Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-04-21 12:00:39 የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች የማረጋገጫ ምልክት ተነሳ።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ከሆኑ ሰንበትበት ብሏል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ይጠቀሳል።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

ከእነዚህ ውስጥም የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ሲጠቀስ፥ የሌሎች በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች ተሰጥቶ የነበረው የማረጋገጫ ምልክት ተነስቷል። (ለአብነት የተጠቀሱ ገጾችን በምስሉ ይመልከቱ)

በርካቶች ይሄንን ውሳኔ በተመሳሳይ ስም የሚከፈቱ "የማረጋገጫ ምልክት" የሚኖራቸው አካውንቶች እንዲኖሩ እድሉን ይከፍታል በሚል የተቃወሙት ቢሆንም ውሳኔው ግን ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ይህም ሀሰተኛ መረጃን ያባብሳል ተብሎ ተሰግቷል። በተለይ አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቱን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ ለአጭበርባሪዎች (Scammers) በር በመክፈት በርካቶችን ሊጎዳ ይችላል።

የገጾችን ትክክለኛነት ለማሳየት የምንጠቀምበት ይህ የማረጋገጫ ምልክት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጫነት ብዙም ጥቅም የሚኖረው አይመስልም።

የገጹ ተከታይ ብዛት እንደ ማረጋገጫ መውሰድ ብንችልም እንደ ሀገራችን የሀሰተኛው ገጽ ተከታይ ቁጥር ከትክክለኛው በሚበልጥበት ሁኔታ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም አዳጋች ያደርገዋል።
2.2K views09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:37:49 ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News pinned a photo
19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:37:41 አዲስ አበባ

ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ መንገዶች ይዘጋሉ።

1444ኛው የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል የኢድ ሶላት (በአዲስ አበባ ስታዲዮም እና አካባቢው) ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቅ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረኃይል ይፋ አድርጓል።

አሽከርካሪዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መንገዶች የሚዘጉ መሆኑን በማወቅ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ ብሏል።

የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

- ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችል ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

- ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ፤

- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

- ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውሃ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት ፤

- ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ  ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ ፤

- ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ እንዲሁም ለከባድ መኪና አጎና ሲኒማ አካባቢ #ይለፍ_ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።
515 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 22:37:13
ዒድ ሙባረክ

የሸዋል ወር ጨረቃ በሳኡዲ አረበያ በመታየቷ የኢድ አል ፊጥር በዓል በነገው ዕለት ጁምዓ ሚያዝያ 13/ April22/2023 መሆኑ ታውቋል።

BREAKING NEWS: The Crescent for the month of Shawwal 1444 was SEEN today in Tumair and Sudair subsequently tomorrow i.e Friday, 21st April 2023 is the day of Eid Al Fitr
511 views19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:06:57 አራት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በፌስቡክ ማንነቱን ቀይሮ በመተዋወቅ ‘‘ካናዳ እና እንግሊዝ እወስዳችኋለው’’ በማለት ጾታዊ ግንኙነት እንዲፈጽሙ አድርጓል የተባለው ግለሰብ በጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጣ።

ግለሰቡ ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ እና 20 ግራም ወርቅ ተቀብሎ የማታለል ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ ነው በጽኑ እስራትና በገንዘብ እንዲቀጣ የተወሰነው።

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ አርቲዲ ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ተከሳሹ ታዲዮስ ዘላለም በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ነዋሪ ነው።

ተማሪዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጽ “ናቲ መላኩ” ብሎ ማንነቱን ቀይሮ በካናዳ ነዋሪ በመምሰል ከተዋወቃቸው በኋላ ‘’ካናዳና እንግሊዝ እወስዳችኋለው’’ ብሎ የማታለል ተግባር መፈጸሙ በክሱ ተመላክቷል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሹ ከካናዳ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ በማስመሰል በግንቦትና በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም በተለያዩ ቀናቶች ለ4 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግል ተበዳዮች ስልክ ይደውላል፡፡

በዚህም'' ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ የሚፈጽምላችሁ ሰው ይመጣል፤ አሻራ የሚወሰደው ከዘር ፈሳሽ እና ከወርቅ ስለሆነ አልጋ ይዛችሁ ጠብቁ በማለት'' የግል ተበዳዮች በተለያየ ቀናቶች በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አልጋ ይዘው እንዲጠብቁ ማድረጉ በክሱ ተጠቅሷል።

አልጋ እንዲይዙ ካደረገ በኋላ ማንነቱን ቀይሮ ወደ አልጋ ቤት በመሄድ የግብረስጋ ግንኙነት እንዲፈጽሙ ማድረጉም በክሱ ተመላክቷል።

በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በደረጃ ስድስት በዕርከን 25 መነሻ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነ ሲሆን÷በዕርከን 3 መሰረት ደግሞ በ3 ሺህ ብር የገንዘብ እንዲቀጣ ተወስኗል።
(በታሪክ አዱኛ)
1.8K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:06:05 የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት የዒድ አልፈጥር በዓል ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ ማታ ከታየች ነገ አርብ  ካልታየች ደግሞ ቅዳሜ ይከበራል ሲል አሳውቋል።

ይህን ያሳወቀው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ፤ ለኢትዮጵያና ለመላው ዓለም ህብረተሰብ  የሰላም፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞቱን የገለፀው ሼሪዓ ፍርድ ቤቱ  ሙስሊሙ ህብረተሰብ  በዓሉን ሲያከብር ያጡና የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና በመርዳት እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።
1.8K views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:05:18 የጠቅላይ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤቶች ሊከሰሱ ነዉ ተባለ

ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት በኬኒያ የታገተው የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል  ቤተሰቦች በሁለቱ ተቋማት ላይ ክስ ሊመሰርቱ እንደሆነ አስታዉቀዋል፡፡

በሳምሶን ጉዳይ  የውጭ ጉዳይ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ነው ያሉት ቤተሰቦቹ፤ ክስ ሊመሰሩት መሆኑ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሃለፎም እስካሁን በመስራቤቶቹ በኩል እየተሰጠን ያለው መረጃ ለዜጋ የሚመጥን አይደለም ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተሰጠን ምላሽ እና አሁንም እየተሰጠን ያለው ተመሳሳይ ነው ብለዋል፡፡

በኬኒያ የሚገኝው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በግለሰቡ ዙርያ ምርመራ እያካሄድን ነው ከማለት ውጭ የሚሰጠን ተስፋ የለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በፌደራል እንደዚሁም በኦሮሚያ ክልል ማንኛውም ፍርድ ቤት ጠበቃና የህግ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ዳባ ጩፋ የአቶ ሰምሶን ጉዳይ እልባት አለማግኝት በኬኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ድክመት ነው ብለዋል፡፡

ኤምባሲው ልክ እንደ መንግስት የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ ሲጠበቅበት ነገሩን በቸልታ እያለፈው ይገኛል ብለዋል፡፡

የአቶ ሳምሶን ቤተሰቦች ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ቢያቀርቡም አንድም ውጤት አለማምጣቱትን ነው የገለጹት፡፡

በመሆኑም የአቶ ሳምሶን ተ/ሚካኤል   ቤተሰቦች በሁለቱ ፅሕፈት ቤቶች ላይ ክስ በመክፈት የልጃቸዉን አድርሻ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ በሰጡት መግለጫ አስታዉቀዋል፡፡                       
(ሄኖክ ወልደ ገብርኤል)
1.8K views13:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 15:02:47
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት ምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ ገብተዋል።
2.8K views12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:57:20
የሱዳን ተፋላሚዎች ለ24 ሰአት እንዲቆይ የደረሱት የተኩስ አቁም ስምምነት ተጣሰ!

የሱዳን ተኩስ አቁም ተግባራዊ ሊሆን ትንሽ ሲቀረው የተፈጠረው ተኩስ እንዲጣስ አድርጎታል።ተኩስ አቁሙ የተደረሰው አሜሪካ ሰብአዊ ቀውስ እንዳይፈጠር በማል በሱዳን ተፋላሚ ወገኞች ላይ ጫና ማሳደሯን ተከትሎ ነበር።

ስምምነት ከተደረሰ ከደቂቃዎች በኋላ በካርቱም ዋና ከተማ የአረብ የቴሌቭዥን የዜና ማሰራጫዎች በቀጥታ ስርጭት ሲዘግቡ ከባድ ፍንዳታ ከጀርባ ይሰማ ነበር ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

የጦር አውሮፕላኖች ከካርቱም በላይ ሰማይ ላይ እያገሱ እንደነበር እና በምስራቅ ወደ ከተማዋ ከፍተኛ የጦር ሰራዊት መግባቱን እማኞች ገልጸዋል።
Via:—Alain
2.7K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:52:52
አቶ አንዱዓለም አራጌ ከመሰረቱት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መልቀቃቸውን ዛሬ አስታውቀዋል።
2.5K views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ