Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-06 11:26:58
መንግስት 2 ሚሊዮን የሰራተኛ ስራ ስምሪት ጥያቄ ከዉጭ ሀገራት እንደቀረበለት አስታወቀ

ባለፉት 11 ወራት 3.1ሚሊየን  ገደማ ሰዎች ስራ ይዘዋል ተብሏል


ጠ/ሚ አብይ አህመድ የስራ እድል እና ፈጠራ ክህሎት በሚኒስቴር  ደረጃ ኢትዮጵያ ውስጥ ተቋቁሞ እንደማያውቅ ለተወካዮች ምክር ቤት በሚያብራሩበት ወቅት ገልፀዋል ።

ከተለያዩ ዓለም ሀገራትም መንግስት 2 ሚሊየን ገደማ የሰራተኛ ስምሪት ጥያቄ ቀርቦለት እየተፈራረመ መሆኑን  ጠ/ሚንስትሩ ተናግረዋል። በዚያ ደረጃ እንዲቋቋም የተፈለገበት ደረጃ ስራ አጥነትን መቀነስ ነው ስራ አጥነትን መቀነስ ሰላም ያመጣል ብለዋል።

በቅርቡም የኩዌት መንግስት በወርሃዊ የ
3መቶ የአሜሪካን ዶላር በደረሰ ክፍያ ሰራተኞችን ለመዉሰድ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር መስማማቱን ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

ሰፋፉ የስራ እድል ቢፈጠር ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር ይቀነሳል የሚል እምነት በመያዙ ተቋሙ በሪፎርሙ በሚኒስትር ደረጃ እንዲቋቋም መደረጉን ገልፀዋል።

ከፍተኛ ለውጥ እያመጡ ካሉ የፌደራል ተቋማት አንዱ የስራ እድል እና ፈጠራ አንዱ መሆኑን አንስተዋል። በተጨማሪ የስራ ስምሪት ቁጥጥር በሀገር ውስጥ መቶ በመቶ በሚቀጥለው ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል ። ማን ስራ እንደያዘ እና የት ስራ እንደያዘ ስለሚታወቅ የውሸት ሪፖርቶችን ለማስቀረት ይረዳል ብለዋል ።

ባለፉት 11 ወራት 3.1ሚሊየን ገደማ ሰዎች ስራ መያዛቸውንም ገልፀዋል። ከነዚህም ውስጥ በግብርና 1.2ሚሊየን የሚጠጋ ሰው፣በኢንደስትሪ 600ሺ ገዳማ፣ አገልግሎት፣1.2ሚሊየን ገደማ፣ለውጭ ህጋዊ በሆነ መንገድ 100ሺ ሰው ገደማ ስራ መያዙን ጠቅሰዋል።

በምህረት ታደሰ
#ዳጉ_ጆርናል
2.7K viewsBeⓒk, edited  08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 10:44:24
በሁሉም ባንኮች በቁጠባ የተሰበሰበው ገንዘብ 2.1 ትሪሊዮን መድረሱን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ተናግረዋል

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ያሉ የባንኮች ቁጥር 31 መድረሱን ተናግረዋል። የመንግስታቸዉ ለዉጥ አንዱ የሆነዉ የኢኮኖሚያዊ መሻሻል ማሳየት መቻሉ መሆኑን የተለያዩ ማጣቀሻዎችን አንስተዉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት የባንኮችን ቁጥር ከፍ ከማድረግ በዘለለ በሁሉም ባንኮች በቁጠባ የተሰበሰበው ገንዘብ መጠን 2.1 ትሪሊዮን መሻገሩን ገልጸዋል። ከዚህ ዉስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ መጠን ብቻ ከ 1 ትሪሊዮን ብር በላይ መሻገሩን ብስራት ራዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።

በተጨማሪም 100 ሚሊዮን የቁጠባ ሂሳብ  መከፈቱንም አክለዋል። በሌላ በኩል  የባንኮችን ቅርንጫፎች ተደራሽ ከማድረግ አኳያ 11 ሺህ ገደማ የደረሱ የሁሉም የባንክ ቅርንጫፎች በመላዉ ኢትዮጵያ እንዳሉ ገልጸዋል። 461 ቢሊዮን ብር ብድር መሰጠቱንም ተናግረዋል። ከዚህ ዉስጥም 85 በመቶኛዉ ለግል እንዲሁም ቀሪዉ 15 በመቶዉን ብድር መንግስት መዉሰዱን ጠቁመዋል።

በዲጂታል መንገድም እስካሁን ከ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ብድር መዉሰዳቸዉን ተናግረው ይህም ባንኮች ለህብረተሰቡ ከሚያቀርቡት ብድር በተሻለ ማሰራጨቱን ገልጸዋል።

የአጠቃላይ የሁሉም ባንኮች ሀብትም አሁን ላይ 2.9 ትሪሊዮን ብር መድረሱንም ጨምረዉ ተናግረዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
2.8K viewsBeⓒk, edited  07:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 10:10:24
በተያዘዉ አመት ኢትዮጵያ የ 7.5 በመቶ እድገት ይኖራታል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል

የአለም ገንዘብ ድርጅት በአንጻሩ ኢትዮጵያ የ6.1 እድገት ይኖራታል ብሎ ተንብዯል


ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በዛሬዉ እለት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 2ኛ አመት 28ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው በተያዘዉ አመት ኢትዮጵያ የ 7.5 በመቶ እድገት ይኖራታል ብለን እንጠብቃለን ሲሉ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

አጠቃላይ የአለም ሀገራት እድገት እየቀነሰ ነዉ ያሉት ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ እድገት በአንጻሩ በ 7.6 በመቶኛ እንደሚያድረግ ገልጸዋል።

የአለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራትም በባለፈዉ አመት 3.8 በተያዘዉ አመት 3.6 በቀጣዩ አመት ደግሞ 4.2 በመቶኛ እድገት እንደሚያስመዘግቡ ይጠብቃል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዚሁ ተቋም በተተነበየዉ መሰረትም በባለፈዉ አመት 6.4 በመቶ እድገት እንዳሳየች ተቋሙ አሳዉቋል ብለዋል። በዚህኛዉም አመት 6.1 በመቶ እድገት እንደሚኖር ገምቷል ብለዋል። በቀጣዩም አመት ኢትዮጵያ የ 6.4 እድገት እንደምታስመዘግብ ገምቷል ብለዋል።

በተያዘዉ አመትም የአለም ገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ ይኖራታል ብሎ ከሚገምተዉ የ6.1 በመቶ በበለጠ መንግስት የ 7.5 በመቶ እድገት ይጠብቃል ብለዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsBeⓒk, edited  07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 09:51:11
የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ካነሱት ሌላኛዉ ጉዳይ ዉስጥ - ገዢዉ ፓርቲ ብልጽግና አመጣለሁ ቢልም በተግባር ለኢትዮጵያ ህዝብ ያመጣለት ጉስቁልና ሆኗል። ለወደቀዉ የእርሶ እና የፓርቲዎ አመራር መፍትሔዉ ምንድነዉ? የሀገራዊ ቀዉስ መፍትሔ አፈላላጊ ጉባዔ እንዲዘጋጅ አድርገዉ ሳይረፍድ መፍትሄ ቢበጅ አይሻልም ወይ? እንደ ህዝብ ተወካይነቴ ብልጽግና መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማ ሀገራችን ከገባችበት ፖለቲካዊ ቅርቃር ማዉጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ እና ፓርላማዉንም እንዲበትኑ እና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsBeⓒk, edited  06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 09:45:21
"ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ። ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል። በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ(የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ።" የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለ ጠ/ሚ አብይ ካነሷቸዉ ጉዳዮች መካከል።

#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsBeⓒk, edited  06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 09:41:16
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአብን እና የምክርቤቱ አባል ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ - ጠ/ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል ፣ ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsBeⓒk, edited  06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 09:36:16
በአዲስአበባ እና በሸገር ከተሞች ከተከናወነዉ የቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ለምን በወቅቱ ማስቆም አልተቻለም? ቤት የፈረሰባቸው ሰዎችና የሀይማኖት ተቋማት እጣ ፋንታስ ምንድነዉ? የተከበሩ አቶ አኔሳ ሚልኮ ለጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ያነሱት ጥያቄ።

#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsBeⓒk, 06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 18:05:31
የማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ፈቃድ ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ፈቃድ ማገዱን አስታዉቋል።

ባለስልጣኑ ጣቢያዉን ያገድኩት፤ ቅዱስ ሲኖዶስ እያደረገ ያለዉን ስብሰባ አስመልክቶ ግንቦት 13 ቀን ሰበር በሚል ባሰራጨው መረጃ መሆኑን ጠቅሷል። ይህም ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ መልዕክት በማሰራጨቱ ነዉ ብሏል።

በቀጣይ የባለስልጣኑ ቦርድ ተወያይቶ ዘላቂ ዉሳኔ እስኪሰጥ የጣቢያዉን ፈቃድ አግጃለሁ ብሏል።

#ዳጉ_ጆርናል
2.1K viewsBeⓒk, edited  15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 15:33:02 የአቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅም በዓል በደብረ ሊባኖስ ገዳም በርካቶች በተገኙበት ተከበረ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ሊባኖስ ወረዳ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም የአቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅም ዓመታዊ ክብር በዓል በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እንደተከበረ ተገልጿል ።

ለክብረ በዓሉ ከአዲስ አበባ ፣ቢሾፍቱ ፣ ከደብረብርሃን እና ከሌሎች አካባቢዎች የተውጣጡ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው በዙ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

ይኸው ክብረ በዓል አቡነ ተክለሃይማኖት መጀመሪያ ከተቀበሩበት ዋሻ አፅማቸው ተነስቶ ግንቦት 12 ቀን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ያረፈበትን ዕለት ለማሰብ የሚከበር ነው ። ደብረ ሊባኖስ ገዳም የካቲት 16 ቀን 1267 ዓ.ም በፃዲቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የተመሰረ ሲሆን ገዳሙ ለዕይታ ማራኪ የሆነ አቀማመጥ ሲኖረው ዳግማዊ እየሩሳሌም በመባል ይታወቃል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
2.7K viewsTrue, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 13:34:30
ክፍት የስራ ማስታወቂያ

Telegram join
https://t.me/Bruk_Sales_consultant

በሀገራችን  የሪል እስቴትገቢያ እና ሽያጭ  መሰረታዊ  የፍላጎቶችን ለማድረስ እና የሚታዩ  ችግሮችንም  በቀላሉ ለመቅረፍ የሚስችል ከመሆኑም በላይ ለራስዎም መልካም የስራ እድል በመፍጠር  በቂ ልምድ  እውቀት እና ክህሎት ካላቸው  የሪል እስቴት ገቢያ እና ሽያጭ አማካሪዎች  ጋር ለመስራት የሚስችልዎትን  እድል አመቻችተናል ።

ስራዎት ሳይበደል ጊዜ ሳይባክን ከ25ሺ  እሰከ 100ሺ ብር ማግኘት የሚስችለዎትን የኮሚሽን ስራ  አዘጋጅተናል ። አሰፈላጊ የሆነ የሪል እስቴት ስልጠናወችንም እንሰጣለን ። ከዚህ በፌት የሪል እስቴት የስራ ልምድ ያላችሁም ከሆነ በደስታ እንቀበላለን ።
ይግዙ ይሽጡ ያማክሩ ያለዎትን ሪሶርስ በቀላሉ ይጠቀሙበት ።
መረጃ እውቀትም ገንዘብም  ነው ።
ጊዜ ወርቅ ነው ።

ይደውሉ

ብሩክ ሠጠኝ
የገበያና ሽያጭ ባለሙያ/አማካሪ

+251912898237


Telegram join
https://t.me/Bruk_Sales_consultant
2.9K viewsTrue, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ