Get Mystery Box with random crypto!

የደቡብ አፍሪካን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ እስካሁን 48 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተባለ የደቡብ | ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የደቡብ አፍሪካን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ እስካሁን 48 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም ተባለ

የደቡብ አፍሪካ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ባለፈው ወር በኩዋዙሉ-ናታል የደረሰዉን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ እስካሁን ድረስ 48 ሰዎች የደረሱበት እንዳልታወቀ አረጋግጠዋል። በአጠቃላይ በአደጋዉ የሟቾች ቁጥር 445 እንደደረሰም መንግስት ይፋ አድርጓል፡፡

የአደጋ አስተዳደር ቡድን አባላትን ጨምሮ ፖሊስ እና የደቡብ አፍሪካ ጦር አሁንም ጠፉ የተባሉ ሰዎችን ለማግኘት ፍለጋዉን ቀጥሏል፡፡ነገር ግን የጠፉ ሰዎች በርካታ ቤተሰቦች የሚወዷቸውን በህይወት ዳግም የማግኘት ተስፋቸው እየቀነሰ ይገኛል፡፡ጎርፉ በደቡብ አፍሪካ ባለፉት 10 ዓመታት ከደረሱ የተፈጥሮ አደጋ ሁሉ የከፋ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

በጎርፉ የደረሰዉ የጉዳቱ መጠን አሁንም እየተገመገመ የሚገኝ ሲሆን በመነሻ በተሰጠ ግምት መሰረት ከ1.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ሀብት ወድሟል፡፡በዝናቡ ዋና ዋና መሰረተ ልማቶች በመጎዳታቸው በርካታ ነዋሪዎች ለሳምንታት የውሃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል