Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 232

2022-05-11 16:11:05
የቀድሞ ብራዚላዊ እግር ኳስ ተጫዋች ሮናልዲኒሆ ላይ ክስ መስርቶ የነበረው እውቅ አቃቤ ህግ በኮሎምቢያ የጫጉላ ሽርሽር ላይ እያለ ተገደለ

በፓራጓይ የተደራጁ ወንጀሎችን በመታገል የሚታወቀው አቃቤ ህግ በኮሎምቢያ የጫጉላ ሽርሽር ላይ በነበረበት ወቅት በጥይት ተመቶ መገደሉ ተሰምቷል። ማርሴሎ ፔቺ በሁለት ታጣቂዎች የተገደለው ባሩ በተሰኘች የቱሪስት ደሴት የባህር ዳርቻ ላይ ነበር።

ግድያው ከመፈፀሙ ከሰዓታት በፊት የአቃቤ ህጉ ፔቺ ባለቤት ነፍሰጡር መሆኗን በኢንስታግራም ገጿ ላይ አስታውቃ ነበር። የፓራጓይ ፕሬዝዳንት ማሪዮ አብዶ ቤኒቴዝ ድርጊቱን “የፈሪዎች ተግባር ግድያ ነው” ሲሉ ገልፀውታል።

የአቃቢ ህጉ ባለቤት የሆነችው ጋዜጠኛ ክላውዲያ አጉይሌራ ባሏ ላይ ጥይት ከመተኮሱ በፊት ሁለት ሰዎች ወደ እነርሱ መቅረባቸውን ተናግራለች። ምንም አይነት ዛቻ አስቀድሞ እንዳልደረሰበት ግን አስታውቃለች። ግድያውን የፈፀሙት ሁለት ሰዎች በትናንሽ ጀልባ መምጣታቸውን ብትገልፅን በደንብ ግን ማየት አልቻልኩም ብላለች።

ይህው አቃቢ ህግ እ.ኤ.አ. በ2020 ሀሰተኛ የፓራጓይ ፓስፖርት ይዞ ወደ ፓራጓይ ሊገባ ሲል በተያዘው የቀድሞ ብራዚላዊ እግር ኳስ ተጫዋች ሮናልዲኒሆ ላይ ክስ መስርቶ እንደነበር ይታወሳል።

የኮሎምቢያ ፖሊስ ኃላፊ እና ከፓራጓይ የመጡ መርማሪዎች ግድያው ወደተፈፀመበት ቦታ ተጉዘዋል። የኮሎምቢያ ብሄራዊ ፖሊስ አዛዥ ጄኔራል ሆርጌ ሉዊስ ቫርጋስ እንዳሉት የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት ለምርመራው እገዛ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.5K viewsTrue, 13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 15:35:55 ኢትዮጵያ እና ቱርክ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት እና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ ተስማሙ

በኢትዮጵያ መንግስት እና በቱርክ ሪፐብሊክ መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት እና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የጋራ የሕግ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ ሥምምነቶች ተፈርመዋል፡፡በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፍትህ ሚኒስቴር የመንግስት ሕግና ፍትህ አገልግሎት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደዉ የተመራ የልዑካን ቡድን አንካራ ቱርክ የገባ ሲሆን፤ የልዑካን ቡድኑ በቱርክ የፍትህ ሚኒስቴር በመገኘት በኹለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡

በዉይይቱም የቱርክ ሪፐብሊክ መንግስት የፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ያኩፕ ሞጉል በቱርክና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መሆኑ እና በፍትህ እና በወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚደረጉ ትብብሮች አስፈላጊና ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸዉ መሆኑን ገልፀዋል። አክለውም በኹለቱ አገራት መካከል የተለያዩ ትብብሮች ሲደረጉ የቆየ ቢሆንም፤ በዚህ ደረጃ የፍትህ ትብብሮች ሰነድ መፈረማቸዉ ግንኙነቱን የበለጠ ሕጋዊ መሰረት የሚሰጠዉ መሆኑን ጠቅሰዉ በኹለቱ አገራት የሚፈለጉ ወንጀለኞችም በማንኛዉም ጊዜ በፍጥነት ተላልፈው መሰጠት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

አለምአንተ አግደዉ በበኩላቸዉ፤ ኢትዮጵያ ከብዙ አገራት ጋር በወንጀል ጉዳዮች ላይ በትብብር እንደምትሰራ፣ ከቱርክ መንግስት ጋር በወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚደረገው የጋራ ሥምምነትም በኹለቱ አገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግረዉ መሆኑን ተናግረዋል።በተጨማሪም ቱርክ በተለያዩ መንገዶች የኢትዮጵያ አጋር መሆኗን ማሳየቷን ገልፀው፤ በአቅም ግንባታ ዙሪያ ከቱርክ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ኢትዮጵያ ዝግጁ መሆኗን፤ ቱርክ በሽብርተኛ ቡድኖች የደረሰባትን አሳዛኝ ጉዳቶች ኢትዮጵያ እንደምትገነዘብና በዚህም ከቱርክ መንግስትና ህዝብ ጎን እንደምትቆም፣ አገራችን ሽብርተኞችን እንደምታወግዝና ሽብርተኝነት እንዳይስፋፋ ጠንክራ እንደምትሰራ ገልጸዋል፡፡

በኹለቱ ወገኖች መካከል ከላይ በተጠቀሱት ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ በቀጣይ በጋራ በቅርበት በመስራት ትብብሩን በማጠናከር ረገድ ትኩረት እንደሚሰጥ የኹለቱም አገራት ተወካዮች መግለፃቸውን የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በመቀጠልም በኹለቱ አገራት መካከል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ ለመስጠት እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ ኹለት ሥምምነቶች በፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አለምአንተ አግደዉ እና በቱርክ ፍትህ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ሚስተር ያኩፕ ሞጉል አማካኝነት ተፈርሟል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, edited  12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 15:05:40 ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ ባለመኖሩ የአቅሜን ያህል እየሰራሁ አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ልብ ሕሙማን ህፃናት መርጃ ማእከል አስታወቀ

ከ30 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ ባለመኖሩ የአቅሙን ያህል እየሰራ እንዳልሆነ አስታዉቋል፡፡ከሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ በቀን ከ10 አስከ 12 የሚሆኑ ህጻናት ወደ ማዕከል የሚመጡ ሲሆን ቋሚ የገቢ ምንጭ አለመኖሩ በስራዉ ላይ እንቅፋት እንደሆነበት ገልጿል፡፡

የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕክል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ናሆም ስንታየው ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት የልብ ቀዶ ህክምና ዓለም ላይ ወድ የሚባል የህክምና አይነት ሲሆን ይህንንም አገልግሎት ማዕከሉ በነጻ እየሰጠ መሆኑን አንስተዋል፡፡ለአንድ ህጻን የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ እስከ መቶ ሺ ብር የሚያስወጣ መሆኑን ገልጻዋል፡፡

በተጨማሪም 80 በመቶ የሚሆነው ለቀዶ ህክምና የሚያስፈላጉ ቁሳቁሶች አላቂ እቃዎች ከውጪ ሀገራት የሚመጡ እንደመሆናቸው በቀላሉ ለመግዛት እና ለማስመጣት መቸገሩን ሌላኛው ህክምናውን በሚፈለግ መልኩ ለመስጠት አስቸጋሪ ያደረገው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት በተደረገ ጥናት ህክምናዉን ለማግኘት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ህጻናት ከ7ሺ በላይ ሲሆን እነዚህን ህጻናት ለመታደግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉ ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ድጋፍ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው 6710 ላይ ከአንድ ብር አንስቶ እስከ መቶ ብር ድረስ እገዛ ማድረግ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

በትግስት ላቀዉ
#ዳጉ_ጆርናል
3.4K viewsTrue, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ