Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-04-19 14:49:55 ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ " ቴሌብር " ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል።

በ " ቴሌብር " ነዳጅ ስለ መቅዳት አሸከርካሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው ?

በቅድሚያ የ " ቴሌብር "ተጠቃሚ መሆን፤
በቂ ክፍያ የቴሌብር አካውንት ውስጥ ኖሩን ማረጋገጥ፤
የ " ቴሌብር " የሚስጥር ቁጥርዎን ማስታወስና በአግባቡ መያዝ፤

የአከፋፈል ሁኔታው ምን ይመስላል ?

የነዳጅ ማደያ ሰራተኞች የተጠቃሚውን ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ የእርስዎ ስልክ ላይ የሚስጥር ቁጥርዎን እንዲያሥገቡ የሚጠይቅ አጭር መልዕክት ይመጣሎታል፤

በመቀጠል የሚስጥር ቁጥርዎን ከማስገባትዎ በፊት ከደረስዎት መልዕክት ላይ የተቀመጠ ገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን ያረጋግጡ፤ ካረጋገጡ በኃላ የሚስጥር ቁጥርዎን ያስገቡ፤

በመጨረሻም ክፍያው ከተፈፀመ በኃላ የክፍያውን ማረጋገጫ አጭር የመልዕክት ቁጥር ወዲያውኑ ይደርሶታል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ፤ የተሽከርካሪ ነዳጅ ግብይት ከሚያዚያ 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ በ " ቴሌ ብር " ብቻ የሚፈፀም በመሆኑ ሁሉም አሽከርካሪ እንዳይጉላላ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
3.2K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:49:31 አቶኒዮ ጉተሬዝ ጉብኝቱን በአቶ ደመቀ ደብዳቤ መልከላቸው ተሰማ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፤ ወደ ትግራይ ለመጓዝ የያዙት እቅድ በኢትዮጵያ መንግስት ውድቅ በመደረጉ “ክፉኛ ተበሳጭተው” እንደነበር “ዋሽንግተን ፖስት” ጋዜጣ የተመለከተው አንድ ምስጢራዊ ሰነድ አጋለጠ። የዋና ጸሀፊው ጥያቄ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት አለማግኘቱን በመግለጽ ለጉተሬዝ ደብዳቤ የጻፉላቸው፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መሆናቸው በዚሁ ምስጢራዊ ሰነድ ይፋ ተደርጓል።
“ዲስኮርድ” በተሰኘው የመልዕክት መለዋወጫ “ሰርቨር” የተለቀቁትን እነዚህን ሰነዶች ያወጣው፤ የማሳቹሴትስ የአየር ኃይል ብሔራዊ ዘብ ባልደረባ የነበረ የ21 ዓመት ወጣት ነው።

አሜሪካ “በወዳጆቿ እና አጋሮቿ ላይ ስታካሄድ የቆየችውን ስለላ ያጋለጡ ናቸው” ከተባለላቸው ሰነዶች መካከል አራቱ፤ ከጉተሬዝ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን “ዋሽንግተን ፖስት” ትላንት ሰኞ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። የካቲት 10፤ 2015 የተጠናቀረ አንድ ሪፖርትን በማሳያነት የጠቀሰው ዘገባው፤ ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያደርጉት ያቀዱት ጉዞ መሰረዙን በተመለከተ፤ በወቅቱ በተመድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን ታዬ ታዬ አጽቀስላሴን ለመጋፈጥ ፈልገው እንደነበር አትቷል።

ጉተሬዝ ወደ ትግራይ ሊያቀኑ አቅደው የነበረው፤ በክልሉ የነበረውን ጦርነት ላስቆመው የሰላም ስምምነት ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ ነበር ተብሏል። ንደ “ዋሽንግተን ፖስት” ዘገባ ከሆነ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ እቅድ የተጨናገፈው፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጉብኝቱን ውድቅ የሚያደርግ ደብዳቤ ከላኩላቸው በኋላ ነው ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።
2.4K views11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:09:07 የተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ትጥቅ የሚፈቱ የቀድሞ ተዋጊዎችንና ታጣቂዎችን የመመዝገብና ወደ ማዕከሎች የማስገባት ሥራ በቀጣዩ ሰኔ እንደሚጀምር ማስታወቃቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። ኮሚሽኑ የቀድሞ ተዋጊዎች ትጥቅ ፈትተው እንደጨረሱ ዋናውን ሥራውን እንደሚጀምር የገለጡት ኮሚሽነሩ፣ ኮሚሽኑ ተልዕኮውን ለመወጣት የኹለት ዓመት ዕቅድ አዘጋጅቷል ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል። ከ250 ሺህ እስከ 300 ሺህ የሚገመቱ የቀድሞ ተዋጊዎችንና ታጣቂዎችን መልሶ ለማቋቋም 550 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ኮሚሽነር ተሾመ ተናግረዋል ተብሏል።(Wazema)
4.0K views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:34:13 የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጡ ሰብአዊ መብት የሚጥስ ነው ሲል አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በተመረጡ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የጣለዉን ማዕቀብ እንዲያነሳም ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት ጠይቋል።

አምንስቲ ኢንተርናሽናል እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት እገዳዉን ከጣለ 3ኛ ወሩን ይዟል።

እገዳዉ ሰዎች መረጃ እንዳያገኙ መገደብን ጨምሮ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን የመጠቀምና ያለመጠቀም የሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነዉ ብሏል።
4.0K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 10:27:03 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned a photo
07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 09:52:28
ሱዳን

በሌተና ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ሃይሎች የሱዳን ፖርትን ከፈጣን ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች ማስለቀቁ እየተዘገበ ነው።
1.4K views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 09:51:33 ሱዳን

የፈጥኖ ደራሹን ሀይል የሚደግፉት

አዲስ አበባ
አስመራ
ሞስኮ
ዱባይ
ቻይና ናቸው ተብሏል።

እነዚህ አገራት የፈጥኖ ልዮ ኮማንዶውን ጥቃት ሲያቀነባብሩ ነበር ሲል ነው የሱዳን ዋህድ ጋዜጣ የዘገበው። 11ሺ ጦር ኤርትራ ውስጥ ሲሰለጥኑ እንደኖሩና አሰልጣኙ ሻዕቢያ መሆኑንም ነው ጋዜጣው የዘገበው።

ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ የልዮ ፈጥኖ ደራሹ አዛዥ መሀመድ ሀምዳን ጋደሎ ( አህሜቲ) ከአዲስ አበባ መንግስት ጋር 4 ጊዜ የስልክ ልውውጥ አድርጓል ነው የተባለው። የአገሪቱን ጦር የመገናኛ ሬዲዮ የጠለፉት የሩሲያ መንታፊዎች ሲሆኑ ሞሳድ ለማስለቀቅ ቢጥርም እስካሁን አልተሳካለትም ብሏል ጋዜጣው።
1.4K views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 20:32:52
ሰበር

ሱዳን ነገሮች ተቀያይረዋል።

በሱዳን ካርቱም የተከሰተው ቀውስ የሀገሪቱ ጦር አዛዥ የሆኑት አልቡርሀን በሌላ አካባቢ ያለውን ጦር ወደ ካርቱም ጠርተዋል።የኢትዮጵያን መሬት ወሮ የነበረውን የጀኔራሉ ጦር ያለበትን የአልፋሽጋን ቦታ ጥሎ መውጣቱ ተሠምቷል።
2.4K views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 09:28:41 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይዕዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም
++++++++++++++++++++
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም የትንሳኤ በዓል
1.3K views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 21:01:23 ህወሓት በሱዳን የሚገኙ አባላቱን ጨምሮ  “የቡድን ትጥቆቹን የማስረከብ ሂደት” ከመጪው ሰኞ ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 16/2015 እንደሚከናወን የተሃድሶ ኮሚሽን አስታውቋል።የተሃድሶ ኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ብርጋዴየር ጄነራል ደርቤ መኩሪያ እንዳሉት በትግራይ ክልል እና በመከላከያ ሰራዊት የሚደረገው የቡድን ትጥቆች የመረካከብ ሂደት ከሚቀጥለው ሰኞ ጀምሮ እስከ ባሉት 8 ቀናት ለማጠናቀቅ ከመግባባት ላይ መደረሱን አብራርተዋል።
2.2K views18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ