Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-28 12:17:04 በናይሮቢ በታገተው ኢትዮጲያዊ ዙሪያ ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ፅፈናል ሲሉ አምባሳደር መለሰ ተናገሩ

የኬኒያ መንግስት ለደብዳቤው ስለሰጠው ምላሽ ግን አምባሳደሩ የሰጡት ማብራሪያ የለም


በኬኒያ ናይሮቢ ማንነታቸው ባልታወቁና የደንብ ልብስ በለበሱ አምስት ግለሰቦች የታገተው ኢትዮጲያዊ ሳምሶን ተክለሚካኤል ያለበት ሳይታወቅ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት አስቆጥሯል። ይህንኑ ተከትሎ የኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የኬንያ ኤምባሲ ላይ ክስ መመሥረታቸውን የታጋች ባለቤትና ጠበቃቸው ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሐለፎም፣ አቶ ሳምሶን በኬንያ ፖሊሶች ታፍነው ከተወሰዱ አንድ ዓመት ከስድስት ወራት ቢሆናቸውም፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ስለጉዳዩ ምርመራ እያደረጉ መሆናቸውን ከመግለጽ ባሻገር፣ ያሉበትን ሁኔታ ለማሳወቅ እየተንቀሳቀሱ ያለበት ሁኔታ ቸልተኝነት ታይቶበታል ማለታቸው አይዘነጋም።

ይህንኑ ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቀረበበት ቅሬታ ምን ምላሽ አለው በሚል ከጋዜጠኞች ጥያቄ ቀርቦለታል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለአቀባይ አምባሰደር መለስ አለም ጉዳዩ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱንና አሁንም እያደረገ መሆኑን በማንሳት ለኬኒያ መንግስት ሁለት ጊዜ ደብዳቤ ጽፈናል ማለታቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል።የኬኒያ መንግስት ለደብዳቤው ስለ ሰጠው ምላሽ ግን አምባሳደር መለሰ አለም ከመግለፅ ተቆጥበዋል።

በፌዴራል መንግሥትና በኦሮሚያ ክልል በማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የሕግ አማካሪ የሆኑት ጠበቃ ዳባ ጩፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ‹‹ደንበኛዬ በኬንያ በደረሰባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከአንድ ዓመት በላይ ያለበት አይታወቅም፤›› ብለው፣ መታሰራቸው ወይም መሞታቸው አለመነገሩ አሳሳቢ እንደሆነ መግለፃቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።
‹‹ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት የመጣበት ምክንያት እነዚህ የተከሰሱ አካላት ግዴታቸውን ባለመወጣታቸው ነው፡፡ ፍርድ ቤት በሕግ አግባብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማስገደድ የሚችል በመሆኑ እንደሚያስገድዳቸው እንጠብቃለን፤›› ሲሉም ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

በቤቴልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, edited  09:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 12:16:22
2.9K viewsTrue, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:46:02
በሱዳን የተቀሰቀሰው ግጭት ተከትሎ ኢትዮጲያ ግብረ ሃይል አቋቋመች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም በዛሬው እለት የሚኒስቴሩን ሳምንታዊ የስራ ማብራሪያና ከጋዜጠኞች ለተናነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።በሱዳን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሱዳን ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ጋር እና ከፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሀይሎች መሪ ዳጋሎን ጋር የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል።

ለሱዳን ህዝብ ሰላም እንዲመጣ ሁለቱ መሪዎች እድል  መስጠት እንደሚያስፈልጋቸው እና የውስጥ ችግር ለመፍታት በቂ አቅም ያላቸው ስለመሆናቸው  በስልክ ውይይቱ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ  ተናግረዋል።ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተየያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ግብረ ሃይል መኖራቸውን ባለሙያዎች እስከ ጋራ ድንበር ተልከው እየተሰራ መሆኑን አምባሳደር መለሰ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል ።

ግጭቱ ኢትዮጵያ ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ፣ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዜጎች ካሉ በምን መልኩ እናስተናግድ በሚል እና ዜጎች የቆንስላ አገልግሎት እያገኙ ወደሃገራቸው እንዲመጡ ግብረ ሀይሉ ይሰራል ተብሎ ይጠበቃል።ሱዳን ውስጥ ከ 100 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን አሉ ሁሉም ዜጎች ሰላም እንዲሆኑ እንሰራለን ብለዋል። እስካሁን በ100 የሚቆጠሩ  የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ከሱዳን በኢትዮጵያ ስለማለፋቸውም ጨምረው ተናግረዋል።

በቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, 08:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 11:04:11
ሩሲያ በፈጸመችዉ የሚሳኤል ጥቃት 12 ሰዎች ተገደሉ

ሩሲያ ኪየቭን ጨምሮ በመላው የዩክሬን ከተሞች ላይ በፈጸመችዉ የአየር ጥቃት ቢያንስ 12 ሰዎች ተገድለዋል፡፡በማዕከላዊ ኡማን ከተማ ሚሳይሎቹ በመኖሪያ ሕንፃዎች ላይ መዉደቃቸዉን ተከትሎ 10 ሰዎች መሞታቸውን የዩክሬን መንግስት ባለሥልጣናት ተናግረዋል።አንዲት ሴት እና የሶስት አመት ልጇ በዲኒፕሮ ከተማ በጥቃቱ መገደላቸዉን የከተማዋ ከንቲባ ተናግረዋል፡፡ኢንተርፋክስ የዜና ወኪል እንደዘገበው በክሬመንቹክ እና ፖልታቫ ከተሞች ፍንዳታ እንደነበር አስነብቧል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በኡማን 10 የመኖሪያ ሕንፃዎች ተጎድተዋል ሲሉ በመግለጽ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ዓለም አቀፍ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ።ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች በሩሲያ ላይ መጠናከር እንዳለበት ፕሬዝዳንቱ አክለዋል፡፡የኪየቭ ከተማ ወታደራዊ አስተዳደር ኃላፊ በዋና ከተማዋ ላይ ከ51 ቀናት በኃላ የተሰነዘረ የመጀመሪያው የሩሲያ ሚሳኤል ጥቃት ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡በመዲናዋ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት እስካሁን የተገኘ መረጃ የለም።

በሩሲያ ከተሰነዘሩት 23 ሚሳኤሎች ዉስጥ 21ዱ እንዲሁም ሁለቱ አጥቂ ድሮኖች ላይ በዩክሬን አየር መከላከያ በተወሰደ እርምጃ በሚሳኤል መቃወሚያ ማክሸፍ መቻሉን የዩክሬን መንግስት ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ጥቃቱ የተፈጸመው የዩክሬን ሃይሎች በምዕራባውያን አጋሮች የተሰጡ ታንኮችን ጨምሮ አዳዲስ መሳሪያዎችን በመያዝ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጁ ነው ተብሎ በሚታመንበት ወቅት ነው።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.1K viewsTrue, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 09:24:15
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአቶ ግርማ የሺጥላ ላይ የተፈጸመዉን ግድያ አወገዙ

በወንድማችን አቶ ግርማ የሺጥላ በስራ ላይ እያሉ በታጠቁ ሃይሎች በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ስሰማ ከፍተኛ እና ጥልቅ የሆነ ሀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን።

አቶ ግርማ እና የግል ጠባቂዎቻቸው ላይ የተፈጸመው ድርጊት ፍጹም ተቀባይነት የሌለው፣ የህዝባችንን እሴት የማይመጥን ነውር እና ህገወጥ ድርጊት ነው ሲሉ አክለዋል። አቶ ግርማ የህዝብ ህይወት እንዲሻሻል የተሰጠውን ህዝባዊ ኃላፊነት እየተወጣ የሚገኝ መሪ ሲሆን በህልፈቱ ለመላው ለክልላችን እና ሀገራችን ህዝቦች ከፍተኛ ጉዳት ነው።

መንግስት ይህን ድርጊት የፈጸሙ አካላትን ለህግ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ይሰራል ያሉ ሲሆን ሟች ፈጣሪ ነፍሱን በገነት እንዲያኖርው፥ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጅ ዘመዶቹ እና መላው ህዝባችንም መጽናናትን እንዲሰጥልን እመኛለሁ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.3K viewsBeⓒk, 06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 09:17:17
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦርነት መሪዎች ጋር በስልክ ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ጦር ኃይሎች መሪ ጄኔራል አብደልፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ጋር በስልክ መወያየታቸውን ገለጹ።

ታላቁ የሱዳን ሕዝብ ሰላም ያስፈልገዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁለቱ መሪዎች ልዩነቶቻቸውን በመግባባት እንዲፈቱ እና ለሀገራቸው መረጋጋትን ማምጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.3K viewsBeⓒk, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 23:16:20 የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

ሁለተኛዉ አጋማሽ 54'

ማንችስተር ሲቲ 2-0 አርሰናል
ዴብራየን
ስቶንስ
ዴብራየን

#ዳጉ_ጆርናል
329 viewsBeⓒk, 20:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 23:08:12
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

ሁለተኛዉ አጋማሽ ተጀምሯል
45'

ማንችስተር ሲቲ 2-0 አርሰናል
ዴብራየን
ስቶንስ

#ዳጉ_ጆርናል
488 viewsBeⓒk, edited  20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:23:05 የኢራን ፍርድ ቤት አሜሪካ እና ኦባማ ለ'አሸባሪዎች' ጥቃት የ313 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንዲከፍሉ አዘዘ

የኢራን ፍርድ ቤት በ2017 በአይኤስ ቡድን ለተፈፀመው ጥቃት የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እና የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች እና አካላት ካሳ እንዲከፍሉ ወስኗል።በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን የሚገኘው ፍርድ ቤት በሰኔ 2017 በተፈፀመው ጥቃት የአስራ ሰባት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካታ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ የሶስት ሟች ቤተሰቦችና ስድስት ተጎጂዎች ባቀረቡት ቅሬታ መሰረት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል ሲል የፍትህ አካላት ይፋዊ የዜና ድረ-ገጽ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ 9.95 ሚሊዮን ዶላር ለተጎጂዎች ካሳ መከፈል እንዳለበት ወስኗል፣ 104 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ የሞራል ካሳ እና 199 ሚሊዮን ዶላር ለሀብት ዉድመት በአጠቃላይ 313 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፈል አዟል።ክስ የቀረበባቸዉ የአሜሪካ መንግስት፣ ኦባማ፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብልዩ ቡሽ፣ ሴንትራል ኮማንድ (CENTCOM) እና የቀድሞ አዛዡ ቶሚ ፍራንክ፣ የማዕከላዊ መረጃ ኤጀንሲ፣ የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት፣ የጦር መሳሪያ አምራች ሎክሂድ ማርቲን እና የአሜሪካ አየር መንገድ ቡድን ይገኙበታል።

ለጥቃቱ ለምን ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትወቀስ ድረ-ገጹ ባሰፈረዉ መረጃ የአሜሪካ ባለስልጣናት “አሸባሪ ቡድኖችን በማደራጀት እና በመምራት” የተጫወቱት “መሰረታዊ” ሚና፣ በአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የሚታተሙ ዜናዎች እና መረጃዎች እንዲሁም መጽሃፎች እና ንግግሮች የአሜሪካ ባለስልጣናት ያላቸውን አስተያየት መነሻ በማድረግ ነዉ። የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት አይኤስን ጨምሮ “የሲአይኤ አሸባሪ ቡድኖችን በመፍጠር የሚጫወቱት ሚና” ከፍተኛ መሆኔን አንስቷል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
1.5K viewsTrue, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-26 21:03:49 በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል

በኦሮሚያ ክልል ከሚያዝያ 09 እስከ ሚያዝያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ19 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ34 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ37 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ መረጃ ጥናት እና አገልግሎት ዲቪዥን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

አደጋዎቹ ምእራብ ወለጋ አርያ፣ ምስራቅ አርሲ ጀጆ፣ ሰሜን ሸዋ ደገም፣ቦረና ዞን ድሬ፣ምስራቅ ወለጋ ጂጋ፣ምእራብ ሸዋ ኤጀርሳ ወረዳዎች እና አንቦ፣ሮቤ ከተማዎች የደረሱ ናቸው።

አደጋዎቹ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ለሊቱ 6 ፣00 ሰዓት የተመዘገቡ ሲሆን አብዛኛዎቹ የሞት አደጋዎች የደረሱት በጭነት ተሽከርካሪ፣ በህዝብ ማመላለሻ እና በሞተር ሳይክል እና በሶስት እግር (ባጃጅ) አሸርከርካሪዎች የተከሰቱ መሆናቸው ተገልጿል።

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፤ መንስኤዎቹ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣የተሽከርካሪ የቴክኒክ ችግር፣ርቀትን ጠብቆ አለማሽርከር መሆኑን ረዳት ኢንስፔክተር ታደለ ሌጂሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
1.7K viewsTrue, 18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ