Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-17 14:41:27
ከነገ ጀምሮ በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የሚመክር ኮንፈረንስ ሊካሄድ ነዉ

ከነገ ሐሙስ ግንቦት 10/2015 ዓ/ም ጀምሮ በአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታዎች እና የቀጣይ መፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ የሚመከር ኮንፈረንስ ሊካሄድ መሆኑን የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታዉቋል፡፡

የፓርቲው የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው አወቀ ኮንፈረንሱን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ፈተናዎችን ተሻግረን የኢትዮጵያን ልዕልና እናበስራለን" በሚል መሪ ቃል በክልሉ የሚገኙ የከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ይካሄዳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ እና የተጀማመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ማሳደግ ዓላማ ያደረገ ኮንፈረንስ መሆኑን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ትግል ይደረጋል ያሉት ኃላፊው ኮንፈረንሱ የአማራ ክልልን ወደ ፊት ለማስፈንጠር ግብ አስቀምጦ ይመክራል ብለዋል፡፡

ኮንፈረንሱ ለመላው የፓርቲው አመራር እና አባል በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያለመ መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ጋሻው አመራሩ ጠንካራ የፖለቲካ እሳቤና የተስተካከለ የፖለቲካ ትግል ማድረግ ይጠበቅታልም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ከ1 ሺህ 400 በላይ በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉ ሲሆን ይህንኑ የሚመጥን በቂ ቅድመ ዝግጅት መደረጉም ተሰምቷል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsBeⓒk, edited  11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:33:46
የደቡብ አፍሪካ የ10 ዓመት አብዛኛው ልጆች ለማንበብ እንደሚቸግራቻው ተነገረ

ከ10 የደቡብ አፍሪካ ተማሪዎች መካከል ስምንቱ እድሜያቸው 10 ዓመት ቢደርስም በደንብ ለማንበብ ይቸገራሉ ሲል አንድ  አለም አቀፍ ጥናት አመልክቷል። አለም አቀፉ የንባብና መጻፍ እድገት ተቋም (PIRLS) 2021 ዓመት በ43 ሀገራት ውስጥ በሚገኙ በአራተኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድ ያለውን የንባብ ክህሎት ገምግሟል።

ደቡብ አፍሪካ በዚሁ ጥናት መሰረት ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በደቡብ አፍሪካ ከተገመገሙት ህፃናት 81 በመቶ ያህሉ በሀገሪቱ ለትምህርት ከሚሰጡ የአፍ መፍቻ 11 ይፋዊ የስራ ቋንቋዎች የሚጠቀሙት በሙሉ ማንበብ እንደማይችሉ አሳይቷል።

እንደ አለመታደል ሆኖ በፈተና ውጤቶች መሰረት በማንበብና መጻፍ የሚያስቆጭ ዝቅተኛ ውጤት አሳይተዋል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሯ አንጂ ሞትሼክጋን ተናግረዋል። ትምህርት ቤቶች ለአንድ ዓመት ያህል በኮቪድ ወረርሽኝ መዘጋታቸው ትልቅ ፈተና እንደነበር ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsTrue, 10:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:54:41 እስራኤል በጋዛ ሰርጥ 30 ፍልስጤማውያንን ገደለች

እስራኤል ከማክሰኞ ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ ላይ እየፈጸመች ባለዉ የአየር ጥቃት 30 ፍልስጤማውያንን ሲገደሉ ከ90 በላይ መቁሰላቸዉን የፍልስጤም የጤና ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡ከሟቾቹቹ መካከል ስድስት ህጻናት እና ሶስት ሴቶች እንዲሁም የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን መሪ እና ምክትላቸው ይገኙበታል።

በጋዛ የሚገኙ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን አንጃዎች በበቀል እርምጃ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሳቸውን ቀጥለውበታል፣ በትላንትናዉ ዕለት አንድ ሰው ከእስራኤል ወገን ተገድሏል፡፡የግብፅን የሽምግልና ጥረት ተከትሎ ሁለቱም ወገኖች ከነሐሴ ወር ጀምሮ የከፋውን ትኩሳት ለማብረድ ዝግጁ የማይመስሉ ሲሆን ዉጥረቱ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የአየር ኃይሉን የጦር ሰፈር በጎበኙበት ወቅት በቪዲዮ የተቀረጸ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት “እኛ በዘመቻ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነን” ብለዋል ።" እኛን ሊጎዳ የሚመጣ ሁሉ ደሙ ከንቱ ይሆናል ሲሉ አክለዋል።የአሊ ጋሊ እና አህመድ አቡ ዳቃ ሞት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ከማክሰኞ ወዲህ በጀመረችዉ ጥቃት የተገደሉት የፍልስጥኤል ታጣቂ ቡድን አባላት(PIJ) ከፍተኛ ባለስልጣናትን ቁጥር ወደ አምስት አድርሶታል።

ግብፅ በሁለቱ ወገኖች መካከል የእርቅ ስምምነት እንዲደረስ እየሞከረች ቢሆንም እስካሁን ግን ጥረቷ ከንቱ ሆኖ ቆይቷል።የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ግብፅ ሁለቱን ወገኖች ለማረጋጋት እና የፖለቲካ ሂደቱን ለማስቀጠል የምታደርገው ጥረት እስካሁን ፍሬ አላፈራም" ብለዋል።

የፍልስጥኤም ታጣቂ ቡድን የተኩስ አቁም እንዲደረስ እስራኤል ከእንግዲህ መሪዎቻቸውን ላለመግደል ቃል መግባት አለባት ብሏል። ይህንን ግን እስራኤል እንደማታደርግ ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ አምስቱ መሪዎቻችን ስትገድል አይተናል እናም የአጸፋ ምላሽ የመስጠት መብት አላን ሲል አስታዉቋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
399 viewsTrue, 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:54:14
400 viewsTrue, 07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:32:07 ኹለተኛው ምዕራፍ የኦነግ ሸኔ እና የመንግሥት ድርድር በቅርቡ እንደሚደረግ ተሰማ

ለኹለተኛ ጊዜ በፌዴራል መንግሥት እና በኦነግ ሸኔ መካከል የሚደረገው ድርድር በቅርቡ እንደሚጀመር የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኃይሉ አዱኛ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፤ ለኹለተኛ ጊዜ በፌዴራል መንግሥት እና በኦነግ ሸኔ መካከል የሚደረገው ድርድር በቅርቡ እንደሚጀመር አሳውቀዋል፡፡

ኃላፊው በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላይ ግጭትን በዘላቂነት ለማቆም፣ የሕዝብን እና የአገርን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በኦሮሚያ ክልል በሀሳብ አለመግባባት በመንግሥት እና በኦነግ ሸኔ ኃይሎች መካከል እየተፈጠሩ ባሉ ግጭቶች እየተሰቃየ የሚገኘውን ሕዝብ በዘላቂነት ሰላሙን ለመመለስ እና በነጻነት ወጥቶ እንዲገባ ለማስቻል በሰለጠነ መንገድ ከመወያየት እና ውሳኔ ላይ ከመድረስ በቀር ሌላ አማራጭ የለንም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ለዚህም <<መንግሥት በክልሉ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን ወደ ሠላም መንገድ ለመመለስ ብሎም ሃሳባቸውን ለመስማት ዝግጁ ነው።>> ያሉ ሲሆን፤ ሕዝቡ ከጦርነት ወሬ ወጥቶ ወደ መደበኛ ሕይወቱ እንዲመለስ እንዲሁም ኑሮውን እንዲያሻሽል መግባባት እና ሠላም ማውረዱ አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በታንዛኒያ ሲደረግ በነበረው ድርድር የተሻለ መቀራረብ እና መግባባት እንደነበረ ያስታወሱት ኃላፊው፤ በቅርቡ በሚደረገው ኹለተኛ ዙር የድርድር መድረክ ይህንኑ ምህዳር በማስፋት ዘላቂነት ያለው ሰላም ለማስፈን መንግሥት አጽንኦት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የትኛውም የፖለቲካ ኃይል ከዚህ በፊት ካሳለፍናቻው ጥፋቶች በመማር እና አሁን የተመቻቸውን የውይይት እንዲሁም የድርድር ጅማሮ በመጠቀም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመጣም የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡

የሕዝባችንን እና የአገራችንን ሰላም ለመመለስ የተጀመረውን የሰላም ድርድር ለማደናቀፍ እና ከግብ እንዳይደርስ እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሠላም ጠል አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም ኃላፊው ጠይቀዋል፡፡

የተጀመርው ድርድር በስኬት እንዲጠናቀቅም የሐይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች ምሁራን እና መላው ሠላም ወዳድ የኢትዮጵያ ሕዝብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በኦሮሞ ነጻነት ስራዊት እና የፌዴራል መንግሥት መካከል ሲደረግ የነበረው የመጀመሪያው ዙር ድርድር በታንዛኒያ ራስ ገዝ በሆነቸው ዛንዚባር ደሴት በኬንያ እና በታንዛኒያ አደራዳሪነት ሲደረግ እንደነበር ይታወሳል።

በመጀመሪያው ዙር ድርድር ኹለቱ ኃይሎች ባደረጉት ድርድር ያለ ስምምነት መለያየታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ ስምምንት ላይ ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች ውሳኝ የሚባሉ የፖለቲካ ጉዳዮች መሆናቸውም ገልጸዋል፡፡

Via አዲስ ማለዳ
#ዳጉ_ጆርናል
684 viewsBeⓒk, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 10:23:33 በደብርሃን ከተማ በነፃ መሬት ይሰጣል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ተነገረ

በደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ቤት የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች ወደ ከተማው በመምጣት መሬት በነፃ ይሰጣል ተብለናል በማለት ሀሰተኛ መረጃ ይዘው የሚመጡ በርካታ መሆናቸውን የከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ በየነ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በከተማው ከዚህ ቀደም በርካታ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ህገ ወጥ መኖሪያ ቤቶች ናቸው በሚል ቤት እንደፈረሰባቸው የታወቀ ሲሆን ወደ ወደ ደብረብርሃን ከተማ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም ከኦሮሚያ ክልል ከዚህ በፊት የተፈናቀሉ በርካታ በመሆናቸው ከአዲስ አበባ እና ዙሪያው የመጡትን የተወሰኑንት ብቻ በመቀበል ሌሎቹን ግን በቂ ምግብ፣መጠለያ እና አልባሳት ባለመኖሩ ወደ መጡበት እንዲመለሱ የተደረገ ሲሆን አቅም ያላቸው ደግሞ በከተማው መኖሪያ ቤት ተከራይተው እየኖሩ መሆኑ ተገልፆል፡፡

አሁንም በከተማው ከ25 ሺ በላይ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን መጪው የክረምት ወቅት በመሆኑ የምግብ እና የመጠለያ ድጋፍ እንደሚያስገልፋቸዉ ተጠቁሟል፡፡በቀጣይ ከአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚመጡ ተፈናቃዮች በቂ መጠለያ ባለመኖሩ መቀበል እንደማይችሉ እና መሬት ይሰጣል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ በመሆኑ ዜጎች ሊጠነቀቁ ይገባል ሲሉ የከተማው ከንቲባ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ፀጋዬ በየነ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
794 viewsTrue, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 08:52:33
ዘማሪት ሂሩት በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

ዘማሪት ሂሩት በቀለ፣ ባደረባት ህመም በሃገር ውስጥና በውጭ በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው እለት ግንቦት 04 ቀን 2015 ዓ.ም ህልፈተ-ሕይወቷ ተሰምቷል፡፡

ከ1950 መጀመሪያ እስከ 1980ዎቹ መጨረሻ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያስደመጠችን ሂሩት በቀለ ሕይወት እንደሸክላን ጨምሮ በርካታ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን እንካችሁ ብላለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘማሪነት/አገልጋይነት ስራዎችን ስትስራ እንደነበር ይታወሳል፡፡

የቀድሞ ድምጻዊት ከዛም ዘማሪት ሂሩት በቀለ በተወለደች በ80 ዓመቷ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየችው፡፡

ሂሩት በቀለ የ7 ልጆች እናት፣የ10 ልጆች አያት እና የ7 ልጆች ቅድመ አያት ነበረች።

ምንጭ :- ታዲያስ አዲስ

#ዳጉ_ጆርናል
1.5K viewsNH, edited  05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 20:32:03 የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ለጥርስ ህክምና በሚል በእንግሊዝ የሚያደርጉትን ቆይታ አራዘሙ

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ለጥርስ ህክምና የለንደን ቆይታቸውን ለአንድ ሳምንት ማራዘማቸዉን ረዳታቸዉ ገልጸዋል፡፡ፕሬዝዳንቱ ወደ እንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ባለፈው ሳምንት የተጓዙት የንጉሥ ቻርለስ ሳልሳዊ የንግሥና ሥነ ሥርዓት ላይ ለመታደም ነበር።

በዚህ ሳምንት ወደ ናይጄሪያ ለመመለስ ቀጠሮ ተይዞላቸዉ የነበረ ቢሆንም በጀመሩት የጥርስ ህክምና ምክነያት ቆይታቸዉን ለማደራዘም ወስነዋል፡፡የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ ፌሚ አዴሲና በሰጡት መግለጫ “የጥርስ ሀኪም ስፔሻሊስቱ ፕሬዚዳንቱን በአምስት ቀናት ልዩነት ውስጥ ማየት አለባቸው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ የተራዘመ የቆይታ ጊዜ በአገር ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ትችቶችን አስከትሏል፣ ራሳቸዉ ለመታከም የማይመርጡት የህክምና ስርዓት ዘርግተዋል በሚልና ለአገር ውስጥ ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠት ይኖርባቸዋል ምክንያቱም የጸጥታ ችግር እየተስፋፋ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡እ.ኤ.አ በ 2015 ቡሃሪ ወደ ስልጣን ከወጡ በኋላ ፣ ባልታወቁ የህክምና ምክንያቶች ወደ እንግሊዝ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተጉዘዋል ።

እ.ኤ.አ በግንቦት 29 ለተመራጩ አዲሱ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲንቡ ስልጣናቸዉን አሳልፎ ለመስጠት ቀነ ቀጠሮ ተይዞለታል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.0K viewsTrue, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 19:28:53
ፈጣሪን ለማስደሰት ዘንጠዉ የሚታዩ ጎሳዎች
dressing like millionaires in poverty

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚኖሩ ሳፐርስ በመባል የሚታወቁ ሰዎች የዳንዲዝም የህይወት ዘይቤ ተከታዮች ሲሆን ፈጣሪ ተዉበን እንድንታይ ይፈልጋል የሚል አመለካከትን ከ300 ዓመታት በላይ አዳብረዋል፡፡ በፈጣሪ ዘንድ ዘንጦ ለመታየት የሚከተሉትን ማድረግ ግድ ይላል።

1.  ረዘም ያለ ካልሲ
2.  በአንድ ጊዜ ሶስት የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ልብስ መልበስ
3.  አንድ ሳፖር ከተለመደው የንፅህና አጠባበቅ በተለየ መልኩ ግላዊ ንፅህናውን የመጠበቅ ግዴታ አለበት
4.  ሰዓት ማሰር የግድ ነዉ
5.  ምንም ዉድ ቢሆንም ከልብሱ ጋር የሚሄድና የታወቀ ብራንድ ያለው ልብስና ጫማ መልበስ
6.  አንድ ሳፖር ሙሉ ሱፍ ወይም ደግሞ የሱፍ ኮት በሚለብስበት ሰወቅት የልብሱን አምራች የሚገልፀ ማንኛውም ምልክት ከሱፉ ማስወገድ ይገባዋል
7.አንድ ሳፖር ምንም አይነት ኣደንዛዥ እፅ እንዲጠቀም አይፈቀድም
8.ሳፖሮች እጅግ ሰላማዊ ከመሆናቸው የተነሳ ሽጉጡን ትተን ስራ እንስራና ቅንጡ ልብሶችን እንልበስ የሚል መሪ ሃሳብ ያላቸውና እጅግኑ ኣማኞች የሆኑ ከቤተ ክርስትያን ደጃፍ የማይጠፉ ሰዎች ናቸው።
9. የመጨረሻውና ዋነኛው መርህ ደግሞ አንድ ሳፖር ሱሪዉን ዝቅ ኣድርጎ መልበስም ሆነ የቻይና ምርት የሆነ ልብስ መልበስ በፍፁም የተከለከለ ነው።

Via ዳጉ ጆርናል
3.1K viewsTrue, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 19:10:48 ኢትዮጲያ  ከቆዳ የምታገኘው ገቢ ከዓመት ዓመት ቅናሽ እያሳየ መሆኑ ተነገረ

በኢጠዮጲያ የቆዳ እና ሌጦ  ኢንዱስትሪ ከስጋ ማምረት ሂደት ውስጥ የሚገኘውን ተረፈ ምርት  መሰረት ያደረገ  ሲሆን በአሁኑ ሰአት  ኢትዮጵያ ከዚሁ የቆዳ ኢንዱስትሪ የምታገኘው ትርፍ  በየጊዜው እየቀነሰ መሆኑን የኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሰለሞን ጌቱ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ኢንደስትሪው ከአምስት አመት በፊት ከውጭ ምንዛሬ እስከ 130 ዶላር ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ታገኝ እንደነበረ ያስታወሱት ዋና ጸሃፊው ባለፈዉ 2014 በጀት ዓመት የተገኘዉ ገቢ  ከ 40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያልበለጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡በተያዘዉ የ2015 በጀት ዓመት ያለው ገቢ ከወር ወር መቀነስ እያሳየ መሆኑ አሳሳቢ እንዳደረገዉ አንስተዋል፡፡

ለገቢው መቀነስ በርካታ ምክንያቶች ያሉት ቢሆንም በዋናነት ከከብት እርባታ ጀምሮ ያለው አያያዝ የሚያመጣው ችግር ብሎም ደግሞ  ከ 95 በመቶ በላይ የሚካሄደው እርድ  በተደራጀ መልኩ አለመሆን ዋናው ተግዳሮት እንደሆነ አንስተዋል፡፡ የጥሬ ቆዳ እና ሌጦ የግብይት ሰርአት አዋጅ ጸድቆ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ወደተግባር  አልገባም፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ያለዉ ችግር እንዲብሱ ምክንያት ሆኗል የሚሉት አቶ ሰለሞን በንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር በኩል ክፍተቱ ታይቶ ወደስራ እንዲገባ  ቢደረግ ችግሮቹ ሊፈቱ የሚችሉ መሆናቸዉን ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
2.8K viewsTrue, 16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ