2023-04-25 21:29:57
አጫጭር መረጃዎች የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል ግጭት ውስጥ የምትገኘው ሱዳን የሩሲያ የግል ወታደራዊ ኩባንያ የሆነውን የዋግነር ግሩፕ አገልግሎት የመጠቀም መብት እንዳላት ተናግረዋል። ላቭሮቭ ይህንን የተናገሩት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
በሱዳን ታጣቂ ሃይሎች እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች (አርኤስኤፍ) መካከል የ72 ሰአታት የተኩስ አቁም ስምምነት በዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት ቢደረስም በካርቱም መንትያ ከተማ ኦምዱርማን የከባድ መሳሪያ እና የተኩስ ድምጽ እየተሰማ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመላክተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሱዳን ባለው ጦርነት እስከ 270,000 የሚደርሱ ሰዎች ወደ ጎረቤት ሀገራቱ ደቡብ ሱዳን እና ቻድ ሊሰደዱ እንደሚችሉ ገለፀ። በቻድ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ 20,000 ሰዎች ወደ ሀገሪቱ መግባታቸውን እና እስከ 100,000 የሚደርሱ ስደተኞችን እንደሚጠብቅ ገልጿል።
በደቡብ ሱዳን የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ 45,000 ስደተኞች ከሱዳን ድንበር አቋርጠው መውጣታቸውንና 125,000 ደቡብ ሱዳናውያን በሁከቱ ምክንያት ሱዳንን ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ገልጿል።
እንግሊዝ የብሪታንያ ፓስፖርት የያዙ ሰዎችን ከሱዳን የማስወጣት ተልእኮ ጀምራለች፣ከዋና ከተማዋ ውጭ ወደሚገኝ አየር ማረፊያ የብሪታንያ ፓስፖርት የያዙ ዜጎች እንዲመጡ ጠይቃለች።
የግብፅ አል አህራም ጋዜጣ እንደዘገበው በሳውዲ አረቢያ በጦር ኃይሎች አዛዥ አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን እና በአርኤስኤፍ መሪ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ መካከል የእርቅ ውይይት ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ዘግቧል።
ከ10 ቀናት የከተሞች ጦርነት በኋላ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ በመደረጉ ፈረንሳይ 538 ሰዎችን ከሱዳን ማስወጣቷን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል። የፈረንሳይ ዜጎች ከጠቅላላው የተፈናቃዮች ቁጥር 209 ያህሉ መሆናቸውን ማክሮን በኤሊሴ ቤተ መንግስት የመከላከያ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
በሱዳን በምዕራብ ዳርፉር በጄኔናም ጦርነት መቀስቀሱን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመላክተዋል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, 18:29