Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹 ኢትዮ Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiostudents — 🇪🇹 ኢትዮ Students
የሰርጥ አድራሻ: @ethiostudents
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 56.17K
የሰርጥ መግለጫ

Our Bot :
@EthioExamBot
Contact : @ethioexamsupport
Or
@Etssupport

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-13 10:58:22
18 ሰዓታት በፈጀ  የቀዶ ህክምና 20 ሳ.ሜ ከፍታ ያለው የጭንቅላት እጢ በተሳካ ሁኔታ ተወገደ

18 ሰዓታት በፈጀ የጭንቅላት እጢ በቀዶ ህክምና ማስተካከል መቻሉን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ጫኔ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በቀዶ ህክምናው ዋና ዋና ተግባራት በጭንቅላቱ ላይ የነበረውን 20 ሳንቲሜትር ከፍታ የለው እብጠት በቀዶ ህክምና እንዲወጣ ተደርጓል ።

አያይዘውም እብጠቱ የወጣበትን ቦታ በሌላ የሰውነት ክፍል የመተካት ተግባር ተከናውኗል።በሶስተኛ ደረጃ ከታካሚው ከተለያዮ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ከእጆቹ ላይ ደም ቅዳና ደም መልስ ተመሳሳይ ደም ስሮችን ወደጭንቅላቱ እንዲደርስ ተደርጓል  በማለት ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በአራተኛ ደረጃ ደግሞ በቀዶ ህክምና  ወቅት በሰውነት ክፍሉ የደም መፍሰስ ችግር እንዳይኖር አስቀድሞ በቂ ደም የመያዝና  የደም ስሮችን የመቋጠር ተግባር  መከናወኑ ተገልጿል።በመጨረሻም ታካሚው ከ18 ሰአታት በኋላ በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደቆየ ተደርጓል ያሉት አቶ አለምሰገድ በአሁኑ ሰአት  በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህም የተሳካ ቀዶ ህክምና የተሳተፉ የተለያዩ  ስፔሻሊስቶች ፣  ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች፣ አኒስቴትክስ፣ ነርሶች ፣ፖርተሮች እና ፅዳቶች  ሲያከናውኑ የነበሩ የቡድን አባላቶች ስራ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ  ተጠቅሷል።ዶ/ር አብዱራዛቅ  የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ስፔሻሊስት ባለሙያና የማክሮ ሰርጀሪ ሰብ ስፔሻሊስት በዚህ ህክምና ላይ ለተሳተፉ አጠቃላይ ሰራተኞች  ምስጋናቸውን  አቅርበዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 14:17:31 በሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በዛሬው እለት ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ያደረጉ ሁለት ግለሰቦች ሲገደሉ ፖሊሶች ቆሰሉ

ተጨማሪ ሌላ አንድ መንገደኛ ግለሰብም ተገድሏል


በዛሬዉ እለት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ከፖሊስ አባላት ጋር የተኩስ ልዉዉጥ ካደረጉ ሰዎች ዉስጥ ሁለቱ ሲገደሉ ሌላኛዉ በቁጥጥር ስር መዋሉን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የአዲስአበባ ፖሊስ ፤ ናሁሰናይ አንድአርጌ ታረቀኝ ፣ አቤኔዜር ጋሻው አባተ እና ሀብታሙ አንድአርጌ ተሰማ የተባሉት ሰዎች በአዲስአበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ ደርሼባቸዋለሁ ያለ ሲሆን በቁጥጥር ስር ለማዋል የፖሊስ አባላት እንቅስቃሴ እያደረጉ ባለበት ሁኔታ ሚሊኒዬም አዳራሽ አካባቢ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆን ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።

ግለሰቦቹ በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2C 14373 አ/አ አይነቷ ሱዙኪ ዲዛዬር መኪናን በመጠቀም  ከፖሊስ አባላት ጋር ተኩስ በመክፈታቸው ናሁሰናይ አንዳርጌ ታረቀኝ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ገልጿል። በተጨማሪም ሀብታሙ አንዳርጌ ተሰማ በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል ብሏል ፖሊስ፡፡

ሌላዉ አቤኔዘር ጋሻው አባት የተባለው ሳይቆስል በቁጥጥር ስር መዋሉን አዲስ አበባ ፖሊስ በመግለጫው መጥቀሱን ዳጉ ተመልክቷል፡፡ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ እንቅስቃሴ ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ መቁሰላቸዉንም ፖሊስ አረጋግጧል።

ሌላዉ አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ግለሰብ ታጣቂዎቹ  በመኪናቸው እንዲጭኗቸው  ቢያስገድዷቸውም ግለሰቡ አልተባበር በማለታቸው በታጣቂዎቹ ተገድለዋል ሲል ፖሊስ ወንጅሏል፡፡  አቶ እንደሻው ሲያሽከርክሯት የነበረቸው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ  80457 በጥይት ጉዳት እንደረሰባት አዲስ አበባ ፖሊስ  ጨምሮ ገልጿል ፡፡

#ዳጉ_ጆርናል

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.2K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 17:16:26
#ትዝብት_ከ_ቲክቶከር

ለ2 አራት ምግብ በልተው ሂሳብ ሲባሉ የለንም ሰሃን እንጠብ አሉ። አይቻልም ደውላችሁም ቢሆን አስመጡ ተባሉ ። ቲክቶከሮች ነን በልቶ ያለመክፈል ቪዲዮ እየሰራን ነው ብለው የቆዩ ቪዲዮዎቻቸውን አሳዩ። ለሬስቶራንቱም ማስታወቂያ ነው ብለው ሰከሱ ። ባለቤቱና ጥበቃዎች ጓዳ አስገብተው መከሯቸው። ሰሃኑንም አጠቡ። ለማስታዎሻ ይህንን ፎቶ አነሷቸው ። ችግሮችን በመመካከር መፍታት ይቻላል።

#huleadismedia

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENST
12.7K views14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 12:41:14
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በአንድ አካል ሁለት ጭንቅላት ያላቸው ልጆች ተወለዱ

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቪ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ አካል ጭንቅላታቸው የተያያዙ መንታ ልጆች አንዲት እናት መገላገሏን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው እለት ከምሽቱ 3፡30 ገደማ የወለደችው እናት እድሜዋ 40 ዓመት ሲሆን የአምስት ልጆች እናት መሆኗ ተገልፆል፡፡

ጭንቅላታቸው ተጣብቆ የተወለዱት ህፃናቶቹ እና እናትየው በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብሏል

በሆስፒታሉ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ እንደሆነ እና ወደ አዲስ አበባ ሪፈር እንደሚደረጉ ነገር ግን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከባድ መሆኑን  በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በንግሥት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕረሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዳነ ደስታ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡

በሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም ሁለት እና ሦስት መንትያ ልጆች ተወልደው ቢታወቅም ይህ ክስተት  የመጀመሪያ ነው ሲሉ ዶክተሩ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በደምቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል ሁለት ጭንቅላት ያለላቸው ልጆች መወለዳቸው ይታወሳል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
13.2K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 13:02:12
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንድ ለሊት ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ ሳይደርስበት እንደቀረ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6, ለሊት የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም ችግር ያጋጠመው ሲሆን የችግሩ መንስኤ በሞባይል አፕሊኬሽኑ update ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል።

የሞባይል ባንኪንጉ ተጠቃሚዎች ገንዘብ በሚያዘዋውሩበት ጊዜ ከአካውንታቸው ተቀናሽ ባለማድረጉ ምክንያት ባንኩን ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ሊጥል ችሏል።

በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አጋጣሚውን በመጠቀም በነፃ ወደ ሌሎች ባንኮች ገንዘብ ሲያዘዋውሩ አድረዋል።

ይህ ዜና እስከተሰራበት ጊዜ ድረስ የዚህ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ ሲስተም አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን ባንኩ የደረሰውን ችግር ወደነበረበት ለመመለስ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
13.5K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-23 20:07:14
"ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም" ያለው የሜድስን ተማሪ ከሞት ተርፏል

እምሩ ሙስጠፋ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የሜዲስን ተማሪ ሲሆን በማህበራዊ ትስስር ገፁ "ቤተሰቦቼን አደራ፣ እኔ ሰውን እኩል በማታይ ሀገር ውስጥ መኖር አልፈልግም፣ እኔ መኖር እፈልጋለው መኖር ግን አልተፈቀደልኝም፣ ባልፈጠር ይሻለኝ ነበር ባልፈጠር እኔንም ቤተሰቤንም አላስቸግርም" በማለት ራሱን እንደሚያጠፋ ከገለፀ በኋላ በጓደኞቹ፣ በፖሊስ እና በዩኒቨርሲቲው ጥረት ራሱ ላይ ጉዳት ሳያደርስ ተይዟል። ቤተሰብ እስኪመጣ በነቀምት ከተማ ፖሊስ እንደሚቆይ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሃሰን ዩሱፍ (PHD) ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K viewsedited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-20 12:14:08 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ገለፀ በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል። አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ያለው ባንኩ ለተፈጠረው…
12.6K views09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-20 10:53:22 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት መቋረጥ እንዳጋጠመው ገለፀ

በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ያለው ባንኩ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ ጠይቋል።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.8K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-19 20:30:59
ኢየሱስ ወደ ኢትዮጲያ መልዕክት ልኳል፦ Pastor Tee

አንድ ዓመት ብቻ ነው የቀራቹም ብሏል

የጌታ ታናሽ ወንድም ነኝ ,እናቴ ማርያም ናት አባቴ ዮሴፍ ነው ሲል የሰነበተው ኬንያዊ ናይሮቢ እና ዋንጅራ ከተሰኙት ሁለት የኬንያ ከተሞች ተልዕኮዬን ጨርሼ አዲስ አበባ ልመጣ ነውም ብሏል

ይህ ኬንያዊ ከኢየሱስ ለኢትዮጲያዊያን መልዕክት ይዤያለው ያለ ሲሆን ፤ይህንንም መልዕክት በቀጣይ ወር ይዞ እንደሚቀርብና እስከዛው ግን ምዕመኑ ፀሎት እንዲያደርግ አሳስባለው ሲል በx ገፁ አጋርቷል።

ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ማለትም 2025 ማርች ወር ላይ ወደ ዓለም እንደሚመጣ'ና የዓለም ፍፃሜም እንደሚያደርግ
ገልጿል።

ከዚያህ በፊት ግን አንድ ዓመት ብቻ ለቀራቸው ሀበሾች መልዕክት አድርስ ተብያለው ብሏል።


@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
12.6K viewsedited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-30 21:31:08
ከዓለማችን ትልቁ መርከብ አንዱ ወደ ካሪቢያን ደሴቶች ጉዞ ጀምሯል።

መርከቡ ከታይታኒክ መርከብ በ5 እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን ዋጋውም 2 ቢሊዮን ዶላር ነው።

7,600 መንገደኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን 20 ጋቢናዎች ፣ ከ40 በላይ ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎችና ቡና ቤቶች፣ ሞቃታማ ዕፅዋት ያሉት መናፈሻ፣ ቲያትር ቤተረ ፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ የውሃ ፓርክ አሉት።

@ETHIOSTUDENTS
@ETHIOSTUDENTS
14.8K viewsedited  18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ