Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.42K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-25 17:13:42
የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በሚኒባስ ተሽከርካሪ ውስጥ ባዶ ፍራሽ አንጥፈው የኩላሊት ታማሚ የተኛ በማስመሰል በህክምና ሰበብ ገንዘብ ሲሰበስቡ የተገኙ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።ግለሰቦቹ ድርጊቱን ሲፈፅሙ የተገኙት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማራስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው አራት ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 43018 አ.አ በሆነ ሚኒባስ ውስጥ ባዶ ፍራሽ በማንጠፍ ፣ በፍራሹ ላይ የኩላሊት በሽታ ታማሚ የተኛ በማስመሰልና የግለሰብ ፎቶ በባነር አሳትመው በመስቀል በስፒከር እየቀሰቀሱ በህክምና ወጪ ሰበብ ከህብረተሰቡ ገንዘብ ሲሰበስቡ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ ባከናወኑት የማረጋገጥ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsTrue, 14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:14:01 ዩክሬን 78 ዜጎቿን ከሱዳን አስወጣች

ዩክሬን 87 ዜጎቿን ጨምሮ 138 ሰዎችን ከሱዳን ወደ ግብፅ ማስወጣቷን አስታውቃለች። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና የስለላ ዳይሬክቶሬት በቴሌግራም ላይ በሰፈሩት መልዕክት "በሱዳን የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በአጠቃላይ 138 ሰዎች ከሱዳን በማስወጣት ግብፅ በሰላም መድረሳቸውን” ተናግረዋል።

በሱዳን አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱ ይፋ ቢደረግም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ይገኛል።ከ11 ቀናቶች በፊት የተጀመረውን ጦርነት ለማስቆም አራተኛው የተኩስ አቁም ጥረት ሲሆን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ሙከራዎች ገቢራዊ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እንደተናገሩት የ72 ሰአታት እርቀ ሰላም በጦር ኃይሉ እና በፈጣን ደጋፊ ሰጪ ሃይሎች (RSF) መካከል ከ48 ሰአታት ድርድር በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። የመጨረሻው የተኩስ አቁም ስምምነት የተጀመረው ሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ ነው። በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን ቢያንስ 459 ሰዎች እንደተገደሉ ቢነገርም ትክክለኛው የሟቾች ቁጥሩ ከዚህ የበለጠ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን እንደሚያቆሙ ግን ማረጋገጭም ሰጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.2K viewsTrue, 13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 15:56:23 በሀገረ አቀፍ ደረጃ  የደም እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ  መኖሩ ተነገረ

      በቀን 400 ዩኒት ደም ያስፈልጋል

በኢትዮጰያ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ የደም እጥረት ያለ ሲሆን ይህ የሆነውም በቀደሙት ወራት  በነበረው የአብይ ጾም እና የረመዳን ጾም  አማካኝነት አብዛኛው ህብረተሰብ ደም መለገስ ባለመቻሉ መሆኑን  የኢትዮጰያ ደም እና ህብረ ህዋስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬከተር አቶ ሃብታሙ ታዪ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ይህ መሆኑን ተከትሎ የካንሰር ህሙማንን ጨምሮ በየቀኑ ደም የሚያስፈልጋቸው ህጻናት ደም እያገኙ አለመሆኑን ያስረዱ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች ጨምሮ ይህ የደም እጥረት መኖሩንም  አንስተዋል ፡፡ በአዲስአበባ ደረጃ እንኩዋን በቀን 400 ዩኒት ደም የሚያስፈልግ ቢሆንም አቅርቦት እና ፍላጎት እየተጣጣመ አይደለም ብለዋል፡፡

ከጾም ፍቺ  በኋላ ባሉት ቀናት 300 እሰከ 400  ዩኒት ደም መስበስብ የተቻለ ቢሆንም ብዙ ሆስፒታሎች የተሰበሰበውን ደም ወዲያው መጥተው በመውሰዳቸው  እና አሁንም  በርካታ ዩኒት ደም በማስፈለጉ የዘመቻ ስራዎች እተሰሩ ስለመሆኑ ያነሱት  አቶ ሃብታሙ ሆኖም ግን አሁንም ድረስ የማህበረሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ በመሆኑ የተፈለገውን ያህል ደም መስብሰብ አለመቻሉን አንስተዋል፡፡

አቶ ሃብታሙ አክለውም አንድ ሰው ከሚሰጠው ደም  የሶስት ሰው ሂወት ማዳን እንደሚቻል ሲያነሱ በተለይ ለካንሰር ህሙማን የሚያገለግለው ሴል እጅግ ተፈላጊ ነውም ብለዋል፡፡ህብረተሰቡ አሁንም ከፍተኛ ደም እንዲያስፈልግ እና በርካቶች በደም እጥረት እየተሰቃዩ መሆኑን አውቆ  ደም  ቢለግስ ሲሉ የኢትዮጰያ ደም እና ህብረ ህዋስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬከተር አቶ ሃብታሙ ታዪ ጨምረው ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጰያ ደም እና ህብረ ህዋስ አገልግሎት ባላፉት ዘጠኝ ወራት እሰበስባለሁ  ያለውን ደም አለሰበሰበም ፡፡

ቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
3.1K viewsTrue, edited  12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 15:56:18
2.9K viewsTrue, 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:33:44
የክልል ፕሬዝዳንቶች በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ትግራይ ክልል እንደሚጓዙ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ተናገሩ

ይህ የተነገረው በዛሬው እለት በተካሄደው "ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናጽና" የምስጋና እና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ በተከነወነው መርሃ ግብር ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) የክልል ፕሬዝዳንቶች በቀጣዮቹ ቀናት ወደ ትግራይ ክልል እንደሚጓዙ ላይ በመድረኩ ገልፀዋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነቱ እልባት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የማመስገንና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

በመረሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት፣ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በቤቴልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
2.2K viewsTrue, 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:32:10
ኦነግ ሸኔና የኢትዮጲያ መንግስት በታንዛኒያ ከማክሰኞ ጀምሮ ንግግር እንደሚጀምሩ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ተናገሩ

ይህ የተነገረው በዛሬው እለት በተካሄደው "ጦርነት ይብቃ፣ ሰላምን እናጽና" የምስጋና እና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ በተከነወነው መርሃ ግብር ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ከኦነግ ሸኔ ጋር የፊታችን ማክሰኞ በታንዛኒያ ንግግር እንደሚጀምር በመድረኩ ገልፀዋል።

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የነበረው ግጭት በሰላም ስምምነቱ እልባት እንዲያገኝ ቁልፍ ሚና ለነበራቸው አካላት የማመስገንና የእውቅና መረሀ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።

በመረሀ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት፣ የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አንጋፋ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በቤቴልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል
2.1K viewsTrue, edited  16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 22:07:16 የ5 አመቱን ህፃን አፍኖ በመውሰድ የ1.5 ሚሊዮን ብር ክፍያ የጠየቀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ!


የአጋች ታጋች የወንጀል ጉዳይ ልፋትን የጠየቀ አዲስ አበባን ጨምሮ አራት ከተሞችን ያደረሰ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ህፃኑ በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የጠቆመ ሲሆን በህፃኑ እገታ ዋና ወንጀል ፈፃሚ የሆነው አማኑኤል ተክላይ የተባለው ግለሰብ ቤተሰባዊ ጉዳይን ምክንያት በማድረግ  የ5 ዓመቱን ህፃን ናታኒ ጎይቶምን ሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ/ም አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አለም ባንክ ስድስት ጎጆ ከሚባል አካባቢ ከሚገኘው የህፃኑ ወላጆች ቤት አፍኖ በመውሰድ 1.5 ሚሊዮን ብር ካልተከፈለው ልጁን እንደሚገድለው ይዝታል፡፡

የህፃኑ መታገት መረጃው የደረሰው አዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ጋር በጥምረት ባከናወነው ብርቱ የምርመራና የክትትል ተግባር ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ህፃኑን ለወላጆቹ ማስረከቡን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ከአርባ ምንጭ ቀጥሎ አዋሳ ከዚያም አዳማ ከተማ  እየተዘዋወሩ አድራሻቸውን ለማጥፋት ጥረት ቢያደርጉም የፖሊስ የክትትልና የምርመራ አባላት 24 ሰዓት ባደረጉት ጠንካራ ክትትል እና ምርመራ ሚያዝያ 14 ቀን 2015 ዓ/ም ቢሾፍቱ ከተማ ሸማኔ ሜዳ አካባቢ ህፃን ናታኒም ጎይቶም ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስበት ማግኘታቸው ታውቋል፡፡

ተጠርጣሪው አማኑኤል ተክላይ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ለፖሊስ በሰጠው ቃል የህፃኑ አክስት ገንዘብ ስለወሰደችበት ብሩን ለማስመለስ ወንጀሉን እንደፈፀመ አስረድቶ ባልጠቀቀው ሁኔታ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ተናግሯል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቦ በዚህ የህፃን አፈና  የወንጀል ድርጊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጃቸው ያለበትን ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ህግ ፊት ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

#ዳጉ_ጃርናል
3.7K viewsNH, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 22:06:30
3.3K viewsNH, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 13:51:53
በሻሸመኔ ከተማ ቁልፍ በማስቀረፅ ተሽከርካሪ የሰረቀው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ

በሻሸመኔ ከተማ ወረዳ 02 ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ንብረትነቱ የአቶ አብዱልቃድር የሆነ ተሽከርካሪን ቁልፍ በማስቀረፅ አስነስቶ ሊያመጥ የነበረው ተከሳሽ በእስራት መቀጣቱን የወረዳ 02 ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን አህመድ ሲሊ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።የግል ተበዳይ ተሽከርካሪ የህዝብ ማመላለሻ የሆነ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 ቢ አ.አ 78942 መሆኑን የክስ መዝገቡ ያሳያል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ሚያዚያ 7 ቀን 2015 ሲሆን በእለቱ በሻሸመኔ ከተማ በተሰናዳው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ ወደ መኖሪያ ቤታቸው አቶ አሽዱልቃድር ማቅናታቸውን ተከሳሽ ረይኑ አህመድ ሲከታተል ቆይተዋል።ተከሳሹ ከተሽከርካሪው በተጨማሪ የመኖሪያ ቤታቸውን ቁልፍ አስቀርጾ የነበረ ሲሆን አቶ አብዱልቃድር ላይ ቤቱን ከወጪ በመዝጋት መኪናውን አስነስቶ ለመሰወር ይሞክራል።

በዚህ ወቅት በተሽከርካሪ ጥበቃ ላይ የነበረ ግለሰብ እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ለፀጥታ አካላት ያሳውቃል። ፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል መዝገቡን አጣርቶ ለፍርድ ቤት ያቀርባል። የክስ መዝገቡን የተመለከተው የሻሸመኔ ወረዳ ፍርድ ቤት በፈጣን ችሎት ተከሳሽ ረይኑ ጥፋተኛ በማለት በአምስት ዓመት እስር እንዲቀጣ ውሳኔ ማሳለፉን ሳጅን አህመድ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.9K viewsTrue, 10:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 12:42:11
#እያንዳንዳቸው በብር 8000(ስምንት ሺህ)ዋስትና ከእርስ ሊለቀቁ ፍ/ቤቱ ወስኗል

ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ከመጋቢት 17/2015 ዓ.ም ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በፍ/ቤት ይሁንታ ታሰረው መቆየታቸው ይታወቃል ::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 14/2015 ዓ.ም በዋለው የጊዜ ቀጠሮ ችሎትም ፖሊስ የምርመራ ስራዬን ለማጠናቀቅ እችል ዘንድ ተጨማሪ 14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል:በእኔ በኩል የደንበኞቼ የዋስትና መብት እንዲከበር ተገቢውን ክርክር አቅርቤያለሁ::

  ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎትም የፖሊስን የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ውድቅ በማድረጋ እያንዳንዳቸው በብር 8000(ስምንት ሺህ)ዋስትና ከእርስ ሊለቀቁ ይገባል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል::

#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsTrue, edited  09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ