2023-04-11 11:27:02
በሰሜን ወሎ ዞን በተለዩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ የሚደረግ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ውሳኔ ተላለፈ
የሰሜን ወሎ ዞን የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የዞኑን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ከሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የሚከተሉትን ክልከላዎችን ውሳኔ አሳልፏል።
ኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ የሚተገበርባቸው አከባቢዎች ቆቦ ከተማ፣ ራያ ቆቦ፣ ራያ አለማጣ፣ ራያ ባላ፣ አለማጣ ከተማ፣ መርሳ ከተማ፣ ሐብሩ እና ጉባላፍቶ ወረዳ ይሆናሉ።
ጥብቅ ክልከላዎች:-
1. ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
2. ኮማንድ ፖስቱ ባካተታቸው ወረዳዎች/ከተሞች ከዋናው አስፋልት መንገድ በግራ እና በቀኝ በአንድ ኪሎ ሜትር ርቀት የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ አይፈቀድም።
2. ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ፣ መጥረቢያ፣ ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል ነው።
3. በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገበያ እና ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
4. በክልከላው ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ቡኋላ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው ።
5. በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ።
6. የሠራዊቱን አልባሳት ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው። ማለትም የልዩ ኋይል ፣ የፓሊስ ፣ የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስ አልባሳትን ከሚመለከታቸው አካላት ውጭ መልበስ ወንጀል ነው።
7. በክልከላ በተካተቱ ወረዳዎች/ከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ብቻ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል።
8. የህዝብና የጭነት ተሽከርካሪዎች ከንጋቱ 12:00 እስከ ምሽት 2:00 ሰዓት ብቻ የሚንቀሳቀሱ ይሆናል።
9. የእግረኛን እንቅስቃሴን በተመለከተ ኮማንድ ፖስት በታወጀባቸው ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከንጋቱ 12:00 እስከ ምሽት 3:00 ብቻ ይሆናል።
9. በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ ያስጠለለ፣ ስንቅ ያቀበለ፤ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ያደናቀፈ እና ያወከ በህግ የሚጠየቅ ይሆናል።
10. በየደረጃው መንግስት ያልፈቀደው ማንኛውም አይነት ስብሰባ እና መንግስት ያልፈቀደው ሠልፍ ማድረግ፣ መቧደን፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው።
11. አድማ መቀስቀስ፣ መንገድ መዝጋት እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን መግታት፣ ከመንግስት አካላት ውጭ መዋጮ ወይም ገንዘብ መሠብሰብ፤ ኬላ ማቋቋም፣ ህዝብን እረፍት መንሳት እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው።
12. ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።
13. የመንግስትን የታጠቀ ሀይል ያስከዳ፣ በተለያየ መንገድ አማሎ የጦር መሳሪያ የገዛ፣ የለወጠ፣ ባልተገባ መንገድ መታወቂያ የሠጠ፣ መንገድ የመራ ማንኛውም አካል በህግ ተጠያቂ ይሆናል።
14. የመንግስት የጸጥታ ሀይል ህግና ስርአትን ለማስከበር በሚያከናውናቸው ተግባሮች ዙሪያ ማንኛውም ሠው የመተባበር ግዴታ አለበት። የማይተባበር ከሆነ በህግ ይጠየቃል።
15. ማንኛውም አካል ለኮማንድ ፖስቱ ውሳኔዎች ተገዥ መሆን አለበት።
16.ማንኛውንም አይነት መረጃ ለዞኑ እና በየደረጃው ለተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ወይም የመንግስት የጸጥታ ሀይል መጠቆም ይችላል።
2.6K views08:27