2023-05-01 09:22:26
" የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም አለን " - አቶ ካሳሁን ፎሎ
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) መንግስት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ለመጠየቅ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አቅዶ የነበር ቢሆንም መንግሥት ሰልፉን እንዳይደረግ መከልከሉን አሳውቋል።
የኮንፌደሬሽኑን ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ እንዳሳወቁት ፤ ዛሬ የሚከበረውን የሰራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ)ን ተተርሶ ነበር ሰልፉ እንዲደረግ ታቅዶ የነበረው።
የሰልፉ ዋነኛ ዓላማ ፤ ሰራተኛው በኑሮ ውድነቱ መኖር ባለመቻሉ መንግሥት የገቢ ግብርን እንዲቀንስ ለመጠየቅ ሲሆን በተጨማሪም ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዲወሰን፣ የኤጄንሲ ሰራተኞች 20/80 ክፍያ ገቢራዊት እንዲሁም የመደራጀት መብትን ለመጠየቅ ነበር።
ነገር ግን የመንግሥት ፀጥታ ቢሮ ይሄ ሰልፍ እንዳይካሄድ መከልከሉን ኢሰማኮ አሳውቋል።
የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ፤ በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሽህ በላይ ሰራተኞች ይሳተፉበታል የተባለው ሰልፍ በከተማዋ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ መከልከሉ ገልጸዋል።
" ማክሰኞ ሚያዚያ 17 የከተማ አስተዳደሩን ስለ ሰልፉ አሳውቀናል ፤ ከሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋርም ስንነጋገር ነው የሰነበትነው ነገር ግን ካላንደር በዘጋው ቀን ድምጻችንን እንዳናሰማ ተከልክለናል " ብለዋል።
" ሰልፉን ለማድረግ ፈቃድ አያስፈልግም፡፡ እኛ ለራሳችን ደህንነታችንን እንዲጠብቁን አሳውቀናል፡፡ የአዲስ አበባ ጸጥታ ቢሮ ይህን ጥያቄ ይዛችሁ አደባባይ አትወጡም አለን፡፡ ህግ እናስከብረለን ስላሉ ሰራተኛው እንዳይጎዳ አስቀረነው " ሲሉ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ትላንት ምሽት ባወጣው ማሳሰቢካ ደግሞ የላብ አደሮች ቀንን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ ምንም አይነት የአደባባይ ኩነቶችና ሰልፍ እንዲሁም ፖሊስም ሆነ የአስተዳደር አካላት የሚያውቁት ምንም ዓይነት ስብሰባ የለም ብሏል።
መረጀውን ከአልዓይን ፣ የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) እና ከአ/አ ፖሊስ የተገኘ ነው።
1.9K views06:22