Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-19 20:26:43
የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን ተቀናቃኛቸዉንና ምክትላቸው ዳጋሎን ከስልጣን አነሱ

የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ምክትላቸውን እና የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች (RSF) አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቱ በመባል የሚታወቁትን ከስልጣናቸው አሰናብተዋል፡፡

ጄኔራል ቡርሃን እና ሄሜቲ ከጥቅምት 2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ የገዢው ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር እና ምክትል ሆነው አገልግለዋል።ጀነራል ቡርሃን በዛሬዉ እለት በተለቀቀው አዋጅ የቀድሞ የአማፂ ቡድን መሪ የነበሩትን ማሊክ አጋርን ምክትል አድርገው ሾመዋል።

ማሊክ አጋር የሱዳም ሉዓላዊው ምክር ቤት አባል ናቸው።የሉዓላዊው ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አዋጁ በአስቸኳይ እንዲተገበር መመሪያ ሰጥቷል።የጦር አዛዡ አል ቡርሃን ባለፈው ወር የአርኤስኤፍን ቡድን እንዲበተን በማድረግ ተዋጊዎቹን በአማጺነት ከፈረጀ በኃላ በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የስልጣን ሽኩቻ ተፈጥሯል፡፡

ሱዳን ከዚያን ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ጦርነትና ትርምስ ውስጥ ገብታለች።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
4.0K viewsTrue, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 17:11:59 በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምና ሊጀምር መሆኑን የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታወቀ

የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የግንባታ ሂደቱ በመጠናቀቅ ላይ በሚገኘዉ የካንሰር ማዕከል በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምናን እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡በሆስፒታሉ የህጻናት የደምና የካንሰር ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ማሙዴ ድንቅዬ በተለይ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ህፃናት ከሚጠቁበት የካንሰር አይነቶች መካከል የደም ካንሰር ከፍተኛ ድርሻ እንዳለዉ ገልጸዋል፡፡

በዚህም የተነሳ በርካታ ህጻናትን ከደም ካንሰር ለመታደግ ሲባል ሆስፒታሉ ይህንን የህክምና አገልግሎትን በቅርቡ ለመጀመር ማቀዱን ተናግረዋል፡፡ዶክተር ማሙዴ አክለውም የመቅኔ ንቅለ ተከላ ህክምና ከህጻናት የደም ካንሰር ውጪ ለማንኛውም በሰውነት ውስጥ ሊሰራጭ ለሚችል ካንሰር መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል መሆኑን አክለዋል፡፡

ህክምናውንም ለመስጠት ከወዲሁ የህክምና ባለሙያዎችን ከማሰልጠን ጀምሮ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶች መከናወናቸው ተገልጿለረ፡፡በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የካንሰር ህክምና በዝቅተኛ ሂደት ላይ የነበረ በመሆኑ በርካታ ህሙማን ለሞትና ለከባድ ህመም ስቃይ ሲዳረግ ነበር፡፡

የንቅለ ተከላ ህክምናው እንዲሰጥ መታቀዱ ይህንን ችግር ይቀርፋል ተብሎ የታመነበት ሲሆን በርካታ ህጻናትን ከሞት ለመታደግ ያስችላል፡፡

በቅድስት ደጀኔ
#ዳጉ_ጆርናል
4.0K viewsTrue, 14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:38:50
ራህዋ ክንፈ"ሚስ ብላክ ቤልጂየም" ትግራይን በመወከል አሸነፈች

በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይን ግጭት ሸሽታ ቤልጅየም ውስጥ ጥገኝነት የጠየቀችዉ ወጣት በሚስ ብላክ ቤልጂየም የ2023 የቁንጅና ውድድር ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።ራህዋ ክንፈ የትግራይን ባህልና እሴት በአለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ ኩራት እንደተሰማት ተናግራለች።

አብዛኞቹ ተወዳዳሪዎች ሀገራቸውን ወክለው በውድድሩ ላይ ቢሳተፉም ራህዋ ግን በምትኩ ክልሏን ትግራይ እንድትወክል የተፈቀደላት የራሷ ባንዲራ፣ ባህልና ታሪክ እንዳለው ለአዘጋጆቹ ከተናገረች በኋላ እንደሆነ ገልጻለች።በፌደራል መንግስት እና በትግራይ አመራሮች መካከል የሰላም ስምምነት መፈራረሙን ተከትሎ ባለፈው አመት ህዳር ላይ ያበቃው ጦርነት፣ በክልሉ ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች ህይወት ቀጥፏል፡፡በግጭቱ ወቅት በርካታ ሴቶች እና ልጃገረዶች አስገድዶ መድፈር እና ጾታዊ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ስትል ገልጻለች።

ባለፈው አመት መጋቢት ወር ወደ ቤልጂየም የተሰደደችዉ ራህዋ ተወልዳ ያደገችው በታሪካዊቷ የትግራይ ከተማ አክሱም ነዉ።ለአምስት ዓመታት ያህል ለኢትዮጲያ አየር መንገድ በበረራ መስተንግዶ ሰርታለች። የእርስ በርስ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ለእስር ተዳርጋ እንደነበር ተገልጿል፡፡“በርካታ ጓደኞቼ ታስረዋል፣ እና መውጫ አጥተን ነበር፡፡ ከተፈታሁ በኋላ ወደ ቤልጂየም መጣሁ” ስትል ተናግራለች።

ውድድሩ ሌሎች እድሎችን ከፍቶልኛል በሚስ ቤልጅየም ውድድር ላይ በቀጥታ እንድወዳደር የሚያስችለኝም “ወርቃማው ትኬት” ቀርቦልኛል ስትል ተናግራለች፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsTrue, 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:28:19
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ በአረብ ሊግ ጉባኤ ለመሳተፍ ድንገተኛ ጉብኝት ወደ ሳዑዲ አረቢያ አደረጉ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በአረብ ሊግ አመታዊ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ በዛሬዉ እለት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ድንገተኛ ጉዞ አድርገዋል።በጉባኤዉ ላይ ንግግር ያደረጉት ዘሌንስኪ አረንጓዴ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሰዉ ሲሆን "አብዛኛዎቻችን እዚህ ያለነው ለሰላም እና ለፍትህ ነዉ " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ጠላታችን ያለዉን ያህል ሚሳኤል የለንም ግን አነስተኛ የአየር ኃይል አለን ፤ ኢራን ለሩሲያ የምታቀርበው በርካታ ገዳይ አውሮፕላኖች የለንም። ያን ያህል መድፍ የለንም፤ ነገር ግን እዉነት እኛ ጋር ስላለ በጥንካሬ እንቆያለን” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ዘሌንስኪ በመቀጠል “የዩክሬን ሙስሊም ማህበረሰብን ጨምሮ ህዝባችንን ለመጠበቅ ለሁላችሁም የተከበረ ጥሪ” ማቅረብ እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

በክራይሚያ ባሕረ ገብ የሱኒ ሙስሊሞች የቱርኪክ ቡድን የክራይሚያ ታታር ማህበረሰብ መሪ ሙስጠፋ ዛሚሌቭ በሥፍራው ተገኝተው ነበር።ዘለነስኪ በተጨማሪም የዩክሬን ኢኮኖሚያዊ እና ትምህርታዊ ትስስር ከአረቡ ዓለም ጋር ያለውን ጠቀሜታ ገልጸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.3K viewsTrue, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:23:24 ፖሊስ መስከረም አበራን ጨምሮ ስድስት ግለሰቦች ላይ ምርመራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የ7 ቀን ጊዜ ተፈቀደ!

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ የሰራውን እና ቀረኝ ያላቸውን የምርመራ ሥራዎች እንዲሁም የተጠርጣሪዎችን የመከራከሪያ ነጥቦች መርምሮ እንዲያቀርብ የ7 ቀናት የምርመራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎቹ መስከረም አበራ፣ ሳሮን ቀባው፣ ዮርዳኖስ አለሜ፣ ቢሰጥ ተረፈ፣ አሰፋ አዳነ (ዶ/ር) እና ታደለ መንግስቱ ትናንት በነበራቸው ቀጠሮ ከአምስት ጠበቆቻቸው ጋር ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ከዚህ በፊት በተሰጠው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ ከ15 ባንኮች ማስረጃ ማምጣቱን፣ የተጠርጣሪዎችን የጣት አሻራ ማስነሳቱን፣ የኋላ ታሪካቸውን የመለየት ስራ መስራቱን፣ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ ቁጥር 27/2 መሰረት የተከሳሽነት ቃላቸውን መቀበሉን፣ የቴክኒክና የፎረንሲክ ማስረጃዎችን በከፊል ማስመጣቱን እና በተጠርጣሪዎች መኖሪያ ቤት ብርበራ ማድረጉን ገልጿል።

ቀሪ ያላቸውን ሥራዎች ማለትም በወንጀለኛ መቅጫ ስነ/ህግ ቁጥር 30 መሰረት የቀሪ የምስክር ቃል መቀበል፣ ከቀሪ ባንኮችና ከተለያዩ ተቋማት ማስረጃዎችን ማስመጣት፣ በአማራ ክልል በተፈጸመ የሁከትና አመፅ ማስነሳት ተግባር ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን ውጤት ከፌደራልና ከክልል ተቋማት ማስመጣት ፣ ግብረዓበር ተከታትሎ የመያዝ ስራ እንደሚቀረው ጠቅሶ በወ/መ/ስነ/ህግ ቁጥር 59/2 መሰረት ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጠው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢወጡ ከአገር ሊሸሹ ይችላሉ ሲል ግምታዊ ስጋቱን ገልጾ፤ የዋስ መብታቸው እንዳይፈቀድም ጠይቋል።የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ‹‹ፖሊስ በተሰጠው የምርመራ ጊዜ ውስጥ ዕድገት ያለው ምርመራ አላደረገም›› ሲሉ ተከራክረዋል።ቀሪ ሥራ ተብሎ የቀረበው ምክንያቶች ለተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ሆነው መቅረባቸው ተገቢነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።

በተጨማሪም ‹‹ተጠርጣሪዎች በእስር በቆዩባቸው ጊዜያቶች የተሳትፎ ድርሻቸው ተለይቶ አልቀረበም፣ ደንበኞቻችን በዋስ ቢወጡ የሚፈጥሩት መሰናክል ስለመኖሩ በፖሊስ ባልተገለፀበት ሁኔታ ላይ ደንበኞቻችን በእስር የሚቆዩበት ምክንያት የለም›› በማለት ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የዋስትና መብት እንዲፈቀድ የጠየቁ ሲሆን፤ በተጨማሪም ምንም ምስክር አልቀረበም ሲሉም ተከራክረዋል።

ዮርዳኖስ የተባለው ተጠርጣሪና መስከረም አበራ በሙያቸው እንደሚሰሩና ‹‹ለእስር የሚዳርግ ድርጊት አልፈፀምንም›› ብለው ተከራክረዋል።ፖሊስ በበኩሉ ማንም ሰው ያለምክንያት በቁጥጥር ሥር እንደማይውልና የወንጀል ተሳትፎ የመነሻ ጥርጣሬ ሲኖር ብቻ ወደ ህግ እንደሚቀርብ አስረድቷል።

የተጠርጣሪዎቹ ተሳትፎ ተለይቶ አልቀረበም ለሚለው የጠበቆች የመከራከሪያ ነጥብን በሚመለከት ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የፖለቲካና ፣ የወታደራዊና የሚዲያ ክንፍ በማዋቀር በህቡዕ በመደራጀት የተደረገ የሽብር ወንጀል ተግባር እንቅስቃሴ መኖሩን የሚያመላክት ማስረጃ ሰብስበናል ሲል መልስ ሰጥቷል።በዚህ መልኩ መርተው በቀሰቀሱት አመፅና ብጥብጥ ምክንያት ከ18 ሰው በላይ ህይወት መጥፋቱን፣ ከ46 የሚበልጡ ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን እና በሚሊየኖች የሚቆጠር ንብረት ላይ ጉዳት ተከስቷል ሲል ፖሊስ በሰጠው ምላሽ አብራርቷል።

በተጨማሪም መርማሪው ከተጠርጣሪዎች መካከል አንድ ተጠርጣሪ በአዲስ አበባ እና በሌሎች አካባቢዎች የሽብር ወንጀል ጥቃት እንዲፈጸም በማቀድ 10 ቦምቦችን ከአማራ ክልል በማምጣት ለሌሎች ተጠርጣሪዎች መስጠቱን ተከትሎ ቦምቦቹ ሳይፈነዱ መያዛቸውን መርማሪ ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ገልጿል።ተጠርጣሪዎች አይተዋወቁም በማለት ጠበቆች በሰጡት አስተያየት ላይ መልስ የሰጠው ፖሊስ በህቡዕ በመደራጀት እንቅስቃሴ ተደርጓል ሲል ገልጿል።

በተለይም ጠበቆች ደንበኞቻችንን በሚመለከት ምንም ምስክር ቃል አልተቀበለም በማለት ያነሱትን መከራከሪያ ነጥብን በሚመለከት ፖሊስ ተጠርጣሪዎች በተጠረጠሩበት ወንጀል ከ20 በላይ የምስክር ቃል መቀበሉን የፎረንሲክ ማስረጃ መሰብሰቡን ፖሊስ ገልጾ መልስ ሰጥቷል።የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ መርምሮ ተጨማሪ ጊዜ መሰጠት አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን ለመወሰን በይደር ለዛሬ በያዘው ቀጠሮ መሰረት የተጠርጣሪዎቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የቀረውን የምርመራ ሥራውን አጠናቆ እንዲቀርብ የ 7 ቀን ጊዜ መፍቀዱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsTrue, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-19 16:12:39 አሐዱ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊዮን ብር አሳደገ

ይህ የተነገረዉ በዛሬው እለት አሀዱ ባንክ ከቻፓ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን እና ከ ትረስትድ ቴክ ጋር የስራ ስምምነት ፊርማ በተፈራረመበት መድረክ ነዉ፡፡ከተመሰረተ 10 ወራትን ያስቆጠረው አሃዱ ባንክ ከ 10 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች በ671 ሚሊዮን ብር አክሲዮን የተቋቋመ ሲሆን ደንበኞቹን በይበልጥ ለማገልገል የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን በማከናወን መሆኑን አስታዉቋል፡፡

አሀዱ ባንክ ካፒታሉን ወደ 5 ቢሊዮን ማሳደጉን ከባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰፊአለም ሊበን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡በአሁኑ ወቅት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ ቅርንጫፎች ብዛት 60 የደረሰ ሲሆን እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ ተጨማሪ 15 ቅርንጫፎችን እንደሚከፍት አስታዉቋል፡፡

አሐዱ ባንክ የደንበኞቹን ብዛት ከ 1 መቶ አርባ ሁለት ሺ በላይ ያደረሰ ሲሆን የተቀማጭ መጠኑ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሶልኛል ብሏል፡፡ባንኩ ከተለያዩ የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በጋራ በመሰራት በፋይናንስ ተደራሽነት እና የ2025 ዲጂታል ኢትዮጵያ መሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከቻፓ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ እና የትረስትድ ቴክ (aki pay) (fin-tech) ተቋማት ጋር ስምምነት ተፈራርምዋል።

ቻፓ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ለሃይማኖት ተቋማት ገንዘባቸውን መቆጣጠር እንዲችሉ ብሎም ደግሞ ማንኛውም ሰው ከሀገርም ሆነ ከውጭ ገንዘብ መላክ እና ካለበት ሆነ አስራት በኩራት ለማውጣት እንዲችል የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ማቅረቡን ጠቁሟል፡፡ ትረስትድ ቴክ ቤተክርቲያን ፈንድ ማግኘት እንድትችል የሚያደርግ ትረስት ፈንድ የተሰኘ ቴክኖሎጂን ያመጣ ሲሆን ማንኛውም ሰው በፈለገበት አይነት ማገዝ የሚችለበት ሁኔታ በቴክኖሎጂ እንደሚያመቻች ተገልጿል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 14:49:04
በፆግብጂ ወረዳ የጥራሪ ድልድይ በመፍረሱ ከ68 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የረድኤት ድጋፍ ማድረስ እንዳልተቻለ ተነገረ

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ዞን ብሄረሰብ አስተዳደር አስተዳደር ከሁለት ዓመታት በላይ ተፈናቅለው የነበሩ ከ34 ሺ በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ፆግብጂ ወረዳ እንዲመለሱ መደረጉን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡በአስተዳደሩ ካሉ 10 ወረዳዎች መካከል ነፃ በወጡ 3 ወረዳዎች ተፈናቃዮቹ እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን አገልግሎት በማይሰጡ የመንግስት ተቋማት እና በመኖሪያ ቤቶች እንዲያርፉ መደረጉ ተገልፆል፡፡

ተፈናቃዮች ከዋግ ኽምራ በሁለት ተሸከርካሪዎች ወደ ወረዳው እንዲመለሱ የተደረገ ቢሆንም ጥራሬ እተባለ የሚጠራው ድርድል በመፍረሱ በእንግልት ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡በመሆኑም በአፋጣኝ ድልድዩ ካልተጠገነ የተለያዩ ምግብ ነክ የሆኑ እና ሌሎች ግብቶችን ለማድረስ ከባድ ችግር መሆኑን እና ነዋሪዎችን በርረብ ዳግም ህይወታቸው እንዳያልፍ ስጋት መኖሩም ተገልፆል፡፡

በወረዳው አቅመ ደካሞች፣ ህፃናት እና ነብሰጡር እናቶች በመኖራቸው ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፎች ቢደረጉን ወደ ፆግብጂ ለማድረስ የጥራሪ ድልድይ በመፍረሱ ምንም አይነት ድጋፍ ማድረግ እንዳልተቻለ የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳድር የአደጋ መከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ቡድን መሪ/ወ/ሮ ዝናሽ ወርቅ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

የመንገዱ እና የፀጥታው ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ ድጋፍ የሚያደርጉ ግብረሰናይ ድርጅቶች ወደ ወረዳዉ ለመሄድ መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡በድልድዩ መፍረስ የተነሳ ሁለት ተሸከርካሪዎች በወንዝ መወሰዳቸዉን ወ/ሮ ዝናሽ ወርቅ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
581 viewsTrue, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 14:19:06
በሰሜናዊ ጣሊያን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 9 ሰዎች ሞቱ

በሰሜናዊ ጣሊያን ኤሚሊያ ሮማኛ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ ​​ዘጠኝ ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ከቤታቸው ተፈናቅለዋል።

የሲቪል ጥበቃ ሚኒስትር እንዳስታወቀዉ፤ አንዳንድ አካባቢዎች በ 36 ሰአታት ውስጥ ከአማካይ ዓመታዊ የዝናብ መጠን ግማሹን በማግኘታቸውን ገልጿል።

በዚህ ወንዞች ከተፋሰሳቸዉ እንዲያፈነግጡ በማድረግ ውሀ ከተሞችን እንዲያጥለቀልቅ ሆኗል ተብሏል። በተጨማሪም በሺዎች የሚቆጠር ሄክታር የእርሻ መሬቶችን አዉድሟል አደጋዉ።

የኤሚሊያ ሮማኛ ክልል ፕሬዝዳንት ስቴፋኖ ቦናቺኒ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም ታይተው የማያውቁ አስከፊ ክስተቶች እያጋጠሙን ነው ሲሉ ሁኔታውን ገልጸውታል።

የአከባቢው የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ 14 ሺህ ያህል ሰዎች አሁንም በተቻለ ፍጥነት ከአካባቢው መልቀቅ አለባቸው ብለዋል። በ37 ከተሞች የጎርፍ አደጋ መከሰቱን እና ወደ 120 የሚጠጉ የመሬት መንሸራተት አደጋዎች መመዝገቡን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

በቦሎኛ ከተማ አቅራቢያ ቢያንስ አንድ ድልድይ ፈርሷል ፣ አንዳንድ መንገዶች በጎርፍ ውሃ ተበላሽተዋል እና ብዙ የባቡር አገልግሎቶች ተቋርጠዋል።

የፊታችን እሁድ በግዛቲቱ ፎርሙላ ዋን (Formula1) የተሰኘ እዉቅ የመኪና ዉድድር ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞም ነበር።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
886 viewsBeⓒk, 11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 13:38:55
ከሱዳን ከ17 ሺህ በላይ ዜጎችን ማስወጣት መቻሉን አምባሳደር መለሰ ዓለም ተናገሩ

በሱዳን የተከሰተዉን ጦርነት ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጲያዉያን ዜጎች ለማስወጣት በኢትዮጲያ መንግስት በኩል ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የዜጎችን ደህንነት ለማረጋገጥ የነዋሪነት ፍቃድ ባይኖራቸውም ኢትዮጲያዊ መሆናቸዉን በማረጋገጥ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተመቻቸ እንደሚገኝ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለሰ ዓለም ለጋዜጠኞች በሰጡት ሳምንታዊ የስራ ማብራሪያ መግለጫ ላይ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሰምቷል፡፡

በዚህ ሂደት በአጠቃላይ እስካሁን በተሰራው ስራ 17 ሺህ 8 መቶ 85 ዜጎች ከሱዳን ወደ ሀገራቸው በኢትዮጵያ በኩል እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡ በመተማ በኩል 14 ሺህ 7 መቶ 86 ዜጎች በመደበኛ ኢምግሬሽን ወደ ሀገራቸው የገቡ ሲሆን 3700 ዜጎች ደግሞ በጥገኝነት መምጣታቸዉን ገልጸዋል፡፡ከተመለሱት ዜጎች ዉስጥ በቁጥር ውስን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የተቀሩት ኤርትራን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች እንደሚገኙበት አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ወገንተኝነትቷ ከሱዳን ህዝብ ጋር ነው በማለት የተናገሩት አምባሳደር መለሰ ዓለም ሱዳን የራስዋን ችግር በራስዋ አቅም መፍታት እንደሚኖርባትም ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
1.1K viewsTrue, 10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 13:30:49
#በመሀል_ከተማ_ካሳንቺስ

ቅድመ ክፍያ 50%
100% ለሚከፍል 10% ቅናሽ ያገኛል

ስቱዲዮ
     47 ካሬ
     52ካሬ
ባለ1መኝታ
  67 ካሬ
72 ካሬ
91 ካሬ
94ካሬ
ባለ2ምኝታ
125 ካሬ
130 ካሬ
168ካሬ
ባለ 3 መኝታ
202 ካሬ

ብሩክ ሠጠኝ
የገበያና ሽያጭ ባለሙያ
አያት አ.ማ

+251912898237
@Bruk23

Telegram join
@Bruk_Sales_consultant
@Bruk_Sales_consultant
1.1K viewsTrue, 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ