Get Mystery Box with random crypto!

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተገደሉ አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ነሐሴ 27፣ 2014 ― የሸዋሮ | Amba Digital - አምባ ዲጂታል

የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ተገደሉ

አምባ ዲጂታል፤ ዐርብ ነሐሴ 27፣ 2014 ― የሸዋሮቢት ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ የነበሩት አቶ ውብሸት አያሌው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደሩ መረጃ ከሆነ ተቀዳሚ ከንቲባ የነበሩት አቶ ውብሸት አያሌው የተገደሉት ትላንት ነሐሴ 26፣ 2014 ወደ ቤታቸው ሲገቡ ነው፡፡

አቶ ውብሸት ወደ ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በሥራ ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት በቀወት ወረዳ አስተዳደር በተለያዮ ተቋማት በባለሞያነትና በሥራ ኃላፊነት አሳልፈዋል፡፡

ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት የነበሩት አቶ ውብሸት አያሌው በከተማዋ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት የቀብር ሥርዐታቸው ይፈጸማል ተብሏል፡፡

ዝርዝሩን ያንብቡ https://ambadigital.net/2022/13899/