Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-04-13 16:28:28
የፀሎተ ሀሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሥነ -ሥርዓቶች እየተከበረ ነው

በዓሉ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ቆሞሳት፣ ካህናት እና በርካታ ምዕመናን በተገኙበት ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቱ እየተከናወነ ይገኛል።
1.7K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 15:37:11
1.8K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:33:59 194 ቢሊዮን ብር እዳ እንዳለበት

በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በመንግሥት ተግባራዊ የሚደረገው የነዳጅ ዋጋ ማረጋጊያ ፈንድ፤ እስካሁን ድረስ የ194 ቢሊዮን ብር እዳ እንዳለበት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዓለም አቀፍና በኢትዮጵያ የነዳጅ ገበያ መካከል ያለውን ልዩነት ለመቆጣጠር የሚውለው ፈንድ፤ መንግሥትን እዳ ውስጥ ከቷል ያሉት የንግድና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትሩ ገብረመስቀል ጫላ ናቸው። ይህንን እዳ ለማቃለል የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ አስፈልጓልም ብለዋል።

በዚህም የድጎማ ሥርዓቱ ውጤት ማሳየት ጀምሯል ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሰኔ 28/2014 በተጀመረው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ሥርዓት እስካሁን ድረስ መንግሥት 9.8 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ተናግረዋል።

አዲሱ ሥርዓት ተግባራዊ መደረግ በጀመረበት ወቅት በቤንዚል የዓለም ዋጋና በአገር ውስጥ ዋጋ መካከል ከ44 ብር በላይ ልዩነት እንደነበረው የጠቀሱት ሚኒስትሩ፤ ይሁንና አሁን ላይ ያለው የዋጋ ልዩነት 10 ብር መድረሱ የመንግሥትን ጫና መቀነሱን ጠቅሰዋል።

የሚኒስትሩ አማካሪ አሕመድ ቱሳ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ይሠራበት የነበረው የዱቤ ሽያጭ መንግሥትን ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲያጣ እንዳደረገው ገልጸዋል። ምንም እንኳን በፍርድ ቤት የተያዙ ጉዳዮች ቢኖሩም የዱቤ ሽያጩ የፈንድ አስተዳደሩ እዳ እንዲበዛ ማድረጉን አስረድተዋል።

ይህን በማስመልከትም ከመጋቢት 2014 ጀምሮ ኩባንያዎች ከነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በቅድመ ክፍያ እንዲገዙ መደረጉም ተነግሯል።

መንግሥት ለኹሉም ተሽከርካሪዎች ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ በመጪው ሰኔ ሙሉ በሙሉ የሚያቋርጥ ሲሆን፤ በአራት ዓመታት ውስጥ የታለመለት የድጎማ ሥርዓቱም እንደሚቋረጥ ተጠቁሟል።
2.8K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:33:41 ከ100ሺህ በላይ የሚሆኑ የሶማሊላንድ ነዋሪዎች በግጭት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸዉን አምባሳደር መለሰ አለም ተናገሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ከፖለቲካ እና ከኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ አንጻር የመስሪያ ቤታቸዉን ሳምንታዊ ማብራሪያን የሰጡ ሲሆን ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ በሁለት ሀገራት የሚኖሩ አንድ ህዝቦች ናቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሶማሊላንድ ዱልባሃንቴ ታጣቂዎች አማካኝንነት የቆየ ግጭት መኖሩን በማስታወሰ በተፈጠረዉ አለመረጋጋት የተነሳ ከ 100ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ወደ ኢትዮጲያ መግባታቸዉን ገልጸዋል፡፡ግጭትን ፍራቻ ወደ ኢትዮጲያ ለመጡ የሶማሊላንድ ነዋሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር እንሰራለን ማለታቸዉን ተሰምቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ስደተኞች መኖራቸዉን በማንሳት ካለን ጥቂት ነገር እናካፍላለን፤ ስደተኞችን የመቀበል የምኮራበት ታሪክ አለን ሲሉ አምባሳደር መለሰ ዓለም ጨምረዉ ተናግረዋል፡
2.6K views13:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:37:35 የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፥ ከኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ " ከባድ የሙስና ወንጀል " ክስ የተመሰረተባቸው 5 ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተብለዋል።
2.6K views12:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:12:27 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned «ኤርሚያስ ለገሰ ከኢትዮ 360 መሰናበቱ ታውቋል።ኤርሚያስ ቀድሞ በኢሳት ቴሌቪዥን ሲሰራ ነበር።»
07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:12:22 ኤርሚያስ ለገሰ ከኢትዮ 360 መሰናበቱ ታውቋል።ኤርሚያስ ቀድሞ በኢሳት ቴሌቪዥን ሲሰራ ነበር።
2.9K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:12:02 ደብረብርሃን

ደብረብርሃ በህዝባዊ ተቃውሞ ለቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ዛሬ በተፈጠረው መግባባት ተከፍቷል።በትናንትናው እለት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የተከሰተው ችግር በውይይትና በሠላም እንዲፈታ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።አሁን ላይ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባና ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ መንቀሳቀስ ጀምረዋል።
2.8K views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 23:31:21 የደጀን መንገድ ለሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት ሆነ!

በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ምክንያት ለሶስት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ፤ ዛሬ ጠዋት ላይ መከፈቱን አንድ የከተማይቱ አስተዳደር ኃላፊ እና ነዋሪዎች ተናገሩ። ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች፤ ከአዲስ አበባ በደጀን ከተማ በኩል ወደ ባህር ዳር ለሚደረግ ጉዞ ገና ትኬት መቁረጥ አለመጀመራቸውን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ከተማ የሚወስደው አውራ ጎዳና፤ በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በምትገኘው ደጀን ከተማ የተዘጋው፤ ባለፈው ሳምንት አርብ መጋቢት 29፤ 2015 ዓ.ም ነበር። የአማራ ክልል “ልዩ ኃይል መበተንን የሚቃወሙ” የተባሉ ነዋሪዎች፤ በከተማዋ መግቢያ እና ውስጥ ባሉ ቦታዎች መንገዱን ከዘጉ በኋላ በደጀን በኩል የሚያልፉ የህዝብ እና የጭነት ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪዎች መተላለፍ አቁመው ቆይተዋል።

ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 3፤ 2015 ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ ግን፤ ለቀናት ተዘግቶ የነበረው መንገድ ተከፍቶ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ እንደጀመሩ የከተማዋ ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ተናግረዋል። የቡድን መሪው እንደሚያስረዱት መንገዱ የተከፈተው፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ጠዋት ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ተከትሎ ነው ሲል ኢትዮጵያን ኢንሳይደር ዘግቧል።።

☞ ይህ መንገድ ቢቸና ላይ በተሟላ መልኩ አለመከፈቱን ሰምቻለሁ።
1.6K views20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 23:30:49 ዛሬ ባህርዳር ከተማ በነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ቀበሌ12 ከሚኒሻዎች በተተኮሰ ጥይት የ 3 ሰዎች ህይወት ማለፉን አሁን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።
1.6K views20:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ