Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-18 12:59:01
በኢትዮጵያ በየቀኑ በአማካይ 27 እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸዉን እንደሚያጡ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ

በኢትዮጵያ በየእለቱ ከወሊድ ጋር በተያያዘ 27 እናቶች ህይወታቸዉ እንደሚያልፍ በጤና ሚኒስቴር የእናቶች ፣ህጻናትና ወጣቶች ጤና አገልግሎት የእናቶች ጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ብሩክ ሀይሉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል። በየአመቱም 10 ሺህ ገደማ እናቶች በ እርግዝና ወቅት በሚያጋጥሙ የተለያዩ የጤና እክሎች ህይወታቸዉ ያልፋል ብለዋል።

ለሚመዘገቡት የሞት ቁጥሮች ከወሊድ በኋላ የሚከሰት ከፍተኛ የሆነ ደም መፍሰስ ፣ በእርግዝና ግዜ የሚከሰት የደም ግፊትና ኢንፌክሽን ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸዉን አቶ ብሩክ ጠቁመዋል። ቅድመ እርግዝና እና ቅድመ ወሊድ ክትትል የሚያደርጉ እናቶች ቁጥር አናሳ መሆኑም ለሚሰተዉ ሞት ሌላኛዉ ምክኒያት እንደሆነ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ እ.ኤ.አ በ 2020 በተሰራ ጥናት በኢትዮጵያ ከ 100 ሺህ ወሊዶች ዉስጥ 2 መቶ 67 እናቶች በእኚሁ ምክኒያቶች ህይወታቸዉ ይቀጠፋል ብለዋል።

በአለም ጤና ድርጅት በአመቱ በተሰራ ሌላ ጥናት በአለማቀፍ ደረጃ በየእለቱ 8 መቶ እናቶች ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸዉ የሚያልፍ ሲሆን ይህም በየ 2 ደቂቃዉ የአንድ እናት ህይወት ያልፋል እንደማለትም ነዉ።

ከነዚህ ዉስጥ 87 በመቶ የሆነዉ ከሰሀራ በታች እና በደቡብ እስያ ባሉ ሀገራት ይመዘገባል ያሉ ሲሆን 95 በመቶ የሚሆነዉ ደግሞ በዝቅተኛ እና መካከለኛ ሀገራት ነዉ ብለዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
1.4K viewsBeⓒk, edited  09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 12:03:10
በሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድግዜ ሶስት ህፃናት ተወለዱ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሳፊያ መሀመድ አንድ ወንድ እና ሁለት ሴት በድምሩ ሶስት ህፃናትን በተደረገላት የህክምና ባለሙያዎች ድጋፍ በሰላም ተገላግላለች፡፡

የተወለዱት ሶስቱም ህፃናት እና እናታቸው በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ወ/ሮ ሳፊያን ያዋለዷት ሀኪሞች ዶክተር አለማየሁ እሸቱ እና ዶ/ር አብደላ አሊዪ ተናግረዋል፡፡

ወ/ሮ ሳፊያ መሀመድ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሕይወት ፋና ኮምርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ባገኙት የህክምና አገልግሎት መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

እናት ፤ በእርግዝና ወቅት አጠቃላይ የፅንስ ጤና ክትትል ማድረጋቸዉ በወሊድ ወቅት ችግር እንዳያጋጥማቸዉና ፈጥነዉ ወደ ሆስፒታል መጥተዉ ልጆቻቸዉን በሰላም እንዲገላገሉ ረድቷቸዋል መባሉን ብስራት ራዲዮ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ካገኘዉ መረጃ ተመልክቷል።

#ዳጉ_ጆርናል
1.6K viewsBeⓒk, 09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 11:32:18
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ ሐምሌ 19 - 30 ይሰጣል ተባለ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።

የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ ማሳሰቡን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

#ዳጉ_ጆርናል
1.7K viewsBeⓒk, edited  08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 10:15:51
አዲስ አበባ ከ 2መቶ ሜትር በላይ የሚረዝም ህንጻ ባለቤት ብትሆንም ፤ ያላት የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዋ ግን 74 ሜትር ብቻ ርዝማኔ አለዉ

የአዲስአበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በከተማዋ በሚያንዣብቡ አደጋዎች ፣ ከተማዋ ያላት ዝግጁነትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ከ2 ሺህ 500 በላይ ገጽ ያለዉን ጥናት በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ አስጠንቷል።

በጥናቱ ላይ እንደተመላከተዉ ፤ አዲስአበባ 10 በደረሱ የተፈጥሮ እና የሰዉሰራሽ አደጋዎች የተከበበች ነች ተብሏል። ከ 5 ሚሊዮን በላይ ይሆናሉ ተብለዉ የተገመቱ ነዋሪዎቿም በእሳት ፣ በትራፊክ ፣ በተበከሉ ኬሚካሎች ፣ በመሬት መንሸራተት ፡ በጨረር እና ጎርፍ እንዲሁም ከተለያዩ አደጋዎች ጋር ተጋፍጠዉ እንዲኖሩ ተገድደዋል ሲል ጥናቱ አመላክቷል።

እኚህን አደጋዎች ከመከላከል አኳያ ኮሚሽኑ ዘመናዊ መሳሪዎችን እያሟላ ቢሆንም ፤ አሁንም ግን ዉስንነቶች እንዳሉበት ብስራት ራዲዮ ከጥናቱ ተመልክቷል። አዲስአበባ በአሁኑ ሰዓት 209 ሜትር የሚረዝም እና ከ 5.3 ቢሊዮን ብር በላይ ፈሰስ የተደረገበት ህንጻ ባለቤት ብትሆንም ኮሚሽኑ ለእሳት አደጋ መከላከያ ያለዉ መሳሪያ ግን 74 ሜትር ብቻ የሚረዝም መሆኑ ተነግሯል።

የአዲስአበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፍሰሐ ጋረደዉ ለብስራት ራዲዮ እንደተናገሩት ፤ በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች በተሻለ ዘመናዊ እና አሰራሩም የሚደነቅ ቢሆንም ለአደጋ መከላከል የሚረዱ ሂሊኮፕተር እና ዘመናዊ ድሮኖች እንደሚያስፈልጉት ገልጸዋል።

በተጨማሪም አዲስአበባ ከሚያስፈልጓት 7 ሺህ በላይ የመንገድ ዳር የዉሃ ሳቢ ቧንቧዎች ዉስጥ አሁን አገልግሎት የሚሰጡት 3 መቶ 47 ብቻ መሆናቸዉን ጥናቱ አመላክቷል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
2.0K viewsTrue, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 09:32:01 ከቢሾፍቱ -ሰንዳፋ በኬ የሚወስደው የመንገድ ፕሮጀክት መጓተቱ ቅሬታ አስነሳ

ሰንዳፋ በኬ በምስራቅ ሸዋ ከሚገኙ አካባቢዎች የምርት ሃብታም በመባል ትታወቃለች።ሆኖም ግን ያላትን ምርት ለገበያ ለማቅረብ የመንገድ ግንባታ መጓተት ፈተኝ አድርጎታል፡፡ከሰንዳፋ በኬ ወደ ቢሾፍቱና አካባቢዉ ለመጓዝ አዲስ አበባን ማቋረጥ አማራጭ የሌለዉ አስገዳጅ ሆኗል፡፡

ሆኖም ግን በሰንዳፋ በኬ ጨፌ -ዶንሳ ቢሾፍቱ አጭር አቋራጭ መንገድ ቢኖርም የመንገድ ስራው እስካሁን ባለማለቁ ህዝቡም ሆነ የከተማው አስተዳደር ቅር መሰኘቱን የሰንዳፋ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ ተንኮሉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡ከቢሾፍቱ ጨፌ ዶንሳ ሰንዳ የሚወስደው ይሄ መንገድ 55 ኪሎሜትር ርዝማኔ ያለዉ ሲሆን እና በመንገዱ ችግር ሁለት ሰአት ለመጓዝ ያስገድዳል፡፡

ከግንባታዉ በፊት በነበረዉ መንገድ በቀን ከ 1000 በላይ ተሸከርካሪ ይጓጓዙበት እንደነበረ አስረድተዋል፡፡ፕሮጀክቱ ከ 900 ሚሊዮን ብር በላይ ተበጅቶለት ግንባታው የተጀምረ ቢሆንም በስራ ተቋራጩ በኩል የአቅም ውስንነት እንደገጠመው አንስተዋል፡፡ፕሮጀክቱ በአፋጣኝ ወደስራ እንዲገባ እና ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ መንግስት ከውል ውጭ በመመደብ ተጨማሪ በጀት እስከመልቀቅ መደረሱን ገልጸዋል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱ በ2016 ዓመት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያነሱት ከንቲባው የሃገሪቷን ከፍተኛዉን የምስራቅ ሸዋን የንግድ መስመር የሚያገናኝ በመሆኑ ሲጠናቀቅ በርካታ ጠቀሜታዎች ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ከዚህ ቀደም ከሰንዳፋ ወደ ቢሾፍቱና አካባቢዉ ለመሄድ ወደ አዲስ አበባ መጓዝ የግድ ያደረገዉን ሂደት የመንገዱ መጠናቀቅ ይህንን እንደሚያስቀረር ከንቲባ አቶ አለማየሁ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
2.1K viewsTrue, 06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 07:17:54 የሲዳማ ክልል 136 አመራሮችን በሙስና ከሠሠ!

የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ የክልሉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር እና የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የፋይናንስ ሓላፊዎችን ጨምሮ 136 አመራሮች እና ባለሞያዎች፣ በሙስና ወንጀል መከሠሣቸውን አስታወቀ።

ክሥ ከተመሠረተባቸው መካከል 72ቱ፣ ከአንድ እስከ 11 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ገልጿል።በሙስና እና ብልሹ አሠራር በሕግ እንዲጠየቁ የተለዩት 505 አመራሮች እና ባለሞያዎች ሲኾኑ፣ መዝብረዋል የተባሉትን 60 ሚሊዮን ብር ተመላሽ ማድረጉን፣ የሲዳማ ክልል ዋና ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ማቶ ማሩ አስታውቀዋል።

የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ማቶ ማሩ፣ ትላንት ሰኞ፣ ግንቦት 7 ቀን 2015 ዓ.ም. ማምሻውን በሰጡት መግለጫ፣ በክልሉ፣ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል በተደረገው እንቅስቃሴ ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።የሌብነት እና ምዝበራ ወንጀል የተፈጸመው፥ ለኢንቨስትመንት በሚል መሬት በመቀራመት፣ የፋይናንስ ሥርዐቱን በመጣስ፣ በመንግሥት ቤቶች አስተዳደር፣ በገቢ ግብር እና ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን በማዘጋጀት እንደኾነ፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አብራርተዋል፡፡

በሙስና ወንጀል እና በብልሹ አሠራር ለተጠየቁ ሁለት ደንበኞቻቸው ጥብቅና መቆማቸውን የተናገሩት አቶ ዓለማየሁ አየለ፣ አንዱ ደንበኛቸው ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ገልጸው፤ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ለተፈረደበት ሌላ ደንበኛቸው ይግባኝ መጠየቃቸውን ለአሜሪካ ድምፅ በስልክ ተናግረዋል።

የቁጥጥር እና ክትትል ሥራው፣ በክልሉ መንግሥት በተቋቋመው ኮሚቴ መከናወኑን የተናገሩት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ አቶ ማቶ ማሩ፣ በሒደቱ፣ ከሕዝብ 118 ጥቆማዎች መቀበላቸውንና የኅብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላ ሚና መጫወቱን አስረድተዋል።ከኅብረተሰቡ የተሰጡ ጥቆማዎች በምርመራ መለየታቸውን የጠቀሱት የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ መሬትን ጨምሮ የተመዘበረ የሕዝብ ሀብትን ለማስመለስ በተደረገ ጥረት ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል፡፡

በሐዋሳ፣ በይርጋለም፣ በለኩ እና ሆኮ ከተሞች፣ በሕገ ወጥ መንገድ ለግለሰቦች ተላልፎ የነበረ ከአምስት ሄክታር በላይ መሬት፣ ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጓል፤ ብለዋል።በሲዳማ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አንዳንዶቹ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በሚያወጧቸው መግለጫዎች፣ በክልሉ፣ ሙስና እና ብልሹ አሠራር ተንሰራፍቷል፤ ሲሉ፣ በገዥው ፓርቲ እና በመንግሥት ላይ ወቀሳ እና ትችት ያቀርባሉ።

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አቶ ማቶ፣ መረጃ እና ማስረጃ ቀርቦበት፣ በሕግ የማይጠየቅ አካል እንደማይኖር አረጋግጠዋል።በአሁኑ ወቅት በ193 መዝገቦች ክሣቸው እየታየ የሚገኙት የቀሪዎቹ 369 አመራሮች እና ባለሞያዎችም ጉዳይ፣ በፍርድ ሒደት ላይ መኾኑን ያስታወቁት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ፣ በሙስና እና ብልሹ አሠራር የተሳተፉ ባለሥልጣናትን በሕግ የመጠየቁ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል።

Via VoA
#ዳጉ_ጆርናል
2.5K viewsTrue, 04:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 21:57:18 አንድ ኩባያ ማር በላብኝ በማለት ወላጅ አባቱን ጭካኔ የገደለዉ ልጅ በእስራት ተቀጣ

በዳዉሮ ዞን ተከሳሽ አብርሃም አመኑ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለዉ ወላጅ አባቱን ጭካካኔ በተሞላበት ሁኔታ በስለት ወግቶ በመግደሉ እንደሆነ ተነግሯል።

ግለሰቡ አንድ ኩባያ ማር ያስቀመጠዉን ወላጅ አባቱ በመብላቱ ምክንያት አባት ልጄ አታዋርደኝ አባትህ ነኝ በማለት ልጅን ሲለምምን በያዘዉ ጦር ማሳሪያ አባቱን ግራ ደረቱ ላይ በሁለት እጁ ሲወጋዉ ጦሩ በጀርባዉ በመዉጣቱ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።


ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰዉና በህክምና ማስረጃ በማደራጀት የምርመራ መዝገቡን ለዞኑ ዐቃቤ ህግ ክስ ይመሰርታል።


በዚሁ መሠረት የዳዉሮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ አብረሃም አመኑ አርጋዶ በ25 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ማስተላለፉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsTrue, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 20:44:45 መንግስት የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደዉን ቀጥተኛ ብድር በመተካት የ 5 አመት ቦንድ አትሟል ተባለ

መንግስት በበጀት አመት መካከል ለሚያጋጥመዉ የገንዘብ እጥረት ከብሔራዊ ባንክ የሚወስደውን የቀጥታ ብድር በሚተካ መልኩ የ 5 አመት የመንግስት ቦንድ ማተሙን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በቦንዱም 25.6 ቢሊዮን ብር የበጀት መሸፈኛ ማግኘት መቻሉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። አዲስ በተጀመረዉ በዚህ መላ መንግስት የረጅም ግዜ ብድር ከሀገር ዉስጥ ገበያ እንዲያገኝ እንደሚያስችለዉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ከብሔራዊ ባንክ በቀጥተኛ ብድር የሚወሰደዉን ገንዘብ የሚያስቀርና የብድር ጫናን ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑን አክለዋል። በተመሳሳይ ዘንድሮ ለብሔራዊ ባንክ መከፈል የነበረበትን የብድር ገንዘብ ወደ ረጅም ግዜ የብድር ዋስትና በመቀየር በጀት ላይ የሚኖረዉን ጫና በመጠኑ መቀነስ መቻሉን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ሊከሰት የሚችለዉን የበጀት እጥረት ለመቀነስ እንዲረዳ በሚል በ 2015 አመት በጀት ተይዞላቸዉ ያልተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ወደ ሚቀጥለዉ አመት በማሸጋሸግ 18.2 ቢሊዮን ብር ወጪ ለመቀነስ እንደተቻለም አንስተዋል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 17:15:11
ካናዳ ኬንያውያንን ለሥራ ትቀበላለች በሚል የተሰራጨዉን መረጃ አስተባበለች

የካናዳ መንግስት ኬንያውያን ወደ ሀገሪቱ ለስራ እድል ሊሄዱ ይችላሉ የሚለውን ዘገባ አስተባብሏል።ይህ ሊባል የቻለዉ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አልፍሬድ ሙቱዋ ማክሰኞ ዕለት ኬንያውያን ካናዳ ውስጥ ሄደው መኖር ወይም መሥራት እንደሚችሉ ማሳወቃቸዉን ተከትሎ ነው።

በካናዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት ሚኒስትሩ ሙቱዋ ከካናዳ የኢሚግሬሽን፣ስደተኞች እና የዜግነት ሚኒስትር ሴን ፍሬዘር ጋር ተወያይተው በተለያዩ የስደት እድሎች ላይ መስማማታቸውን ተናግረዋል።ወደ ካናዳ መሄድ ለሚፈልጉ ሰዎች ሂደቱ ቀላል ቢሆንም ትጋት የሚጠይቅ ነው ብለዋል።

ልዩ ፕሮግራም ለኬንያ ስደተኞች በማዉጣት ካናዳ እንደምትቀበል የተሰራጨዉ መረጃ የሀሰት መሆኑ ተመላክቷል፡፡ይህ ውሸት ነው፣ እና የተጠቀሱት የኢሚግሬሽን ፕሮግራሞች የሉም ሲል የካናዳ የኢሚግሬሽን፣ስደተኞች እና የዜግነት ቢሮ ባወጣዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

የካናዳ የኢሚግሬሽን፣ስደተኞች እና የዜግነት ቢሮ ወደ ካናዳ እንዴት ሰዎች መሄድ እንደሚችሉ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ኬንያውያን የሀገሪቱን የኢሚግሬሽን ድረ-ገጽ መጎብኘት አለባቸው ብሏል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.6K viewsTrue, 14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 15:29:55
በአለፋ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ ከስምንት ወር በላይ በማስቆጠሩ ህብረተሰቡ ለችግር መዳረጉ ተነገረ

የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የውሃ አቅርቦት እጥረት ፈጥሯል

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በአለፋ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ ከስምንት ወር በላይ በመሆኑ ውሃን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ለማግኘት ነዋሪዎች መቸገራቸውን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ህብረተሰቡ በችግር ውስጥ እንደሚገኝ እና ችግሩ እንዲፈታ  በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ጥያቄ ተነስቶ እንደነበር የአለፋ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አ/ቶ ጌጡ አዳም ከብስራት ራዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።

በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል በሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም መጀመሪያ ችግሩ እንደሚቀረፍ ቃል የገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ተግባራዊ እንዳልሆነ ተነግሯል ። ውሃን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት የከተማ አስተዳደር  የውሃ ቦቲ በማዘጋጀት በየቀበሌው እየተዘዋወረ በጀሪካን አምስት ብር እያቀረበ ቢገኝም በቂ ባለመሆኑ በጋሪ ውሃ ከሚያቀርቡ ግለሰቦች በጀሪካን እስከ 30 ብር እንደሚሸጥ ተጠቁሟል።

በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ሃይልን ተጠቅመው ስራ የሚሰሩ ግለሰቦች  ለችግር መዳረጋቸው ተገልጿል ። ስለሆነም የሚመለከተው አካል ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው ተጠይቋል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ