ ፈተና መስጠቱን የአረካ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታዉቋል።

ይህም ሀገራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች በፈተና ጊዜ የቴክኖሎጂ ችግር እንዳይገጥማቸው ያግዛል ነው የተባለው።

ፈተናው በሙክራ እየተሰጠ የሚገኘው ትምህርት ቤቱ #በራሱ_መምህር አማካኝነት በበለጸገው ሥርዓት አማካኝነት ነው።

የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ የዛሬው ተግባት እጅግ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

የዚህን ትምህርት ቤት ተሞክሮ ወደ ሌሎች በዞን ወደሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ለማስፋፋት እንደሚሰራ ገልጿል።

ይህ የኦንላይን (Online) ፈተና ዝግጅት ከማዳበር ባሻገር ለተማሪዎች የቴክኖሎጂ ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና እንድያጎለብቱ መልካም እድል መሆኑን ትምህርት ቤቱ አሳውቋል።

ትምህርት ቤቱ በዚህ ዘርፍ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ዉጤታማ ለመሆን እየጣራ መሆኑን አመልክቷል።

Via Tikvah
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.4K viewsπ, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 22:55:32


“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል ስያሜ የተቋቋመ 'ተቋም' እንደሌለ የትምህርትና ስልጣና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መቋቋም የሚችለው በአዋጅ ቁጥር 1152/2011 እንዲሁም በሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 መሰረት ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ፈቃድ ሲያገኝ ብቻ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ “የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በሚል መጠሪያ ግንቦት 29/2014 ዓ.ም እንደተቋቋመ በመግልጽ በማህበራዊ ድረ-ገጽ እየተዋወቀ የሚገኝው "ተቋም" እውቅና የሌለው መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

“የኢትዮጵያ አገር በቀል እውቀት ዩኒቨርሲቲ” በማለት ራሱን እያስተዋወቀ የሚገኘው "ተቋም"፤ ከባለሥልጣኑ ምንም አይነት ፈቃድ ያልተሰጠው እንደሆነ ተመላክቷል።

በቀጣይ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ህጋዊ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወስድ ባለስልጣኑ አሳውቋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
2.1K viewsπ, 19:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 13:28:03
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ያሉ ከፍተኛ ውጤት ላላቸው 35 ተማሪዎች አጭር መሰረታዊ የኤሌክትሮኒክስ እና የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል።

ዩኒቨርሲቲው በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስና እና የሂሳብ ማዕከሉ ለአምስት ሳምንታት በቅዳሜ እና እሁድ መረሃ-ግብር ነው ስልጠናውን የሰጠው።

ከጉራጌ ዞን ከተማ አስተዳደር እና አቅራቢያ ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ዙር ስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡

በስልጠናው ማጠናቀቂያ ተማሪዎቹ በነበራቸው ቆይታ የሠሯቸውን ፕሮጀክቶች አቅርበዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
3.8K viewsπ, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ