Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-25 23:36:23 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned a photo
20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 23:22:15
በማንኛውም ባንክ የሚገኝ ተቀማጭና ተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ እገዳ የተጣለባቸው ድርጅቶች!!
2.1K views20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:12:47 በ20 ሺሕ ብር ዋስትና እንዲወጡ ታዟል

የቀድሞው የ“አል አይን ኒውስ” ጋዜጠኛ እንዲሁም “አራት ኪሎ ሚዲያ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እና የኢትዮ ሰላም የበይነ መረብ ሚዲያ መስራች ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው ኹለቱም በ 20,000 ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት አዟል፡፡

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ሐሙስ ሚያዚያ 5/2015 ቂሊንጦ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ማክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱን የሚታወስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፤ ሚያዚያ 4/2015 ምሽት ላይ ባህርዳር ከሚገኘው "ሆምላንድ ሆቴል" በጸጥታ ኃይሎች መወሰዱ ይታወሳል።(ዳጉ ጆርናል
2.6K views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 16:07:01 ከታንዛኒያ ወደ ኮሞሮስ ሄደዋል

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የኮሞሮስ ዋና ከተማ ሞሮኒ ገብተዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን ሞሮኒ ሲገቡ የኮሞሮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶሂር ዳህልክማል ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አቶ ደመቀ ዛሬ ረፋድ ላይ ከኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ ጋር እንደሚገናኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በታንዛኒያ፣ ኮሞሮስ፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
2.5K views13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 14:16:50 በታንዛኒያ ራስ ገዝ ዛንዚባር የሚካሄደው የመንግስትና የሸኔ የሰላም ንግግር መጀመሩ ተሰምቷል።
ከዚህ ቀደም ብሎ የሸኔ(የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት) አዛዥ መሮ ዲሪባ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም ለድርድር ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት በማግኘቱ በታንዛኒያ በሚደረገው ንግግር ላይ እንደሚገኝ ባወጣው መግለጫ መጥቀሱ ይታወሳል። የሠራዊቱ ዋና አዛዥ መሮ ዲሪባ በታንዛኒያዋ ራስ ገዝ ግዛት በሆነችው ዛንዚባር ደሴት ላይ እንደሚከናወን ገልጸው፤ “የጥይት ድምጽ ሳይሰማ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ መልስ የሚያገኝ ከሆነ በራችን ሁሌም ክፍት ነው” ሲሉ ተናግሯል።
2.6K views11:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-25 10:01:02 የነዳጅ ክፍያን በሲቢኢ ብር እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል ይቻላል"የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ደንበኞች የነዳጅ ክፍያዎቸውን በሲቢኢ ብር እና አዲስ ይፋ በተደረገው ‘ነዳጅ’ የተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

ባንኩ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፣ የባንኩ ደንበኞች በሲቢኢ ብር አማካኝነት በማንኛውም የስልክ አይነት፣ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች መክፈል እንደሚችሉ እና ለዚህም ዲጂታል ደረሰኝ እንደሚያገኙ ገልጿል።

ባንኩ ይፋ ባደረገው ‘ነዳጅ’ በተሰኘ መተግበሪያ መክፈል እንደሚቻልም ተጠቅሷል፤ ይህ መተግበሪያም ከደንበኞች የቁጠባ ሐሳብ ጋር የሚገናኝ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ባንኩ ለደንበኞቹ ምቹ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና በቀላሉ የነዳጅ ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ‘ሲቢኢ ብር’ እና ‘ነዳጅ’ መተግበሪያ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ደንበኞች እነዚያን አገልግሎት በመጠቀም ተጠቃሚ እንዲሆኑም አቤ ሳኖ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በሪኦ ሀሰን የነዳጅ ክፍያ በዲጂታል መከናወኑ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።
Via:- EBC
2.8K views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 13:35:51 የ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ እስከ ሚያዝያ 20/2015 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚካሄድ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፥ ማንኛውም የስም፣ የፆታ፣ የተፈጥሮ/የማህበራዊ ዘርፍ እና የፎቶ ማስተካከያ ከፈተና በፊት ስለማይደረግ እያንዳንዱ ተፈታኝና እና መዝጋቢ ትክክለኛነቱን የማጣራትና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት ብሏል።

ይህ መሆን ያለበትም ምዝገባው በበየነ መረብ በመሆኑ በትምህርት ቤት ደረጃ የተካሄደው የምዝገባ መረጃ በቀጥታ በማንም ሳይነካ ወደ ተቋሙ የመረጃ ቋት የሚገባ በመሆኑ ነው ሲል አስረድቷል።

ከሚያዚያ 20/2015 ዓ/ም በኋላ በግለሰብ ወይም በተቋም በኩል የሚመጡ ተመዝጋቢዎችን አላስተናግድም ሲል በጥብቅ ያሳሰበው አገልግሎቱ ፥ ፈተናው የሚሰጠው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥና የመፈተኛ ጊዜን ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ እንደሚገለፅ አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፥ እስካሁን የመፈተኛ ጊዜ አልተገለጸም ያለ ሲሆን ተፈታኞች ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
3.3K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 13:49:10 በአዲስ አበባ ከነገ ሚያዝያ 16 ቀን ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ብቻ የሚፈጸም በመሆኑ ለተግባራዊነቱ በሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በቂ ዝግጅት አድርጊያለሁ ሲል ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።
1.8K views10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 11:31:45 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned a photo
08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 11:21:48
ለጀኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ቦሌ ሩዋንዳ የቆመው ሐውልትና ፓርክ ዛሬ በይፋ ተመርቋል።

ሐውልቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው በይፋ የተመረቀው።

የቀድሞ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ሰዓረ መኮንን "ሰራዊት ሀገር እንጂ ብሄር የለውም!" በሚል እምነት እና አስተሳሰባቸው ይታወቁ እንደነበር በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ጀኔራል ሰዓረ መኮንን ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ ከተራ ወታደርነት እስከ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምነት ሀገራቸውን ማገልገላቸው ይታወቃል።
(Walta)
549 views08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ