Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-10 14:07:42 ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ አቀረቡ አቅርበዋል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት የተስጠው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል።

<<የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች ፵፰ ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያዬት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ማስተላለፏ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሆኖም ግን ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ላልተጋባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ሰሕዝባችን የሚያመጣው መፍትሒ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችንን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን እያሣወቅን ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት ትጠባበቁ ዘንድ እናሳስባለን፡፡>>

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት
2.3K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 23:09:56 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned «" ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ መላው ምዕመን ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቹን ድምጽ ብቻ እንዲሰማ አሳስቧል። " ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ "…»
20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 23:09:33 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned «" ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ መላው ምዕመን ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቹን ድምጽ ብቻ እንዲሰማ አሳስቧል። " ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ "…»
20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 23:09:21 " ሰላማዊ ሰልፉን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ እንሰጣለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ መላው ምዕመን ከስሜታዊነት በወጣ ሁኔታ በከፍተኛ ጽናት እና ጥንካሬ የአባቶቹን ድምጽ ብቻ እንዲሰማ አሳስቧል።

" ቤተ ክርስቲያንን በየአጥቢያችሁ ተደራጅታችሁ እንድትጠብቁ፤ ለአባቶቻችሁ መንፈሳዊ ጥሪ ፈጣን ምላሽ እንድትሰጡ " ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ " እየመጣው ላለ መከራና ስደት ለመንፈሳዊ ተጋድሎ እንድትዘጋጁና በፍፁም መንፈሳዊ ጨዋነት በአንድነት የመጣብንን ፈተና እንድትወጡ አደራ እያልን አባታዊ መልእክታችንን እያስተላለፋለን " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሊደረግ የታሰበውን ሰላማዊ ሰልፍን በተመለከተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ከዚህ ባለፈ ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " በዚህ ጥቃት መስዋእትነት የከፈሉ እና ያረፉ ልጆቻችንን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት በክብር ያሳርፍልን እያልን ጸሎተ ፍትሐትም በየደረጃው የሚከናወን መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

" ዛሬን ጨምሮ በወለቴ እና በሰበታ ከተሞች የደረሰውን የአካል ጉዳት እና ሞት እግዚአብሔር ምህረት እና መጽናናቱን ያድልልን " ያለው  ቅዱስ ሲኖዶስ " እግዚአብሔርም ገድላችሁን፣ ጽናታችሁንና ጸሎታችሁን ይቀበል፤ የቅዱሳን አምላክ ከሁላችን ጋር ይሁን " ብሏል።
1.1K views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 23:08:12 ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትላንት ምሽት የመንግሥት ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል " ወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ " ን አስመልክቶ የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ እንደማይቀበል አሳውቋል።

" መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን በጽኑ እንድናምን አድርጎናል " ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መንግስት ከአጉል እልከኝነቱ ወጥቶ ፦

- ከሕገ ወጦቹ ግለሰቦች ጋር በመተባበር በአደባባይ እየፈጸመ ያለውን የሕግ ጥሰት ዛሬን ጨምሮ በቀጣዮቹ ፪/ሁለት/ ቀናት ውስጥ እንዲያቆም እና ሕግ እና ሥርዓትን እንዲያስከብር

- በኃይል የወረራቸውን መንበረ ጵጵስና እና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለቆ ለቤተክርስቲያኒቱ ሕጋዊ መዋቅር እንዲያስረክብ፣

- ያለአግባብ ያሠራቸውን ካህናት እና ምእመናን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ፣

- ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ለፈፀመው በደል በአደባባይ ይቅርታ እንዲጠይቅ፤

- በካህናት እና ምእመናን ላይ ለደረሰው ሞት እና የአካል ጉዳት ተገቢውን ካሳ እንዲክስ እና የወደሙ ንብረቶቿን እንዲጠግን በጥብቅ ጠይቋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ መንግሥት #በዚሁ_አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መብቷን ለማስከበር እስከአሁን ድረስ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት 5/2015 ዓ/ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን አሳውቋል።

መንግሥት ድርሻው ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ብቻ መሆኑን ያሳሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ " ዛሬም ቢሆን መንግሥት ቆም ብሎ በማሰብ ከእኛ ከአባቶች ጋር ሃይማኖታዊ ፣ ቀኖናዊ እና መንፈሳዊ የአስተዳደር ሥርዓታችንን ባልጣሰ መልኩ ለመነጋገር እና ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ጥረት ካደረገ በውይይት ለመፍታት መንፈሳዊ በራችን ክፍት መሆኑን እናሳውቃለን " ብሏል።

ከዚህ ውጭ ግን በሁለቱ አባቶች መካከል የተፈጠረ ችግር እየተባለ የሚነገረው ፖለቲካዊ ጨዋታ የመንግሥት እንጂ በሀገሪቱ ሕጋዊ ሰውነት የሌላቸውና ከቤተ ክርስቲያን የተለዩ ግለሰቦች ጋር ማነጻጸር ሕገ መንግሥታዊም ሆነ ሞራላዊ የሕግ መሠረት የለውም ሲል አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ በህገመንግስቱ የተደነገገ መሰረታዊ መብት መሆኑን ገልጾ ቤተክርስቲያን የጠራችውን ሰላማዊ እና ሕጋዊ የሆነ የመብት ጥያቄ የማፈን ሂደትን በጥብቅ እንቃወማለን ብሏል። 

ሙሉ መግለጫ : https://t.me/tikvahethiopia/76397?single
1.1K views20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 11:34:57
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፤ መንግስት " በሃይማኖት መካከል ጣልቃ አልገባም "/" ገለልተኛ ነኝ " የሚሉ ንግግሮችን እና ሃሳቦችን ቢያራምድም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከዚህ ፍፁም ተቃራኒ መሆኑን እየገለፀች ትገኛለች።

ቤተክርስቲያን ህገወጥ ናቸው ብላ ያወገዘቻቸው አካላት የመንግስትን የፀጥታ አካላትን ሽፋን እያገኙ፤ የቤተክርስቲያን ስርዓትም በከፍተኛ ሁኔታ እየተጣሰ መሆኑን ገልፃለች።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በተለያዩ ክልሎች እና የፌዴራል መንግሥት በሚመራቸው ቦታዎች ውስጥ በሚገኙ የቤተ ክርስቲያኗ አህጉረ ስብከት የሆኑትን ሥርዓተ አምልኮዋን የምትፈጽምባቸው በየመዋቅሩ የሚገኙ አስተዳደር ቢሮዎችን  ከሕግ አግባብ ውጭ የቤተ ክርስቲያኗ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ግለሰቦችን በማካተት በመንግሥት ልዩ ኃይል ድጋፍ በመውረር እና በመስበር የሕግ አግባብነት በሌላቸው እንዲሁም መብት እና ጥቅም ሳይኖራቸው በማሸግ ቤተ ክርስቲያን ላይ ወረራ እየተፈጸመባት ይገኛል ብሏል።

በሻሸመኔ የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ ጉዳት ደርሷል።

በጭሮ/ ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የጸጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእመናን መወርወራቸውና ተኩስ ከፍተው እንደበር ቤተክርስቲያና ገልጻለች።

ዛሬ በጭሮ ምእመናን ከጠዋት ጀምረው ቤተ ክርስቲያኗን ሲጠብቁ የነበረ ሲሆን የዞኑ የጸጥታ ኃይል "በሁለታችሁ አንገባም" በማለት ገለልተኛ ለመሆን ሞክሮ ውሏል። ነገር ግን ምሽት ላይ ከክልል የመጣ ትእዛዝ ነው በሚል የክልሉ ልዩ ኃይልን ጨምሮ ተኩስ በመክፈት አስለቃሽ ጭስ ወደ ምእምናን መወርወሩ ተገልጿል።

ቤተክርስቲያኗ ፤ የመንግስት አካላት ሕግ ሲጣስ የሕግ አፍራሾች ተባባሪ ሆነው በመገኘታቸው እጅግ አሳፋሪ እና አንገት የሚያስደፋ ድርጊት ነው ብላለች።
2.7K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 11:33:28 የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ጉባዔ በመጥራት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት እና የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ የክፍል ኃላፊዎች፤ ካህናት፤ አገልጋዮች እና ምእመናን ላይ የተፈጸመውንናና እየተፈጸመ ያለውን ሕገ ወጥ እስርና ወከባ በፅኑ አውግዟል።

ዛሬ በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በሻሸመኔ ከተማ በደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ የወጡት ምዕመናን ላይ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ ሕገ ወጥ ድርጊት መፈፀሙን የገለፀው ቅዱስ ሲኖዶስ፤የተፈፀመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የተፈጸመው አሰቃቂ የሞት ድርጊትን ቤተክርስቲያን ፍጹም ታወግዛለች ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በጥር 26/2015 ዓ/ም ካስተላለፈው ውሳኔና ከሰጠው መግለጫ  ጋር ተያይዞ ዛሬ ዝርዝር አፈጻጸም መመሪያ አውጥቷል(ከላይ ተያይዟል)።

ቅዱስ ሲኖዶስ በመጪዎቹ የጸሎትና የምሕላ ጊዜያት የደነደኑ ልቦች ወደ ልቦናቸው ተመልሰው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥሪ ሰምተው የማይፈጽሙ ከሆነ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደረግ አሳውቋል።

በየካቲት 5/2015 ዓ.ም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ከጠዋቱ 11፡00 ጀምሮ በየአጥብያቸው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጠዋቱ 1፡30 ድረስ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተፈጸመ በኃላ ከጠዋቱ 2፡00 ላይ ሁሉም ገዳማት፣ አድባራትና አብያተ ክርስቲያናት በተመሳሳይ ሰዓት ደወል በመደወል ምእመናን በሙሉ እስከ ጠዋቱ 2፡30 ድረስ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከየአጥቢያው በመነሳት የጥምቀተ ባህር/የመስቀል አደባባይ ላይ ታቦተ ሕጉን በማክበር፤በማጀብ በዝማሬና በምህላ በአንድ ቦታ በመሰባሰብ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ ወስኗል፡፡
2.7K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-28 23:39:21 የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ መቀሌ ከተማ መድረሱ ታውቋል።የፌደራል ፖሊስም አየር ማረፊያውን ከቀኑ 10:00 በኋላ መረከቡ ተሰምቷል።ወደ ክልሉ ነዳጅ ማደያዎች ከጅቡቲ እንዲጫን ተፈቅዷል።
2.0K views20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 23:42:46 አዲስ አበባ

ነገ ሰኞ ታህሳስ 10/2015  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ 523 ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያ ክልልን አርማ የመስቀል እና መዝሙር የማዘመር ስራ እንደሚከናወን ተሰምቷል።በሂደቱ ላይ እንቅፋት ለሚሆኑ አካላት በቂ የፀጥታ ኃይል መሰማራቱ ታውቋል።

MLG
1.3K views20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-16 17:59:45
በቦሌ ክፍለ ከተማ 116 የሺሻ ዕቃዎች ተያዙ!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦሌ ክፍለ ከተማ 116 የሺሻ ዕቃዎች መያዛቸው ተገለጸ።የሺሻ እቃዎቹ የተያዙት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ብላክ ፒርል በተሰኘው የምሸት ክለብ ውስጥ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊሰ፣ የፌዴራል ፖሊሰ እና ደንብ አስከባሪዎች በጋራ በመሆን በሰሩት ኦፕሬሽን እንደሆነም ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

MLG
1.5K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ