Get Mystery Box with random crypto!

Amba Digital - አምባ ዲጂታል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ambadigmedia — Amba Digital - አምባ ዲጂታል A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ambadigmedia — Amba Digital - አምባ ዲጂታል
የሰርጥ አድራሻ: @ambadigmedia
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.42K
የሰርጥ መግለጫ

አምባ ዲጂታል በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ፣ ዘገባዎችና አተያዮችን የሚያቀርብ ዲጂታል የሚዲያ መድረክ ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-30 14:57:50 ከወራት በፊት ወደ ትግራይ ክልል ገብተዋል የተባሉ የጦር አውሮፕላኖች ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ https://fb.watch/fdJaWda4iW/
939 views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:05:13

966 views11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:46:38

1.0K views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 16:58:30

1.1K views13:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:39:01

1.1K views12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 11:15:27
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ መጀመሩን አሳወቀ


አምባ ዲጂታል፤ ሰኞ ነሐሴ 23፣ 2014 ― ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 23፣ 2014 ተከታታይ የደንበኞች የኔትወርክ አገልግሎት ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ መጀመሩን አስታውቋል።

ኩባንያው የጀመረው የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ሂደት መሆኑ ተነግሯል።

በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2ጂ፣ 3ጂ እና 4ጂ ኔትወርኮች የሚካሔድ ሲሆን፣ ደንበኞች በ07 በሚጀምረው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ መስመር የስልክ ቁጥሮቻቸውን መርጠው ሲም ካርድ መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል።


ደንበኞች የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሲም ካርዶች የድርጅቱ መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች ማግኘት እንደሚችሉ እና ኔትወርኩን ለአንድ ወር ያህል እንዲሞክሩት የሚረዳ የደንበኝነት ማስጀመሪያ የዳታ፣ የድምጽ እና የጽሑፍ መልዕክቶች ጥቅል ያገኛሉ ተብሏል፡፡

የደንበኝነት ማስጀመሪያ ጥቅሉ በሚያልቅበት ጊዜ ደንበኞች የአየር ሰዓት ከሽያጭ ማዕከላት ወይም መለያ ከተለጠፈባቸው መደብሮች እና ሱቆች በመግዛት መሙላት እና አገልግሎቱን በቀጣይነት መጠቀም እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
1.1K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 10:23:20 የሰኞ ረፋድ መረጃችን ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ማገርሸት በኋላ የትግራይን ክልል የሚያዋስነው የአሚራ ክልል ከተሞች የወሰዷቸውን እርምጃዎች ይቃኛል። ይከታተሉን

1.0K views07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 16:54:47 ኢትዮጵያ ከአጎዋ በመታገዷ ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ከአምስት ሺሕ ሠራተኞች ተሰናበቱ

አምባ ዲጂታል፤ እሑድ ነሐሴ 22፣ 2014 ― የአሜሪካ መንግሥት ኢትዮጵያን ከአጎዋ (የአፍሪካ ነፃ የገበያ ዕድል) ተጠቃሚነት ማገዱን ተከትሎ ምርታቸውን ወደ አሜሪካ ሲልኩ የነበሩ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኙ አምራቾች በገበያ ዕጦት ያሰናበቷቸው ሠራተኞች ቁጥር ከአምስት ሺሕ በላይ ማለፉ ተገልጿል።

ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌደሬሽን (ኢሰማኮ) የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ኢትዮጵያ የአጎዋ ዕድል ተጠቃሚ እንዳትሆን በአሜሪካ መንግሥት ዕገዳ ከተጣለባት ወዲህ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ አምስት የጨርቃ ጨርቅ አምራቾች በገጠማቸው የገበያ ዕጦት ሠራተኞችን መቀነሳቸውንና በመቀነስ ላይ ይገኛሉ፡፡

በአጎዋ ዕድል ተጠቅመው ወደ አሜሪካ ከቀረጥ ነፃ ምርቶቻቸውን ሲያስገቡ ከነበሩ ኩባንያዎች ውስጥ ሁለቱ ሙሉ በሙሉ ሥራ ያቆሙና ሠራተኞቻቸውን ያሰናበቱ ሲሆን ሦስቱ ደግሞ ሠራተኞቻቸውን ቀንሰው ከማምረት አቅማቸው በታች እያመረቱ ይገኛሉ።

ሙሉ በሙሉ ሥራ ካቆሙት ኩባንያዎች ውስጥ ፒቪኤች 1,400 እና ቻርቸርስ 22 ሠራተኞች ነበሯቸው፡፡ ቤስት፣ ኤፔክና ኳድራንት የተባሉት ኩባንያዎች ደግሞ ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ ባያቆሙም እንደ ቅደም ተከተላቸው 3,000፣ 1,200 እና 161 ሠራተኞች እንደቀነሱ ሪፖርተር ጋዜጣ መረጃውን ጠቅሶ ዘግቧል።


ከኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ አልባሳትና የመሳሰሉት ሠራተኞች ኢንዱስትሪ ፌዴሬሽን ያገኘው ተጨማሪ መረጃ እንደሚያመለክተውም፣ ከአጎዋ ተጠቃሚነት ዕገዳ በኋላ በተለይ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያሉ ኩባንያዎች ችግር ውስጥ መሆናቸውንና አማራጭ ገበያ በማጣታቸው ተጨማሪ ሠራተኞች ሊቀነሱ ይችላሉ የሚል ሥጋት አይሏል፡፡ 

ከገበያ ዕጦት ጋር በተያያዘ እነዚህ ኩባንያዎች በአሜሪካ መንግሥት የተጣለው ክልከላ ካልተነሳ ወይም አዲስ ገበያ የማያገኙ ከሆነ ተጨማሪ የሠራተኞች ቅነሳ ሊያደርጉ የሚችሉ መሆኑንም የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ አንገሶም ገብረ ዮሐንስ ሥጋት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ለዚህም እንደማሳያ ኤፔክ የተባለው ኩባንያ ተጨማሪ 100 ሠራተኞች ለመቀነስ እንደሚችል በዚህ ሳምንት ማስታወቁን ጠቁመዋል፡፡ አንፑቺንና ሔላ ሱብሪን የተባሉት ሁለት ኩባንያዎች ደግሞ 400 ለሚደርሱ ሠራተኞቻቸው ከክፍያ ጋር አስገዳጅ የዓመት ፈቃድ መስጠታቸውን ጠቅሰው፣ ይህም በቀጣይ ምን ሊከተል እንደሚችል አመላካች መሆኑን ገልጸዋል። 

ይህ አካሄድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን የሥራ ዋስትና እያሳጣ በመሆኑ ጉዳዩ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነባቸው የገለጹት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት  ኮንፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ ኢትዮጵያ ከአጎዋ ተጠቃሚነት እንድትወጣ በመደረጉ በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ወደ ስድስት ሺሕ የሚጠጉ ሠራተኞች ሥራ ማሳጣቱን ገልጸዋል።
1.2K views13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 17:56:57 የቅዳሜ አመሻሽ ዜናዎችን ያግኙ

592 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:49:14 ሕወሓት ኃይሉን በማሰባሰብ ወደ አማራ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መንግሥት ገለጸ

አምባ ዲጂታል፤ ቅዳሜ ነሐሴ 21፣ 2014 ― ሕወሓት ኃይሉን በማሰባሰብ ወደ አማራ እና አፋር ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መንግሥት የገለጸው ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 21፣ 2014 ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

በኮሚኒኬሽን አገልግሎት በኩል በወጣው መግለጫ፤ ሕወሓት ኃይሉን በማሰባሰብ ወደ አማራ እና አፋር እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ‹‹ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የንብረት ማውደም፣ መሠረት ልማት የማፈራረስና የጭካኔ ተግባራትን ለመፈጸም›› መሆኑን ገልጧል፡፡

መንግሥት ‹‹ግድያ፣ ማፈናቀል፣ የንብረት ማውደም፣ መሠረት ልማት የማፈራረስና የጭካኔ ተግባራትን ለመፈጸም›› ሕወሓት ወደ ሁለቱ ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ነው ስለማለቱ ቡድኑ የሰጠው ምላሽ የለም፡፡

ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ በትግራይ ውስጥ ተጀምሮ ኋላ ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት ላለፉት አምስት ወራት በተደረገ የተኩስ አቁም ስምምነት ጋብ ብሎ ቆይቶ ነበር፡፡ ሆኖም መንግሥትና የሕወሓት አመራሮች ጦርነቱን በውይይት ለመፍታት ድርድር ይጀምራሉ ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ከአራት ቀናት በፊት ጦርነቱ አገርሽቷል፡፡

ጦርነቱን ዳግም በማስጀመር ሁለቱም አካላት እየተወነጃጀሉ ሲሆን፣ በአዲሱ ግጭት ንጹሐን ሰለባ መሆናቸው እየተነገረ ይገኛል፡፡

የሕወሓት ኃይሎች በአፋር በኩል ንጹሐን ላይ ጥቃት መሰንዘራቸው ሲነገር፤ የሕወሓት ኃይሎች በበኩላቸው የፌዴራል መንግስቱ ወደ መቐለ ከተማ የአየር ጥቃት ሰንዝሮ ንጹሐንን ገድለዋል ብለዋል፡፡ የፌዴራል መንግስቱ በበኩሉ የዐየር ጥቃቱ የሕወሓት አቅሞችን ኢላማ ያደረገ ነው ብሏል፡፡

አዲስ ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረትና አሜሪካ የጦርነቱ ማገርሸት እንዳሳሰባቸውና ተፋላሚ ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ ጥሪ አቅርበዋል።
825 views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ