Get Mystery Box with random crypto!

ዩክሬን 78 ዜጎቿን ከሱዳን አስወጣች ዩክሬን 87 ዜጎቿን ጨምሮ 138 ሰዎችን ከሱዳን ወደ ግብ | ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

ዩክሬን 78 ዜጎቿን ከሱዳን አስወጣች

ዩክሬን 87 ዜጎቿን ጨምሮ 138 ሰዎችን ከሱዳን ወደ ግብፅ ማስወጣቷን አስታውቃለች። የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር ዋና የስለላ ዳይሬክቶሬት በቴሌግራም ላይ በሰፈሩት መልዕክት "በሱዳን የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ በአጠቃላይ 138 ሰዎች ከሱዳን በማስወጣት ግብፅ በሰላም መድረሳቸውን” ተናግረዋል።

በሱዳን አዲስ የተኩስ አቁም ስምምነት መደረሱ ይፋ ቢደረግም በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች አሁንም የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ይገኛል።ከ11 ቀናቶች በፊት የተጀመረውን ጦርነት ለማስቆም አራተኛው የተኩስ አቁም ጥረት ሲሆን ከዚህ ቀደም የተደረጉ ሙከራዎች ገቢራዊ መሆን ሳይችሉ ቀርተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እንደተናገሩት የ72 ሰአታት እርቀ ሰላም በጦር ኃይሉ እና በፈጣን ደጋፊ ሰጪ ሃይሎች (RSF) መካከል ከ48 ሰአታት ድርድር በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። የመጨረሻው የተኩስ አቁም ስምምነት የተጀመረው ሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ ነው። በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን ቢያንስ 459 ሰዎች እንደተገደሉ ቢነገርም ትክክለኛው የሟቾች ቁጥሩ ከዚህ የበለጠ ይሆናል ተብሎ ይታሰባል። ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን እንደሚያቆሙ ግን ማረጋገጭም ሰጥተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል