Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-25 13:44:51
ኢትዮጵያን በአሰብ በኩል ከኤርትራ ጋር የሚያገናኘው የሜሎዶኒ መገንጠያ-ማንዳ-ቡሬ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሆነ ተገለጸ፡፡

የመንገድ ግንባታው 71 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና በመንግስት በተመደበ ሁለት ቢሊዮን ብር በጀት በአስፋልት ኮንክሪት እና በሲሚንቶ ኮንክሪት ንጣፍ ደረጃ እየተገነባ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

መንገዱ በገጠር 10 ሜትር እና በቀበሌ ከተሞች ደግሞ 21 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ በመገንባት ላይ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የግብዓት እጥረት፣ በአካባቢው በነበረ የጸጥታ ችግር እና በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ተቀብረው ያልመከኑ ፈንጂዎች መኖር በግንባታ ሂደቱ ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድሩም ችግሮችን በመቋቋም ግንባታው በተፋጠነ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የሀገራዊ እና ቀጣናዊ ትስስሩ ጥረቱን ከማፋጠን ባሻገር የአካባቢው ነዋሪዎች የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም መሰል ግልጋሎቶችን መዳረስ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡

የአሰብ ኮሪደር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የሚካሄደው ሻንዶንግ ሉሽያዎ ግሩፕ ካምፓኒ ሊሚትድ በተባለ የውጭ ሀገር የሥራ ተቋራጭ ሲሆን ግንባታው በመጪው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ዘገባው የአሚኮ ነው
ፎቶ ኢመአ
6.7K views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 08:42:18 ሕወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመቃወም ቅሬታውን ለአፍሪካ ኅብረት አስገባ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የሕጋዊ ሰውነት ጥያቄ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃወም፣ ቅሬታውን ለአፍሪካ ኅብረት ማስገባቱን ሊቀመንበሩ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ሰኞ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም. በትግራይ ለሚገኙ የክልሉ ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት፣ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ከመንግሥት ጋር ተደራድሮ የፈረመው ሕወሓት እንደሆነና ስምምነቱን የመተግበር ኃላፊነትም ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ የሚተው እንዳልሆነ ገልጸዋል።

‹‹የሁሉም ነገር መነሻ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ነው። የስምምነቱ ፈራሚ ደግሞ ሕወሓት ነው። በመሆኑም ሕወሓት ትልቅ ኃላፊነት አለበት፤›› ብለዋል።

‹‹የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሁሉንም የሚያፈርስ ነው። የስምምነቱ ትግበራንም የሚያስር ነው›› ያሉት ደብረፂዮን (ዶ/ር)፣ ስለሆነም የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመቃወም ለፌዴራል መንግሥትና ለአፍሪካ ኅብረት ቅሬታ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

የሕወሓት ቀዳሚ ተግባር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ዓላማዎች ማሳካት መሆኑን የተናግሩት ደብረፂዮን (ዶ/ር)፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት፣ በስምምነቱ ላይ በተቀመጡት አንቀጾች መሠረት የሚተገበር እንጂ ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ የሚተው እንዳልሆነ አስረድተዋል።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) በሰጡት በዚሁ መግለጫ፣ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ በትግራይና በፌዴራል መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት መሻሻሉንና ተቀራርቦ መሥራት መጀመሩን ተናግረዋል።

በሰላም ስምምነቱ መሠረትም በሕወሓት ላይ የተጣለው የአሸባሪነት ፍረጃ፣ በፌዴራል መንግሥት መነሳቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መመሥረቱን፣ የፌዴራል መንግሥት አቋርጦት የነበረውን በጀት በተወሰነ ደረጃ መልቀቅ መጀመሩን፣ በዚህም ባለፉት ወራቶች የትግራይ ሕዝብ ችግሮችን ማቅለል እንደተቻለ ተናግረዋል።

ነገር ግን በፕሪቶሪያው ስምምነት ውስጥ ያልተፈጸሙ ትልልቅ ጉዳዮች፣ ለአብነትም የኤርትራ ጦርና የአማራ ክልል ታጣቂዎች አሁንም ድረስ በኃይል ከያዟቸው የትግራይ ግዛቶች አልወጡም ብለዋል።

በዚህም ምክንያት የተፈናቀሉ የትግራይ ነዋሪዎችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንዳልተቻለና ይህ ጉዳይ አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚሻ አሳስበዋል።

ደብሪፂዮን መግለጫ በሰጡ በማግስቱ ማክሰኞ ግንቦት 15 ቀን በትግራይ በርካታ በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰዎች ሰላማዊ ሠልፎች የተካሄዱ ሲሆን፣ በተካሄዱት ሠልፎችም በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ እንዲሁም የኤርትራና የአማራ ክልል ተዋጊዎች ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡና የፕሪቶሪያው ስምምነት፣ በስምምነቱ መሠረት ይፈጸም የሚሉ ጥያቄዎች ተስተጋብተዋል።

ሕወሓት ወደ ትጥቅ ፖለቲካ በመግባቱ ምክንያት በምርጫ አዋጁ ቁጥር 1162 መሠረት ከፖለቲካ ፓርቲነት እንደተሰረዘ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የገለጸ ሲሆን፣ ውሳኔው ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትም ሆነ ከሽብርተኝነት ፍረጃው ጋር እንደማይገናኝ አሳውቋል። ሕወሓትን ከተሰረዘ በኋላ ሕጋዊ ሰውነት የሚያገኝበት በሕግ የተቀመጠ አሠራር ባለመኖሩ ጥያቄውን ለመቀበል እንደተቸገረና ያለው ምርጫ እንደ አዲስ ምዝገባ ጥያቄ ማቅረብ ነው ሲል ቦርዱ ማሳወቁ ይታወሳል።
3.9K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 08:39:26 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned «ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት…»
05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-25 08:39:19 ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ከግንቦት 1 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው ለቤተ ክርስቲያናችን አንድነት፣ ለሐዋርያዊ ተልእኮ መስፋፋት እና መንፈሳዊ ዕድገት ትኩረት በመስጠት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፎአል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
1. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የሰላም ጉልላት እንደመሆኗ ሰላም መሠረታዊ ተልእኮዋ ነው፡፡ ስለዚህ ወቅታዊውን ችግር ታሳቢ በማድረግ በመላው አገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፤ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ካሉ ተቋማት ጋራ የሚሠራ፣ በሀገሪቱ መንግሥትም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የሚኖረው የሰላም ኮሚቴ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰይሟል፡፡
2. በትግራይ ክልል በሚገኙት አህጉረ ስብከት ተቋርጦ የነበረው መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ግንኙነትን በተመለከተ ቀደም ሲል በቅዱስ ሲኖዶስ ተሠይሞ በሥራ ላይ የሚገኘው ልዑክ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲቀጥል የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ተልዕኮውን እንዲፈጽም ምልዓተ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡
3. በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወገኖቻችን ያሉበትን ከፍተኛ ችግር ታሳቢ በማድረግ አስቸኳይ የሆነ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ሃያ ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
4. በወቅታዊ ችግር ምክንያት በመላው ሀገራችን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን ሁሉ በአጠቃላይ ችግሮቹን በጥናት በመለየት፣ ቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን ልጆቿን በማስተባበር ሁለንተናዊ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ የማጽናናትና የመጎብኘት መርሐ-ግብሮች እንዲደረጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
5. መቀሌ የሚገኘው የቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የሠራተኞችን ደመወዝና የሥራ ማስኬጃ በጀት እንዲለቀቅና በ2016 በጀት ዓመት ተማሪዎችን በመቀበል መደበኛ የሆነ የመማር ማስተማሩ የሥራ ሂደት እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
6. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመጪው ዐሥር ዓመታት የመንፈሳዊ እና ዘላቂ ልማት ግብ መሪ ዕቅድ በማጽደቅ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅሮች ተግባራዊ እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡
7. የቤተ ክርስቲያናችን ቀደምት አበው በቅድስት ሀገረ ኢየሩሳሌም ገዳማት እንዲስፋፉ ሁሉ የነሱን አሰረ ፍኖት በመከተል በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ ካልፎርኒያ ግዛት የተቋቋመው ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም እንዲጠናከር፤ በተጨማሪም በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የአስተዳደር፣ የጽሙና፣ የትምህርትና የምርምር ማዕከል እንዲመሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ አስተላልፏል፡፡
8. በኦሮምያ ክልል በሚገኙ አህጉረ ስብከት ተፈጥሮ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በአህጉረ ስብከትና በአብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት ስለተቋረጠ፣ በርካታ ምእመናንና ካህናት በእስርና እንግልት ላይ ስለሚገኙ በዚሁ መነሻነት ችግሮች እንዲቀረፉና ወደ መደበኛው የአሠራር መዋቅር እንዲመለስ ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን በመሠየም ከፌዴራልና ከኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመወያየት ችግሮች እንዲፈቱ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
9. የመንፈሳዊ ኮሌጆች መከፈት እና የአብነት ትምህርት ቤቶችን ማጠናከር በተመለከተ በኢሉ አባቦራ የመቱ ፈለገ ሕይወት የነገረ መለኮት መንፈሳዊ ኮሌጅ እንዲከፈት የተፈቀደ ሲሆን በሌሎች አህጉረ ስብከት ሊከፈቱ የታሰቡ ኮሌጆችን እና የአብነት ት/ቤቶችን መሠረታዊ ጥናት ተደርጎ ለ2016 ዓ.ም. የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርብ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
10. ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ክፍት በሆኑና በተደራቢነት በተያዙ፣ ጉልህና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው በኦሮምያ ክልልና በደቡብ ክልል ባሉ አህጉረ ስብከት ላይ 9 ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ አስመራጭ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ወደፊትም ተደርበው በተያዙና አስፈላጊ በሆኑ አህጉረ ስብከት እንደአስፈላጊነቱ በመንበረ ፓትርያርክ ተጠንቶ እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
በመጨረሻም በሀገራችን በአንዳንድ ቦታዎች የሚታዩትን አላስፈላጊ ግጭቶች የዜጐች መፈናቀል፣ ስደት ተወግዶ ሁሉም ዜጋ በሀገሩ በእኩልነት፣ በሰላምና በፍቅር ተከባብሮ በአንድነት እንዲኖር፤ ለማድረግ ግጭቶችና አለመግባባቶች በውይይት እንዲፈቱ ቤተ ክርስቲያን የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡ እንዲሁም በመላው ዓለም ጦርነት ባለባቸው ሀገራት ሁሉ ሰላም እና ዕርቅ እንዲሰፍን በመመኘት እና በመጸለይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ሲያካሂድ የቆየውን ጉባኤ በጸሎት አጠናቋል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም አዲስ አበባ – ኢትዮጵያ
3.4K views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-24 12:27:42 "19 መስጅዶች ፈርሰዋል::"

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአዲሱ የሸገር ሲቲ ከተማ አስተዳደር ከረመዳን 1 ጀምሮ የፈረሱ መስጂዶች ቁጥር 19 መድረሳቸውን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ትናንት ግንቦት 15/2015 አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ በከተማ አስተዳደሩ እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ ያወገዘ ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜያት ለሚመለከተው አካል አቤቱታውን ቢያቀርብም በጉዳዩ ላይ እስካሁን በጎ ምላሽ አለማግኘቱን በማንሳት ድርጊቱ አሁንም በአስቸኳይ እንዲቆም በድጋሚ ጠይቋል።በመላው ኦሮሚያ የመጭው ጁምዓ ኹጥባዎች መስጂድ ፈረሳውን የተመለከቱ እንዲሆኑ መልዕክት ተላልፏል።
3.7K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 18:59:02 ሲሚንቶ በቴሌብር……

ሲሚንቶ እንደ ነዳጅ ወደ ዲጅታል ግብይት ሊገባ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።ሂደቱ ሲሚንቶ በተተመነለት ዋጋ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ፣ ስርጭቱ ከፋብሪካው ጀምሮ እስከ ተጠቃሚ ድረስ ያለውን ሰንሰለት ለመከታተል፣ የዘርፉን የግብይት ሥርዓት በማዘመን የግብይት ሰንሰለቱን ለማሳጠር እና ከህገወጥ ደላሎች የፀዳ የንግድ ሥርዓትን ለመዘርጋት ያግዛል ተብሏል።
4.0K views15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 18:58:18 የአማራ ብሄረሰዊ ንቅናቄ አመራር አቶ ጋሻው መርሻ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸው ተሰምተሠቷል።ከአብን በመንግስት መዋቅር ሹመት ካገኙት ዶ/ር በለጠ ሞላ፣የሱፍ ኢብራሂም እና አቶ ጣሂር መሀመድን ጨምሮ 4ኛ ሰው ሆነዋል።
3.8K views15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 09:38:00 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned «<<ድርጅታቸው በድጋሚ ሕጋዊ ፓርቲ ለመሆን የምዝገባ ጥያቄ አያስገባም።ፓርቲያችን በሌላ መንገድ ካልፈረሰ በስተቀር ወደፊትም ባለበት ይቀጥላል።>> የሕወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል ለክልሉ ሚዲያ»
06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 09:37:52 <<ድርጅታቸው በድጋሚ ሕጋዊ ፓርቲ ለመሆን የምዝገባ ጥያቄ አያስገባም።ፓርቲያችን በሌላ መንገድ ካልፈረሰ በስተቀር ወደፊትም ባለበት ይቀጥላል።>>
የሕወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል ለክልሉ ሚዲያ
4.3K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-23 09:37:01 ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝና በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ "የተናጥል ርምጃ ወስዳለች" በማለት የዓረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ "ኾን ተብሎ እውነታውን የመቀየር" አካሄድ ነው ስትል ኢትዮጵያ አውግዛለች።

የሊጉ መግለጫ "የግብጽን ጠባጫሪ አቋም የሚያንጸባርቅ" መኾኑን የገለጸችው ኢትዮጵያ፣ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የኾነ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ቁርጠኛ መኾኗን አረጋግጣለች።

ኢትዮጵያ ጨምራም፣ ግብጽ በዓረብ ሊግ አማካኝነት ኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር መሞከሯ "ቀናዒነት እንደሌላት" ያሳያል ብላለች።

የሊጉ አባል የኾኑ የአፍሪካ አገራት ከሊጉ ውሳኔ ራሳቸውን እንደሚያገሉ እምነቷ መኾኑንም ኢትዮጵያ ገልጻለች።(ዋዜማ)
4.3K views06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ