Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-05-11 18:28:14
ለትግራይ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት 20 ሚልየን ብር የሚገመት የላባራቶሪ እቃዎች ድጋፍ ተደረገ

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለትግራይ የጤና ምርምር ኢንስቲትዩት 20 ሚልየን ብር የሚገመት የላባራቶሪ እቃዎችን በድጋፍ ማበርከቱን ተሰምቷል።

ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ተወክለው የህክምና መሳሪዎቹ ያስረከቡት አቶ ዳንኤል መለስ የህክምና ቁሳቁሶቹ የሟሟላት ሂደት  የመጀመርያ ዙር መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ዛሬ የተካሄደው የህክምና መሳርያ ድጋፍ በጤና ሚኒስትርዋ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ቃል በተገባው መሰረት መሆኑን የገለፁት የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሓየሎም ካሕሳይ የህክምና መሳሪዎቹ ተቋርጦ የነበረው የጤና ምርምር   ስራ ለማስጀመር የሚያስችሉ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

Via ድምፂ ወያነ
#ዳጉ_ጆርናል
2.7K viewsBeⓒk, 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 16:48:20
#በመሀል_ከተማ_ካሳንቺስ

ቅድመ ክፍያ 50%
100% ለሚከፍል 10% ቅናሽ ያገኛል

ስቱዲዮ
     47 ካሬ
     52ካሬ
ባለ1መኝታ
  67 ካሬ
72 ካሬ
91 ካሬ
94ካሬ
ባለ2ምኝታ
125 ካሬ
130 ካሬ
168ካሬ
ባለ 3 መኝታ
202 ካሬ

ብሩክ ሠጠኝ
የገበያና ሽያጭ ባለሙያ
አያት አ.ማ

+251912898237
@Bruk23

Telegram join
@Bruk_Sales_consultant
@Bruk_Sales_consultant
3.0K viewsTrue, 13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 13:11:10 የአቼቶ ምርቶች
1. ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR
2. ዋልታ አቼቶ
3. ሮያል አቼቶ/ROYAL Vinegar
4. ሌመን አቼቶ/LEMEN ACETO
5. ሸገር አቼቶ/SHEGER ACETO
የለዉዝ ቅቤ
1. በእምነት ኦቾሎኒ ቅቤ/BEMNET PEANUT BUTTER
2. ናይስ/Nice peanut butter
የቫኔላ ፍሌቨር
1. ምንም ገላጭ ጽሑፍ የሌለው የቫኔላ ፍሌቨር


#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsTrue, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 12:05:11
በብራዚል የ65 ዓመቱ ከንቲባ የ16 ዓመቷን ልጅ በማግባት ለወላጅ እናቷ ከፍተኛ ሹመት ሰ

በብራዚል አንድ ከተማ ከንቲባ በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይ የ16 ዓመቷን ልጅ በህጋዊ መንገድ ካገቡ በኃላ የሚስታቸውን እናት የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ዋና ኃላፊ አድርገው መሾማቸው ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል።የ65 አመቱ ዴሃይኒ በደቡብ ብራዚል የምትገኘው የአራካሪያ ከተማ ከንቲባ የሰጡትን ሹመት በፓራና ግዛት የሚገኘው አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ተቃውሞታል።

ከንቲባው ከሠርጋቸው ከአንድ ቀን በኋላ የሚስታቸውን እናት ሾመዋል።በብራዚል ህግ መሰረት እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ታዳጊዎች በወላጆቻቸው ፍቃድ ብቻ በህጋዊ መንገድ ጋብቻ መመስረት ይችላሉ። የሙሽሪትን እናት በማዘጋጃ ቤቱ አስተዳደር ውስጥ ጥሩ ክፍያ በሚያስገኝ የስራ መደብ ላይ ከንቲባው መሾማቸው ግን በብዙዎች ዘንድ እንደ ጉቦ ተወስዷል።

ለቀረበው ክስ ምላሽ የሰጠው የከንቲባው ጽሕፈት ቤት "ሹመቱ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቷል በማለት በሕዝብ አገልግሎት የ26 ዓመት ልምድ ስላላት ተሹማለች" ብሏል።ጥንዶቹ አጭርን ቢሆን ወደ ጫጉላ ሽርሽር መሄድ እንደሚኖርባቸው ይጠበቃል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
1.7K viewsTrue, 09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 20:56:23 መንግስት የገቢ ግብር እንዲቀንስ የሚጠይቅ ሰልፍ በአምስት ከተሞች ሊደረግ ነው

በአዲስአበባ በሚካሄደው ሰልፍ ከ 100 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል


በዓለም አቀፉ የሰራተኞች ቀን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ሰራተኞች ለጥያቄያቸው ሰልፍ ሊወጡ ነው
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) ለመንግስት ጥያቄ ለማቅረብ በሰራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ) ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ።

መንግስት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ይጠይቅበታል የተባለው ሰልፉ አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ከተሞች ይደረጋል ተብሏል።
የኮንፌደሬሽኑ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሰራተኛው በኑሮ ውድነቱ መኖር ባለመቻሉ ለመንግስት ጥያቄውን ለማቅረብ መገደዳቸውን ተናግረዋል።

በተለይም እንደ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያሉና በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ሰራተኞች ከ 8መቶ እስከ አንድ ሽህ 2መቶ ብር በወር እየተከፈላቸው መኖር እንዳልቻሉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፤ ባለው የኑሮ ውድነት ለሳምንት ህይወትን መግፋት ተዓምር ሆኗል።

"ደሞዝ ተከፋዩ ሰራተኛ መኖር አልቻለም፤ የኑሮ ውድነቱ በጣም ከፍ ብሏል፤ በዚህ ኑሮ ውድነት መንግስት ድጎማ ወይም ጭማሪ ሊሰጠን አይችልም፤ ቢያንስ ግን በዚህ ችግር ወቅት ከኛ ከሚሰበስበው የስራ ግብር ይቀንስልን፤ ተርበናል፤ የምንበላው አጣን ብለን ነው የምንጠይቀው" ብለዋል።

መንግስት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ በዓለም አቀፉ የሰራተኞች ቀን በአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ጅማና ሌሎችም ከተሞች ሰራተኞች አደባባይ እንደሚወጡ ተነግሯል።
ሰራተኞች የገቢያቸውን እስከ 35 በመቶ መቀረጣቸው ሳያበቃ፤ ውሎ አበላቸውና የትራንሰፖር ክፍያቸው እንዲሁም ሻይ ሲጠጡ 15 በመቶ ግብር መክፈላቸው ወቅቱን የዋጀ አይደለም።

ከ 6መቶ ብር በታች ገቢ ያላቸው ሰራተኞች ብቻ ግብር እንዳይከፍሉ መደረጉ ወቅታዊ የኑሮ ሁኔታን ያገናዘበ ባለሞሆኑ ዳግም ሊጤን ይገባል ያሉት የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት፤ ከ10 ዓመት በፊት የወጣ ህግ በመሆኑ ሰራተኞችን ለችግር እየዳረገ ነው ብለዋል።

“መንግስት ከካዝናው አውጥቶ ደሞዝ ይጨምር የሚል ጥያቄ የለንም” ሲሉ የገለጹት ካሳሁን ፎሎ ፤ ሆኖም ግን የሰራተኛውን ኪስ እያራቆተ ያለው የስራ ግብር መቀነስ አለበት ብለዋል። ይህን ጥያቄ ለመንግስት የሚያቀርቡና ከተለያዩ የሰራተኛ ማህበራት ይውጣጣሉ የተባሉ በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች የፊታችን ሰኞ ድምጻቸውን ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአዲስ አበባ ብቻ ከከተማዋና ከዙሪያዋ አካባቢዎች ከአንድ መቶ ሽህ በላይ ሰልፈኞች ወደ ጎዳናዎች እንደሚወጡ ፕሬዝዳንቱ ለአል አይን ተናግረዋል።

ከግብር ይቀነስልን ባሻገር ሰራተኞች በቀናቸው አደባባይ ሲወጡ፤ ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዲወሰን፣ የኤጄንሲ ሰራተኞች 20/80 ክፍያ ገቢራዊት እንዲሁም የመደራጀት መብትን እንደሚጠይቁ ካሳሁን ፎሎ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) በ1955 ዓ.ም. የተመሰረተ ከ800 ሽህ በላይ ሰራተኞችን በአባልነት የያዙ ሁለት ሽህ 200 ማህበራትን ያቀፈ እናት ማህበር ነው።

#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsBeⓒk, edited  17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 20:56:15
2.9K viewsBeⓒk, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 17:09:15 በዲጂታል መንገድ ክፍያ እንዲፈጸም በተደረገዉ የነዳጅ ግብይት አሽከርካሪዎች ቅሬታ አቀረቡ

በአንዳንድ ማደያዎች አሁንም በእጅ በእጅ ክፍያ የነዳጅ ሽያጭ እየተከናወነ ነዉ


ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በአዲስአበባ ተግባራዊ መደረግ በጀመረዉ ዲጂታል የነዳጅ ግብይት በርካታ አሽከርካሪዎች ቅሬታ እያቀረቡበት ይገኛሉ። ለጣቢያችን አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎች በአዲሱ የክፍያ ስርዓት አሉ ያሏቸዉን ችግሮች እና ጥቅሞች ተናግረዋል።

በርካቶች ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አቤቱታ እያቀረቡበት ያለዉ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ፤ በነዳጅ ሸማቾችም ሆነ ሻጮች በኩል የጠራ ግንዛቤ ባለመኖሩ ለእንግልት መዳረጋቸውን አሽከርካሪዎች ተናግረዋል። ብስራት ራዲዮም በአዲስአበባ ነዳጅ ማደያዎች አካባቢ ረጃጅም ሰልፎችን ታዝቧል።

አቶ ዩሀንስ አለማየሁ ፤ የሜትር ታክሲ አሽከርካሪ ሲሆኑ በዲጂታል መንገድ የተጀመረዉ የክፍያ ስርዓት ግብይታቸዉን ቀላል እና አመቺ እንዳደረገላቸዉ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ መያዝን እንዳስቀረላቸዉ ተናግረዋል። ሆኖም የግብይቱን ስርዓት በወጉ ላልተረዱ ሰዎች የሽያጭ መንገዱ አማራጭ የሚሰጥ ባለመሆኑ በበርካቶች ቅሬታ እየተነሳበት መሆኑን መታዘባቸዉን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ ስርዓቱን በወጉ የሚረዳበት ግዜ እንዲሰጠዉም ጠይቀዋል።

ሌላዉ አስተያየት ሰጪያችን አሁንም በአንዳንድ ማደያዎች በእጅ በእጅ ክፍያ የነዳጅ ሽያጭ እየተከናወነ መሆኑን መታዘባቸውን ተናግረዋል። ይህም አንዳንድ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያዎች በሚከፍሉት ጉቦ መሆኑን ተናግረዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ሌሎች አጋራ አካላቶቹ ጋር በመሆን የነዳጅ ግብይቱን ከእጅ በእጅ ንክኪ እንዲርቅ በማድረጉ መንግስት ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኝ እንደሚያስችለዉ ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል። ይህም ከዚህ ቀደም በነዳጅ ግብይቱ ላይ የማይታሰብ የነበረዉን የታክስ ገቢ መንግስት እንዲያገኝ ያስችለዋል።

ሆኖም የግብይት ስርዓቱ ላይ በርካቶች ተቃዉሞ ባይኖራቸዉም የተሳለጠ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት መቸገራቸዉን ሲገልጹ ይታያል። በአዲስአበባም ነዳጅ ለመቅዳት የሌሊት ሰልፎችም ጭምር እየታዩ ናቸዉ።

በአንጻራዊነት ለቴክኖሎጂ ቀረቤታ አለዉ በሚባለዉ የአዲስአበባ ማህበረሰብ በዚህ ደረጃ ፈታኝ የሆነዉ አዲሱ አሰራር ፤ በቀጣይ በመላዉ ኢትዮጵያ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉ ቀዉስ አስከትሎ እንደሚመጣ ብዙዎች ስጋታቸውን አስቀምጠዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ከ ግንቦት 1 ጀምሮ የዲጂታል ክፍያ ስርዓቱ በመላዉ ኢትዮጵያ ይጀመራል ማለቱን ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, 14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 14:32:18
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ ከ 3መቶ በላይ ቤቶች በእሳት አደጋ ወደሙ

በአለፋ ወረዳ በመንገላ አቫጅውሃ ቀበሌ ሮብ ገበያ ከተማ ከትላንት በስትያ በተከሰተው ድገተኛ የእሳት ቃጠሎ ከ 3መቶ በላይ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች መዉደማቸዉን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል፡፡

ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎው የተከሰተው ሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት አካባቢ ሲሆን በጥንቃቄ ጉድለት ከግለሰብ ቤት የተነሳ ነዉ ተብሏል። በአደጋው ከ 3መቶ በላይ የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ደርጅቶች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መውደማቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ኮማንደር በጋሻው ሽባባው ማስታወቃቸዉን ብስራት ከወረዳዉ ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል፡፡

ቃጠሎውን በቀላሉ ለመቆጣጠር ያልተቻለው በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ አውሎ ነፋስ እንደነበርና ቤቶች ተጠጋግተው በመሰራታቸው አደጋው የከፋ እንዲሆን አድረጎታል ብለዋል፡፡
በቃጠሎው የደረሰውን የንብረት ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ ተጣርቶ በቀጣይ ለህዝብ ይፋ እንደሚሆን ገልፀው ወቅቱ ነፋሻማ አየር የሚያይልበት በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

የወረዳው አደጋ መከላከልና መልሶ ማቋቋም ክትትል ባለሙያ አቶ አንባየ ይግዘው እንዳሉት በቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም ግብዓት በነፃ ብድር ሊመቻችላቸው እንደሚችል አብራርተዋል፡፡ በሌላ በኩል የወረዳው ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት ተወካይ አስተባባሪ አቶ አዲሱ ምልክት በበኩላቸው ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በመለየት ለሚመለከታቸው አካላት መረጃውን በማድረስ ሃብት በማፈላለግ ተጎጅዎችን በዘላቂነት ማቋቋም እንደሚቻል ገልፀዋል፡፡

በእሳት ቃጠሎው ጉዳት የደረሰባቸው የህብረሰብ ክፍሎችም እለታዊ የምግብ ፍጆታና ቁሳቁሶች እርዳታ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsBeⓒk, 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 13:48:05
በታይላንድ የዳይስ ጨዋታን ለ 40 ዓመታት ሳይሸነፍ የቀጠለው ቁማርተኛ ጣቶቹ ዉስጥ ማግኔት አስቀብሮ እንደነበር ታወቀ

አንድ የታይላንድ ዶክተር የታካሚውን እጅ ላይ የቀዶ ህክምና ካደረገ በኃላ ያጋጠመዉን በማህበራዊ ገጽ ትስስር ላይ አጋርቷል፡ታካሚዉ የዳይስ ጨዋታ ላይ ለማጭበርበር እንዲረዳው በጣቶቹ ውስጥ የከተተውን ማግኔት የተመለከተ ጉዳይ ሆኗል፡፡

በታይላንድ ቾን ቡሪ በሚገኘው የዊዋት ኤክስሬይ ክሊኒክ ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ዋት ሉን የህክምና ጉዳዮችን በየጊዜው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያካፍላሉ፡፡ ታዲያ በቅርቡ ለ40 ዓመታት ያህል የዳይስ ጨዋታ ለማጭበርበር በግራ እጁ የመሀል እና የቀለበት ጣቶቹ ዉስጥ ማግኔት ያስቀበረዉን ታካሚ ማግኔቱን ካወጡ በኃላ ምስሉን አጋርተዋል፡፡

ግለሰብ ማግኔቶቹን ለማውጣት የተገደደዉ በአውሮፕላን መጓዝ የግድ ስለሆነበት በኤርፖርት ፍተሻ ሲደረግበት የጸጥታ መሳሪያዎች እንዳይገኙ በመፍራት መሆኑን አስረድቷል።በምስራቅ እስያ ሀገራት ታዋቂ ከሆኑ የዉርርድ ጨዋታዎች መካከል ዳይስ ተመራጭ ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.1K viewsTrue, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 13:38:31
ቸሻየር ኢትዮጰያ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አደረገ

ቸሻየር ኢትዮጵያ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑን የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ማድረጉን እንዲሁም  አካል ጉዳተኞችን የማብቃት  አገልግሎት በሶስት መንገድ እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል ። እነዚህም በመልሶ ማቋቋም  ፣ተንቀሳሰቃሽ ግብረሀይል በማዘጋጀት እና  ቤት ለቤት የእገዛ  አገልግሎት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየሰራ እንደሚገኝ የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

በስልሳኛ ዓመት ክብረበዓሉ ላይ ትልቅ አስተዋጽ ያላቸውን ለማመስገን በመናገሻ ቸሻየር መልሶ ማቋቋም ማዕከል የተቋሙን የማስጎብኘት፣ የእግር ጉዞ እንዲሁም የድጋፍ መርሃግብር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።

በስምንት የእድገት ውስንነት ያለባቸው ህጻናት 
የተጀመረው ቸሻየር በአሁን ሰዓት  በ57 ከተማዎች አካል ጉዳተኞችን  በማገዝ  የተሃድሶ ፣ የስነልቦና በትምህርት አካል ጉዳተኞችን ማብቃት  ላይ እየሰራ እንደሚገኝ  ተነግሯል ።

ቸሻየር ኢትዮጵያን በአፍሪካ  ትልቅ የልቀት ማዕከል ለማድረግ  በአካል ጉዳት እና በልማት  ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑንን የቸሻየር የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት   ዶ/ር ግርማ አባብየ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, edited  10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ