Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 231

2022-05-12 13:32:38 በሶማሌ ክልል በባህላዊ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ግድያ ኢሰመኮ ኮነነ!

በሶማሌ ክልል ቦምባስ ከተማ በባህላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፀጥታ ኃይሎችና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች የ11 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮነነ።በሶማሌ ክልል ከሚገኙት የሶማሌ ጎሳዎች መካከል የሆኑት የአኪሾ ጎሳ አባላት መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የጎሳ መሪያቸውን ለመምረጥ በተሰበሰቡበት ዕለት ከግድያ በተጨማሪ 33 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ማረጋገጡን ኢሰመኮ ዛሬ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም. ባወጣው የምርመራ ሪፖርቱ አስታውቋል።

ኢሰመኮ በስፍራው ተገኝቶ ባደረገውም ምርመራ የክልሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ለሞትና ለአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል ብሏል።ኢሰመኮ በሁለቱ ቀናት ስለተፈጸሙ ግድያዎችና የአካል ጉዳቶች የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ በቦታው በመገኘት የዓይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የአገር ሽማግሌዎችን ማናገሩን አስታውቋል።

በተጨማሪም ከሆስፒታል ምንጮች መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም ፈቃደኛ የሆኑ የክልሉ ኃላፊዎችን በማነጋገር የምርመራውን ሪፖርት አጠናቅሯል።በተጨማሪም ቦምባስ ከተማ የሚገኝ የጥቃቱ ሰለባዎች የተቀበሩበትን መካነ መቃብር መጎብኘቱን ገልጾ በዚህም በመጀመሪያው ቀን የተገደሉ ሰዎች የተቀበሩበትን የጅምላ መቃብር እንዲሁም በሁለተኛው ቀን የተገደለች ሴት ተቀብራበታለች የተባለ መካነ መቃብር መመልከቱንም በዚሁ የምርመራ ሪፖርቱ አካቷል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, edited  10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 12:10:50
የደቡብ አፍሪካን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ እስካሁን 48 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተባለ

የደቡብ አፍሪካ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ባለፈው ወር በኩዋዙሉ-ናታል የደረሰዉን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ እስካሁን ድረስ 48 ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ በአደጋዉ የሟቾች ቁጥር 445 እንደደረሰም መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡

የአደጋ አስተዳደር ቡድን አባላትን ጨምሮ ፖሊስ እና የደቡብ አፍሪካ ጦር አሁንም ጠፉ የተባሉ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋዉን ቀጥሏል፡፡ነገር ግን የጠፉ ሰዎች በርካታ ቤተሰቦች የሚወዷቸውን በህይወት ዳግም የማግኘት ተስፋቸው እየቀነሰ ይገኛል፡፡ጎርፉ በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 10 ዓመታት ከደረሱ የተፈጥሮ አደጋ ሁሉ የከፋ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በጎርፉ የደረሰዉ የጉዳቱ መጠን አሁንም እየተገመገመ የሚገኝ ሲሆን በመነሻ በተሰጠ ግምት መሰረት ከ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ሀብት ወድሟል፡፡በዝናቡ ዋና ዋና መሰረተ ልማቶች በመጎዳታቸው በርካታ ነዋሪዎች ለሳምንታት የውሃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, edited  09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 12:05:48 የትግራይ ህዝብ “ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል” እንዲዘጋጅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥሪ አቀረቡ!

የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ከማዕከላዊው መንግስት ጋር ችግሮችን በዲፕሎማሲ ለመፍታት ሲደረግ የነበረው ጥረት “ባለመሳካቱና የሰላም መንገድ በመዘጋቱ የትግራይን ሕዝብ ነፃነት ለማረጋገጥ” የክልሉ ህዝብ እንዲዘጋጅ ጥሪ አቀረቡ።

ደብረፅዮን በመቀሌ ሌሎች የሕወሃት አመራሮች ደግሞ በተለያዩ የትግራይ ዞኖች ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የትግራይ ህዝብ አሁን ያለበት የከፋ ስቃይ እንዲቀለበስና የትግራይ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲረጋገጥ ለማድረግ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

“ኹሉም የፖለቲካ ችግር በሰላምና በዲፕሎማሲ እንደማይፈታ ብናውቅም አሁን የገባንበት ጦርነት ከመጀመሩ አስቀድመን እንዲሁም በጦርነቱ ወቅት ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተናል” ብለዋል ደብረፅዮን በመቀሌ ከነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ።

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸማጋይነት ጊዚያዊ ሥምምነት ተደርጎ ወደ ክልሉ እህል መድሀኒትና ሌሎች ድጋፎች እንዲገቡ ጥረት ብናደርግም እስከ አሁን ድረስ የተገኘው ድጋፍ ችግሩን ለማቃለል በቂ አይደለም ብለዋል።

መላክ ያለበትን መልዕክት ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ባለን የመገናኛ መንገድ አድርሰናል ያሉት ደብረፅዮን የሚመለከታቸው ያሏቸውን አካላት አልዘረዘሩም።

መንግስት የተኩስ አቁም በሚል ሽፋን የመሳሪያና የሰራዊት ማሰባሰብ ስራ ላይ ነው ሲሉ የከሰሱት ርዕሰ መስተዳድሩ የትግራይ ሕዝብ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚረጋገጠው የኀይል የበላይነትን በመያዝ ብቻ መሆኑን ለተሰብሳቢዎች አስረድተዋል።

ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር(ሞንጀሪኖ)፣ አለም ገብረሐዋድና ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ነዋሪዎችን ያወያዩ ሲሆን ሕዝቡ ለመጨረሻው ምዕራፍ ትግል እንዲዘጋጅ መጠየቃቸውን ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን ባመቻችም ሕወሃት ራሱ ዕርዳታ በማስተጓጎልና ተጎራባች ክልሎችን በመውረር እንቅፋት መፍጠሩን ይናገራል። የትግራይ አማፅያን በቅርቡ ይዘውት ከነበረው የአፋር ክልል ሙሉ በሙሉ ለቀው መውጣታቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት የምዕራብ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊትን በቦታው ተገኝተው ያበረታቱ ሲሆን ወታደራዊ ብቃቱን የሚያሳይ ትርዒትም መመልከታቸው ይታወሳል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, edited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 10:12:56
ጎግል ትርጉም ኦሮምኛና ትግረኛ ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት ቋንቋዎችን ማካተቱን አስታወቀ

አማርኛ፣ ሃውሳን እና ሶማሊኛ ጨምሮ ሌሎች በርካታ የአፍሪካ ቋንቋዎች በጎግል ትርጉም ከዚህ በፊት መቅረባቸዉ ይታውሳል፡፡የጎግል ትርጉም ተመራማሪ የሆኑት አይዛክ ካስዌል እንደተናገሩት "በጎግል ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ያለንን ሽፋንን የማስፋት ስራ ነው ሲሉ " ገልጸዋል።

ጎግል ትርጉም ከተካተቱት መካከል ኦሮምኛና ትግረኛ ቋንቋዎችን ያሉበት ሲሆን በተጨማሪም በጋና እና ቶጎ የሚነገረዉ ኢዌ፣ ክሪዮ በሴራሊዮን ከፍተኛ የቋንቋዉ ተጠቃሚዎች ያሉበት እና ሊንጋላ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን ጨምሮ በማዕከላዊ አፍሪካ ሰፊ ክፍሎች የሚነገረ ቋንቋ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም በኡጋንዳ እና ሩዋንዳ የሚገኘዉ የሉጋንዳ ቋንቋ ፣ በጎግል ትርጉም ከተካተቱት ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው ፡፡

በስምኦን ደረጄ #ዳጉ_ጆርናል
3.3K viewsTrue, edited  07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 22:54:50
ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1005 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በዛሬዉ እለት ከሳውዲ አረቢያ ሪያድ በተደረጉ ሦስት በረራዎች 1 ሺህ አምስት ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከተመላሾች መካከል 635 ወንዶች ፣ 325 ሴቶች እና 45 ህፃናት ናቸው ሲልም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት አስታውቋል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsBeⓒky, edited  19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:55:54 160 ሺ ብር ጉቦ ስትቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘችው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ባለሙያ ክስ ተመሰረተባት።

ዐቃቤ ህግ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ባለሙያ ሆና ስትሰራ 160 ሺ ብር ጉቦ በመቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል በፈፀመች ግለሰብ ላይ ክስ መስርቷል::

ወ/ሮ ሃብታምነሽ ሊሞና የተባለችው ተከሳሽ የሙስና ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 10 (2) ላይ የተመለከተውን በመተላለፏ ነው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባት።

ተከሳሿ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት የሰነድ አጣሪ ባለሞያ ሆና ስትሰራ በስራ ኃላፊነቷ ማድረግ የማይገባትን ለማድረግ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 በተበዳይ ስም ተመዝግቦ ይገኝ የነበረ ይዞታ በሽያጭ ወደ 4ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር በመተላለፉ የሥም ዝውውር እንዲደረግ ለጽ/ቤቱ በቀረበው የአገልግሎት ጥያቄ መሰረት አስፈላጊ መስፈርቶች ሁሉ ተሟልተው እያለ ሚያዝያ 03 ቀን 2014 ዓ.ም የሥም ዝውውር ከተፈጸመ በኋላ ገዢዎችን በመወከል ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው 1ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክርን “ካርታው ተሰርቷል ገንዘብ ካላመጣህ ግን ወጪ አድርገን አንሰጥህም” በማለት 160,000 (አንድ መቶ ስልሳ ሺ) ብር ጉቦ በመጠየቅ ሚያዝያ 10 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 7፡30 በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ላፍቶ ቪው ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ1ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክር ስም የተቆረጠ ቼክ 160,000 (የአንድ መቶ ስልሳ ሺ ) ብር ካሽ የተጻፈበት መኪና ዉስጥ ሆና ስትቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዛለች።በመሆኑ በፈፀመችው ጉቦ መቀበል ከባድ የሙስና ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባታል ፡፡

ተከሳሿ ዛሬ ግንቦት 03/2014 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ሙስና ወንጀል ችሎት ቀርባ የክስ ቻርጅ አንዲደርሳት ከተደረገ በኋላ ክሱ በንባብ ተሰምቷል።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ በክሱ ላይ የምታቀርበው የክስ መቃወሚያ ካለ ለመጠባበቅ ለግንቦት 05/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል ።

[ፍትሕ ሚኒስቴር]
#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsTrue, edited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 20:40:10 የእሮብ ምሽት አጫጭር መረጃዎች የሩሲያ-ዩክሬንን ቀውስ በተመለከተ

ዩክሬን የኔቶ ጥምረት አባል ብትሆን ኖሮ ከሩሲያ ጋር የሚደረገውን ጦርነት መከላከል ይቻል ነበር ሲሉ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል። "ዩክሬን ከጦርነቱ በፊት የኔቶ አካል ብትሆን ኖሮ ጦርነት አይኖርም ነበር" ሲሉ በፓሪስ የፖለቲካ ጥናት ተቋም ለተገኙ ተማሪዎች በቪዲዮ ሊንክ ተናግረዋል።

የአውሮፓ ህብረት ሀገራት በሩሲያ ኢነርጂ ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ በሚሞክሩበት በዚህ ወቅት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከምዕራባውያን ሀገራት ውጭ የእኛን ነዳጅ እና ጋዝ የሚሸምቱ በቂ ገዢዎች አሉን ሲሉ ተናግረዋል።

የሩስያ ሚዲያዎች እንደዘገቡት በዩክሬን የኬርሰን ክልሉ ነዋሪዎች የሩሲያ አካል መሆን እንደሚፈልጉ ለፕሬዝዳንት ፑቲንን ጥያቄ ማቅረባቸውን አስነብበዋል። ነገር ግን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ይህ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ሳይሆን ህዝቡ የሚወስነው ነው ብለዋል።

ሩሲያ ፊንላንድን እና ስዊድን ኔቶን እንዳይቀላቀሉ አስጠንቅቃለች፤ ይህንን እርምጃ የሚወስዱ ከሆነ በአውሮፓ መረጋጋት እንደማይፈጥር ሞስኮ ተናግራለች።

የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን እና የስዊድን አቻቸው ማግዳሌና አንደርሰን ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር ያለው ግንኙነት በፍፁም ሊስተካከል እንደማይችል ተናግረዋል።

ዩክሬን የሩስያ የተፈጥሮ ጋዝን ወደ ምዕራብ አውሮጳ ሀገራት ወደሚገኙ ቤቶች እና ኢንዱስትሪዎች የሚያጓጉዙ የቧንቧ መስመሮችን ዘግታለች።

የመጀመሪያው የሩሲያ ወታደር በጦር ወንጀል በዩክሬን ፍርድ ቤት ቀረበ። የዩክሬን ጠቅላይ አቃቤ ህግ አንድ የሩስያ ወታደር ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በዩክሬን የጦር ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ለፍርድ መቅረቡን አስታውቋል።

በፖላንድ ዋርሶ የሩሲያ አምባሳደር ቀይ ቀለም በመቀባት በተቃዋሚ ሰልፈኞች የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን ተከትሎ ሩሲያ ፖላንድ ይፋዊ ይቅርታ ትጠይቀኝ ስትል ተናግራለች።ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ወደፊትም ሊደርስ የሚችለው የአፀፋ ምላሽ የከፋ ይሆናል ስትል ሞስኮ ዝታለች።

የሩሲያ የስለላ ኤጀንሲ ኃላፊ ሰርጌይ ናሪሽኪን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት የናዚ ፕሮፓጋንዳ ማሽን ከነበረው ጆሴፍ ጎብልስ ጋር በማነፃፀር ፤ ዋሽንግተን ፀረ-ሩሲያ የመልእክት ዘመቻን በማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል በማቀላጠፍ ተጠምዳለች ሲሉ ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከስዊድን ጋር የጸጥታ ስምምነት ተፈራርመዋል።አንዳቸው ላይ ጥቃት ከደረሰ በሁለቱም ሀገራት ዘንድ በተደረሰው ስምምነት መሰረትየጋራ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsTrue, 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 20:34:24
በጦርነት እና እገዳ ከሌላዉ የኢትዮጵያ ክፍል በተገለለችዉ ትግራይ አለቅጥ የናረዉ የምግብ ሸቀጦች ዋጋ የሕዝቡን ኑሮ እያቃወሰዉ መሆኑ ተዘገበ።

ዶይቸ ቨለ እንደዘገበዉ መቀሌ ዉስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ 5 ብር ይሸጥ የነበረዉ 50 ግራም ዳቦ (ፉርኖ) ሰሞኑን 8 ብር ገብቷል።የፉርኖ ዱቄት፣የጤፍ፣ የበርበሬና የመሰል የምግብ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ ሲጨምር ማኮሮኒና ፓስታን የመሳሰሉ የፋብሪካ ምርቶችን ገበያ ላይ ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ።የዚያኑ ያክል እዚያዉ ትግራይ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርትና ቲማቲም የመሳሰሉ ማጣፈጫዎች ዋጋ ብዙ ለዉጥ አላሳየም።የከብትና የስጋ ዋጋ ግን ቀንሷል።

DW
#ዳጉ_ጆርናል
3.5K viewsTrue, edited  17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 18:28:46
ከባድ እና ቀላል የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 106 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

ከባድ የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ቀላል የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ 82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና 147 ካምፓሶቻቸው ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ በ24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶች ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ መወሰዱ ተመላክቷል፡፡
በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን÷ በቀጣይ የተገኘባቸውን ክፍተቶች በማስተካከል በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ የተሰጣቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ የተወሰደባቸው 24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

#ዳጉ_ጆርናል
3.6K viewsTrue, 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 18:14:27 በደብረ ብርሃን ከተማ የ20 ኢንቨስተሮች መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደረገ

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢትዮጲያ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በሆነችው ደብረ ብርሃን ከተማ ከ350 በላይ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን በግንባታ እና በቅድመ ግንባታ ላይ ያሉ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገቡ ከ70 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደሚችሉ ተገልፆል፡፡እስካሁን በከተማዋ ባለው ኢንዱስትሪ ከ20 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር መቻሉን ተነግሯል፡፡

ከ80 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ መምጣታቸው ታዉቋል፡፡ለነዚህ ኢንቨስተሮች የተለያዩ የሚያስፈለጋቸው አቅርቦት ተመቻችተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ተገልፆል፡፡ሆኖም ግን በባለሀብቱ ንብረት በሆነ በሊዝ ውል መሰረት ቅድመ ግባንታ ፣ግንባታ እና ማምረት መቼ እንዳለባቸው ገደብ የሚሰጣቸው ሲሆን በዛ መሰረት መንቀሳቀስ ያልቻሉ ከሆነ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል።በተጨማሪም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ተግባራዊ ባላደረጉት ላይ ደግሞ የተሰጣቸውን መሬት እንዲመለስ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡
እስካሁንም በከተማው ለ50 ለሚሆኑት ኢንቨስተሮች ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን 20 የሚሆኑት ደግሞ የተሰጣቸዉ መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲገባ ተደርጓል ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ብርሃን ገ/ህይወት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት 10 ወራት 330 የኢንቨስትመንት ፍቃድ ለመስጠት ታቅዶ ለ270 ለሚሆኑት መስጠት መቻሉ ተገልፆል፡፡በደብረብርሃን ከተማ ሰፊ የሆነ የኢንቨስትመንት አማራጭ ያለ እንደመሆኖ ማንኛውም ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በሩ ክፍት መሆኑን አቶ ብርሃን ገ/ህይወት ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, edited  15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ