Get Mystery Box with random crypto!

Amba Digital - አምባ ዲጂታል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ambadigmedia — Amba Digital - አምባ ዲጂታል A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ambadigmedia — Amba Digital - አምባ ዲጂታል
የሰርጥ አድራሻ: @ambadigmedia
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.42K
የሰርጥ መግለጫ

አምባ ዲጂታል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ፣ ዘገባዎችና አተያዮችን የሚያቀርብ ዲጂታል የሚዲያ መድረክ ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 10:05:47
የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ነሐሴ 27፣ 2014 ― የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ የነበሩት አቶ ውብሸት አያሌው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደሩ መረጃ ከሆነ ተቀዳሚ ከንቲባ የነበሩት አቶ ውብሸት አያሌው የተገደሉት ትላንት ነሐሴ 26፣ 2014 ወደ ቤታቸው ሲገቡ ነው፡፡

አቶ ውብሸት ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በሥራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዮ ተቋማት በባለሞያነትና በሥራ ኃላፊነት አሳልፈዋል፡፡

ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት የነበሩት አቶ ውብሸት አያሌው በከተማዋ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት የቀብር ሥርዐታቸው ይፈጸማል ተብሏል፡፡

ዝርዝሩን ያንብቡ https://ambadigital.net/2022/13899/
13 views07:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 19:28:55 ሕወሓትንያሳሰቡት ፈረንጅ አሜሪካ እና ጦርነቱ መንግሥት አዲስ መመሪያ አወጣ


737 views16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 12:37:23 መንግሥት እና ሕወሓት በአስቸኳይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ አሜሪካ ጥሪ አቀረበች

አምባ ዲጂታል፤ ሐሙስ ነሐሴ 26፣ 2014 ― መንግሥት እና ሕወሓት በአስቸኳይ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ አሜሪካ ጥሪ ያቀረበችው በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ኃላፊዋ አንቶንዮ ብሊንከን በኩል ነው፡፡

ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ማስታወሻ፤ ተፋላሚ ወገኖች ወታደራዊ እንቅስቃሴውን አቁመው ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ያለፉትን ወራት በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ጋብ ብሎ የቆየው የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት ጦርነት ካገረሸ ዘጠኝ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ በትዊተር የጻፉት አንቶንዮ ብሊንከን፤ ‹‹ጦርነቱ እንደገና መቀስቀሱ እና አደጋ ላይ የሚጥለው የሰው ሕይወት በእጅጉ ያሳስበናል›› ብለዋል።

ተባብሶ በቀጠለው ጦርነት መንግሥት ትላንት ነሐሴ 25፣ 2014 ባወጣው መግለጫ፤ ሕወሓት በወልቃይት አቅጣጫና በሱዳን ድንበር እንዲሁም በዋግ ጥቃት መክፈቱን ገልጧል፡፡ በአንጻሩ የሕወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ መንግሥት ከኤርትራ ጦር ጋር በመሆን በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በኩል አድያቦ አካባቢ ዛሬ ነሐሴ 26፣ 2014 ማለዳ በአራት አቅጣጫ ጥቃት እንደከፈቱባቸው ገልጸዋል፡፡
የአቶ ጌታቸውን ክስ በተመለከተ ከመንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም፡፡ ሆኖም የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ሐሙስ ነሐሴ 26 ‹‹ሕወሓት ወረራውን እያስፋፋ መጮሁን ቀጥሎበታል›› በሚል ርእስ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በዚሁ መግለጫ ላይ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በለኮሰው እና ዛሬም እያስፋፋው ባለው እሳት ንጹሐን እየተገደሉ ነው፤ ሕዝብ እየተፈናቀለ እና ንብረትም እየወደመ ነው ያለው መንግሥት፤ ‹‹ሕወሓትን ከአገር አጥፊነት ተግባሩ የማስቆም ግዴታ በኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ላይ ወድቋል›› ሲል አስፍሯል፡፡

በሌላ በኩል መንግሥት በዚሁ መግለጫ ላይ ለሰላማዊ አማራጮች ያደረግኳቸው ጥረቶች ‹‹እየመከኑ ባሉበት ሁኔታ›› ሕወሓትን መጫን ሲገባቸው ‹‹ሁለቱ ወገኖች›› በሚል የሚወጡ መግለጫዎችን ‹‹ከእውነታው ያፈነገጡ በመሆናቸው›› ተቀባይነት የላቸውም ብሏል፡፡

ባለፈው ዓመት ጥቅምት መጨረሻ ላይ ትግራይ ውስጥ የሚገኘውን የመከላከያ የሰሜን እዝ መመታት ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት የአስር ሺሕዎችን ሕይወት በመቅጠፍ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሏል፡፡
1.0K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 11:47:12 የረፋድ ዜናዎችን ይከታተሉ

1.0K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:56:10 ኦፌኮ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተማጽኖ አቀረበ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ነሐሴ 25፣ 2014 ― የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ ‹‹ግጭት ከሚያባብሱ ንግግሮች በመታቀብ ችግሩን ለማርገብ እና ለመፍታት›› እንዲተባበር ተማጽኖ ያቀረበው ዛሬ ረቡዕ ነሐሴ 25፣ 2014 ባወጣው ወቅታዊ መግለጫ ነው፡፡

ፓርቲው በዚህ ተማጽኖው ለገዥው ፓርቲ፣ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች እና አክቲቪስቶች ተመሳሳይ መልእክት ሰዷል፡፡

ኦፌኮ በዛሬው መግለጫው፤ ‹‹ሐገራችንን ለከፍተኛ ሰብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ኪሳራ የዳረጋት›› ነው ባለው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ማገርሸት እና ‹‹በኦሮሚያ የቀጠለው ግጭት በመባባሱ›› ማዘኑን ገልጧል፡፡

የፓርቲው መግለጫ ጦርነት ‹‹ውስብስብ›› ነው ላለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ችግር መፍትሔ ሊሆን እንደማይችል አጽንኦት ሰጥቶት አልፏል፡፡ አክሎም እነዚህ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉት ‹‹በእውነተኛ እና ሁሉን አቀፍ ድርድር ብቻ›› መሆኑን የገለጸው ኦፌኮ፤ በሁሉም ወገን የሚገኙ ተፈላሚ ኃይሎች ‹‹ግጭቱን በማብረድ ሰለማዊ መፍትሔ እንዲሹ›› ጠይቋል፡፡

ኦፌኮ በመግለጫው ክልላዊ እና ዓለም አቀፍ አሸማጋዮች አንጻራዊ መረጋጋት በነበረባቸው ባለፉት ወራት ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር ጠረጴዛ ለማምጣት እና አጠቃላይ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማስፈን መጠቀም ባለመቻላቸው ‹‹ከፍተኛ ፀፀት›. እንደተሰማው የገለጸ ሲሆን፣ አሁንም በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ‹‹ተጨማሪ ሞት እና የዜጎችን መከራ ለማስቀረት›› ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ‹‹በንቃት እና በተቀናጀ መልኩ እንዲረባረብ›› ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል ኦፌኮ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኦሮሚያ ተስፋፍቷል ያለውን ጦርነት ‹‹ለመፍታት ቀርቶ እውቅና ለመስጠት አለማቻሉን›› አሳስቦኛል ብሏል፡፡ በክልሉ በተለይም በግጭት እና በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ያለው ሰብአዊ ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መድረሱን በመግለጽ፤ ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ‹‹እየተባባሰ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እና ሰላማዊ በሆነ መልኩ በድርድር እንዲፈታ›› ሁኔታዎችን ያመቻች ብሏል፡፡

ላለፉት አምስት ወራት ጋብ ብሎ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ካገረሸ ዛሬ አንድ ሳምንት አስቆጥሯል፡፡
426 views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:08:58 ሳፋሪኮም በስድስት ሳምንታት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተባለ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ነሐሴ 25፣ 2014 ― በኢትዮጵያ ሁለተኛውን የቴሌኮም ፈቃድ በጨረታ አሸንፎ ሥራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ ሳፋሪኮም በስድስት ሳምንታት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሏል፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ለራሱ የመጀመሪያ የሆነውን የቴሌኮም አገልግሎት ሰኞ ነሐሴ 23፣ 2014 በድሬዳዋ ከተማ በራሱ መሠረተ ልማት ማስጀመሩ ይታወቃል፡፡ ሳፋሪኮም በቀጣይም ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሌሎች የአገሪቱ ከተሞች እንደሚጀምር ገልጧል፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሳፋሪኮም በዚሁ መሠረት በመጪዎቹ ስድስት ሳምንታት ውስጥ በተመሳሳይ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በአዲስ አበባ ከተማ ይጀምራል፡፡

አንዋር ሶሳ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ሲካሄድ የነበረው የመሠረተ ልማት ስምምነት በቶሎ ባለማጠናቀቁ አገልገሎቱን ለማስጀመር ጊዜ እንደወሰደባቸውም ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ እንደገለጹት፣ ኩባንያው እስከ ሚያዚያ 2015 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን 25 በመቶ የኅብረተሰብ ክፍል የሚሸፍን አገልግሎት እንዲያቀርብ ውል ገብቷል፡፡ ኩባንያው በዚሁ በተጠቀሰው ጊዜ የሚጠበቅበትን ካላሟላ ኦዲት ተደርጎ በገባው ውል መሠረት ቅጣት ይጣልበታል፡፡ ይሁን አንጂ የቴሌኮም ኩባንያው አሁን በተሳካ ሁኔታ ሥራውን እያከናወነ እንደሆነ አቶ ባልቻ ገልጸዋል፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንደሚሉት ኩባንያቸው የዋጋ ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን የቴሌኮም አገልግሎት እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ በ3G እና በ4G ኔትወርኮች የጀመረ ሲሆን፣ ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

በድሬዳዋ ከተማ አገልግሎት በጀመረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሙከራ ኔትወርክ ደንበኞች ዳታ መጠቀም፣ ጥሪዎችና የጽሑፍ መልዕክቶችን ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ከኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ጋር መለዋወጥ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ጥሪዎችን ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ ሳፋሪኮም በደቂቃ 50 ሳንቲም እንደሚያስከፍልም ታውቋል፡፡
የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም ኦፕሬተር ሆኖ በኢትዮጵያ የተመዘገበው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ላገኘው የአገልግሎት ፈቃድ 850 ሚሊዮን ዶላር ለመንግሥት መክፈሉ ይታወሳል፡፡
583 views09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:49:32 ሱዳን በአገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደር መጥራቷ ተዘገበ

አምባ ዲጂታል፤ ረቡዕ ነሐሴ 25፣ 2014 ― ጎረቤት ሱዳን በአገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮን ጠርታለች የተባለው ከሰሞኑ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከሱዳን በኩል የጦር መሣሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል ሲገባ መትቼ ጥዬዋለሁ ካለው አውሮፕላን ጋር በተገናኘ ነው፡፡

ሱዳን ትሪቡን እንደዘገበው፤ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሰኞ ነሐሴ 23፣ 2014 ከአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ ጉዳዩ የተናገሩት የአገሪቱን ሹማምንት አስቆጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የዘመቻዎች ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ነሐሴ 18፣ 2014 ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሱዳን አልፎ ለሕወሓት የጦር መሣሪያ በመጫን የኢትዮጵያ አየር ክልልን ጥሶ የገባ አንድ አውሮፕላን መትቶ መጣሉን ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ወዲያው ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጀኔራል ይልማ መርዳሳ፤ ከሱዳን በኩል የጦር መሣሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ ክልል ሲገባ ተመትቶ ተጥሏል ያሉት አውሮፕላን ሩስያ ሠራሹ አንቶኖቭ መሆኑን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ጀነራሉ አውሮፕላኑ ‹‹ፍቃድ ያልተሰጠው እና በተከለከለ የበረራ መስመር በኩል የገባ›› እንደነበርም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ማብራሪያ ተከትሎ የሱዳን ጦር ሠራዊት ኢትዮጵያ በአገሪቱ በኩል ጦር መሣሪያ ጭኖ ወደ ትግራይ ሲገባ መትቼ ጣልኩ ካለችው ክስተት ጋር ምንም ግንኙነት የለኝም ሲል በቃል አቀባዩ በኩል ለአሜሪካው ብሉምበርግ በሰጠው ቃል አስተባብሏል፡፡

በአውሮፕላኑ የጦር መሣሪያ ሊጓጓዝለት ነበር የተባለው ሕወሃትም በቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ በኩል በተመሳሳይ የመንግሥትን መረጃ ‹‹ሐሰት ነው›› ብሎታል፡፡

አሁን በአምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ንግግር ተቆጥቷል የተባለው የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የቀረበውን ክስ ‹‹መሠረተ ቢስ›› በማለት ያጣጣለው ሲሆን፣ አምባሳደሩ ጉዳዩን ለመገናኛ ብዙኃን መናገራቸውንም ዲፕሎማሲያዊ አካሄድን የጣሰ ነው ብሎታል፡፡

እንደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል መረጃ መትቼዋለሁ ያለው አውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር ክልል ውስጥ ተመትቶ የወደቀው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ኘሐሴ 17፣ 2014 ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡፡ ሶቪዬት ኅብረት ሠራሽ የሆነ አንቶኖቭ-26 40 ወታደሮችን ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው የመጫን አቅም አለው ተብሏል፡፡
590 views08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 11:31:46 ውድ ቤተሰቦች እንዴት አረፈዳችሁ?
የረፋድ መረጃዎችን ይዘን ቀርበናል፡፡ በዚህ የመረጃ ጊዜ ከአገር ቤት ወልዲያ እና መቐለ እንደርሳለን….
ከውጭ ደግሞ የጎርባቾቭን ስንብት ተመልክተናል፡፡ ይከታተሉን፡፡ አብራችሁን ስለምትሆኑ ደስ ይለናል….


604 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 17:50:13

847 views14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:54:49 የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በፀጥታ ስጋት ምክንያት አዳዲስ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አምባ ዲጂታል፤ ማክሰኞ ነሐሴ 24፣ 2014 ― በአማራ ክልል የሚገኘው የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በፀጥታ ስጋት ምክንያት አዳዲስ ውሳኔዎችን ያሳለፈው በፀጥታ ምክር ቤቱ አማካኝነት ነው፡፡

በዚህም በከተማ አስተዳደሩ በተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚኖር ተፈናቃይ ከምሽቱ 12 በኋላ ወደ መጠለያ ጣቢያውም ሆነ ወደ ከተማው መግባት ክልክል የተደረገ ሲሆን፣ በከተማው የሚገኙ የባጃጅ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ከምሽቱ በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉና ይህን ሲያደርግ የተገኘ ባለባጃጅ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በከተማው የሚገኙ መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች ምሽት ጭፈራ ቤት እስከ ምሸት 2 ሰአት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የወሰነው ምክር ቤቱ፤ በከተማው የሚገኙ የንግድ ቤቶች የምርት የዋጋ ጭማሪ ማድረግን በጥብቅ ከልክሏል፡፡

የጦር መሣሪያን በተመለከተም ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ኃይሎች ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ፈፅሞ ተከልክሏል፡፡ በከተማው ከመንግስት ዕውቅና ውጭ የሚደረጉ ማናቸውም አይነት ውይይቶችና ስብሰባ ማድረግ በጥብቅ ተከልክሏል፡፡

በሌላ በኩል የከተማው ባለሆቴሎች እና አልጋ አከራዮች ማንነቱ ያልታወቀ የታጠቀ ግለሰብ በድርጅታችሁ ሲያጋጥማችው ለህግ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ ያለው የፀጥታ ምክር ቤት፤ የቤት አከራይዎች የሚያከራዩትን ግለሰብ ማንነትት መታወቂያ በመጠየቅ ለይተው እንዲያከራዩ እንዲሁም የተከራዩንም መረጃ በፎርም በመሙላት ለከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንዲያሳውቁ አሳስቧል፡፡

ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ነሐሴ 18፣ 2014 ያገረሸውን የፌዴራል መንግሥት እና ሕወሓት ጦርነት ተከትሎ ከደብረ ብርሃን ከተማ ውጪ ሌሌችም የአማራ ክልል ከተሞች አስገዳጅ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው ይታወቃል፡፡

በፀጥታ ስጋት ምክንያት አዳዲስ ውሳኔዎችን ያሳለፈችው የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፤ ከፌዴራል መንግሥቱ መቀመጫ አዲስ አበባ ከተማ በ120 ኪሎ ሜትር ርቀት እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡
952 views12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ