Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የቴሌግራም ቻናል አርማ zehabesha_official — ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News
የሰርጥ አድራሻ: @zehabesha_official
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.95K
የሰርጥ መግለጫ

@Zehabeshanewsbot
Contact us - @@EthiopiaI
ዘ-ሐበሻ የኢትዮጲያና ኢትዮጲያዊነትን ሁለንተና የሚቃኝ፣ የሀገርንና የህዝብን ጉዳዮች በብዙ መንገዶች ተደራሽ የሚያደርግ፣ በርካታ ዝግጅቶችና አቀራረቦች ያሉት የሚድያ ተቋም ነው።

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-10 13:27:42 ጎንደር ከተማ ክልከላ አስቀመጠ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 1/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፦

1 . በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው  ፤
2 . በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00  ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፤

3 .ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4 . ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

5 . በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ የተከለከለ ነው ።

6 . በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

7 . በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

8 . የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
        -የልዩ ኋይል ፣
        -የፓሊስ ፣
        -የመከላከያ ሠራዊት ፣
        -የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።
9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈላችሁ  የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስታችሁ ወደ ከተማችን የመጣችሁ በከተማችን በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንድትሰባሰቡ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው

12 . ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ  እንዲሁም  ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።
#Share
3.3K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 13:26:47 ከአርብ ጀምሮ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ የተከሰተው የሰደድ እሳት እስካሁን መቆጣጠር አልተቻለም ተባለ።

በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ውስጥ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ሰደድ እሳት መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከ ቀኑ 9 ሰዓት መነሻው ባልታወቀ ምክንያት መነሳቱ ተገልጿል።

የፓርኩ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዛናው ከፍያለው እንደተናገሩት እሳቱን ለማጥፋት የአካባቢው ማህበረሰብ ቢሞክርም መቆጣጠር አለመቻሉንና ተጨማሪም ከ600 በላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እሳቱን ለማጥፋት መግባቱን ጠቁመዋል።

የቦታ አቀማመጡ ገደላማ መሆኑ እሳቱን ለመቆጣጠር ፈተና ሆኖብናል የሚሉት ሃላፊው አቶ አዛናው፣ እሳቱ ግጭ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በኩል እንደተነሳ ገልፀው እስከ ዛሬ ሚያዚያ 02 ቀን 2015 ድረስ ከቁጥጥር ውጭ እንደሆነ ገልፀዋል።

ስለሆነም በፓርኩ የተነሳውን ሰደድ እሳት ለመቆጣጠር የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ የፓርኩ ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።(አዲስ ዘይቤ)
3.2K views10:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-10 09:09:39 ደሴ ከተማ ዛሬ
ከጧት የተቃውሞ ሰልፍ
ከሰዓት በኋላ ደግሞ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ታስተናግዳለች።

የደሴዉ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ዛሬ ሰኞ ረመዷን 19 ሚያዚያ 2/2015 በሆጤ ስታዲየም ይካሄዳል።

በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን ለመርዳት የምትችሉ ሩዝ፣ዘይት፣ዱቄት፣መኮረኒና ፓስታ የመሳሰሉ  ምግቦችንና አልባሳትን ፆመኞች ይዘው በመምጣት በሚደረገው የድጋፍ ማሰባሰቢያ ላይም እንዲሳተፉ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

#Share
3.3K views06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 23:13:54 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ዛሬ እሁድ ባወጣው መግለጫ መንግሥት ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ ያሳለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ በመግፋቱ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ መቀስቀሱን ገልጿል።

ፓርቲው እስካሁን ድረስ ለሀገራዊ አንድነት እና ሰላም ሲባል ጉዳዩን በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ሲከታተል መቆየቱን ገልጾ ይሁንና መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ከዕለት ወደ ዕለት የለየለት የኃይል ፣ የአፈና እና የማደናገር አማራጭ እየገባ መሆኑን መረዳቱን አመልክቷል።

" መንግስት ችግሩን በሰከነ መንገድ ፣ በውይይት ፣ በጋራ መግባባት እና በመተማመን የመፍታት ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም በስህተት ላይ ሌላ ስህተት እየደረበ እና ችግሩን በአፈና እና በጉልበት ለመፍታት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ከዛሬ ጀምሮ ለችግሩ ዘላቂ እልባት እስከሚሰጥ ድረስ መንግስት እና ግብረ-አበሮቹ በአማራ ልዩ ኃይል ፣ በፋኖ እና በአጠቃላይ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚነዟቸውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎች በይፋና በተከታታይ አጋልጣለሁ " ብሏል።

አብን በመግለጫው የአማራ ልዩ ኃይልን ለማፍረስ እና ትጥቅ ለማስፈታት መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ እና የሚያደርገው እንቅስቃሴ ኃላፊነት የጎደለውና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ድጋሜ አሳውቋል።

የብልፅግና ፖርቲ ሥራ አስፈፃሚ ያሰፈው ውቃኔ መሬት ላይ ያለውን ሃቅ ያላገናዘበ ፣ መርኅ አልባ ፣ አድሏዊ እና አምባገነናዊ ነው ሲል ገልጾታል።

ውሳኔውና የአፈፃፀም ሂደቱ በሕግ አግባብ የተመራ ፣ መርኅ ተኮር እንደሆነ ፣ ውይይት እንደተደረገበት እና መግባባት የተደረሰበት እንደሆነ ለማስመሰል የሚቀርቡ አስተያየቶችም በአጠቃላይ ሃሰት ናቸው ብሏል።

#Share
3.4K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 23:12:37 "የአማራ ልዩ ኃይልን በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የተወሰነ ውሳኔ የለም" ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በሀገር ደረጃ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ ልዩ ኃይሎችን በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት ለማደራጀት መወሰኑን ተናግረዋል። ወደ ትግበራም መገባቱን ገልፀዋል።

ውሳኔው በፌዴራል መንግሥት እና በክልል መንግሥታት ስምምነት የተወሰነ መሆኑንም ተናግረዋል። ውሳኔው በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ  እንደሆነም ገልፀዋል።

በአማራ ክልልም ውሳኔውን ለመተግበር እየተሠራ መሆኑን ያነሱት ርእሰ መስተዳድሩ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር መወያየታቸውንም ገልጸዋል፡፡

በአፈጻጸም ላይ በታየ ክፍተት እና በተነዛው ፕሮፖጋንዳ ችግሮች መከሰታቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግር እንኳን ቢኖር ተወያይቶ መፍታት ይቻላል ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ  አብዛኛው የልዩ ኃይል አባል ውይይቱን አጠናቆ ውሳኔውን  በካምፕ ሆኖ እየተጠባበቀ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ጀግና ልዩ ኃይል ነው፣ መስዋእትነት የከፈለ ልዩ ኃይል ነው፣ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር ሆኖ የሀገርን ሕልውና እና ሉዓላዊነት የጠበቀና ያስከበረ  ነው፣ ይህ ልዩ ኃይል ትጥቅ የሚፈታና የሚበተን አይደለም፣ በላቀ አደረጃጃት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የሚያስችል ነውም ብለዋል፡፡

ልዩ ኃይሉ ዓላማውን ተገንዝቦ ለበለጠ ተልእኮ እንዲዘጋጅም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአማራ ሕዝብ በሁኔታው ቅሬታ ውስጥ መግባቱን የተናገሩት ርእሰ መስተዳድሩ ቅሬታው የመነጨው በተሟላ መንገድ ለሕዝቡ መረጃ ባለመድረሱ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ዓላማው የሀገር አንድነትን የሚያጸና፣ አብሮነትን የሚያስቀጥል እና የጸጥታ መዋቅሩ በክልልም ሆነ በፌዴራል የተናበበና ሕግን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ማድረግ ነውም ብለዋል፡፡

አደረጃጀቱ የሚደገፍ፣ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው የሀገርን አንድነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

አደረጃጀቱ የአማራን ክልል በተለየ መንገድ የሚጎዳ አይደለም ብለዋል፡፡

የአማራ ክልልን ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ ትጥቅ ለማስፈታት እና ለመበተን የታለመ ዓላማ እንደሌለ  አስገንዝበዋል፡፡

በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት በአንዳንድ ከተሞች የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ፣ የአድማ ጥሪ እና የሰዎች እና የተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴን የመገደብ አዝማሚያዎች እያታዩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት፡፡

አላስፈላጊ አካሄዶች አውዳሚ እና አክሳሪ እንጂ አትራፊ አለመሆናቸውንም አንስተዋል፡፡

የአማራ ክልል በጦርነት የከረመ ክልል ነው ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በጦርነቱ ምክንያት ሕዝቡ ተጎሳቁሏል፣ በጦርነቱ ምክንያት የተጎዳው ኅብረተሰብ እና መሠረተ ልማት ገና ማገገም አልቻለም ብለዋል፡፡ ከአንደኛው ችግር ሳያገግም ወደ ሌላ ችግር መሸጋገር ሕዝቡን መጉዳት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በመወያየት አላስፈላጊ ጉዳዮችን ማስቆም እንደሚቻልም ገልጸዋል፡፡ ሁሉም አውዳሚ የሆነውን ጉዳይ መከላከል እንደሚገባውም አመላክተዋል፡፡ ግጭት እንዳይፈጠር ወጣቶች እና የሃይማኖት አባቶች የሚመሰገን ሥራ እየሠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ሕዝብ ጉዳዩን በውል በማጤን፣ በመመካከር እና ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ ማስከን ይገባልም ብለዋል፡፡

የአማራ ልዩ ኃይል በተለየ መንገድ የሚጎዳ ውሳኔ አልተወሰነም፣ ወጥና ሀገራዊ ውሳኔ ነው የተደረገው፣ በሁሉም ክልል የሚፈጸም ነው፣ ውሳኔው ለሀገር ግንባታ ታላቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው እናምናለንም ብለዋል፡፡

ከወቅታዊ ጉዳይ አንጻር የሚነሳው ጥያቄ ትክክል ቢሆንም አፈጻጸሙ ለሀገር የሚጠቅም መሆኑን መገንዘብ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ከካምፕ የወጡ የልዩ ኃይል አባላት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

በረጅም የሀገረ መንግሥት ግንባታ ታሪኩ እና በስርዓት አክባሪነቱ የሚታወቀው የአማራ ሕዝብ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ማየት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ ችግሩ ዳር ወጥቶ ግጭት እንዳይከሰት እያደረጉ ላሉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የልዩ ኃይል አባላት ትጥቅ አትፈቱም፣ የምትበተኑበት ነገር የለም፣ ወደ ላቀ ተልእኮ ነው የምትሽጋገሩት፣ ይሄን አውቃችሁ ለሀገራችሁ እና ለክልላችሁ ስታደርጉት የነበረውን አስተዋጽዖ በተሟላ መንገድ ለማስቀጠል እንድትችሉና እንድትዘጋጁ አደራ እላለሁም ብለዋል፡፡
እንደ አሚኮ ዘገባ፤ በመደማመጥ ችግሮቻችን እንፈታለን፣ የአማራን ጥያቄዎች እናስመልሳለንም ነው ያሉት፡፡
3.4K views20:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 12:01:16 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በክልል ልዩ ኃይሎች ላይ የተላለፈው ውሳኔ፤ “ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ ይደረጋል” አሉ

የክልል ልዩ ኃይሎችን ወደ ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች የማካተቱ ውሳኔ፤ “ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን” ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ። ይህ ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይደረግ “ሆን ብለው የአፍራሽነት ሚና በሚጫወቱ” አካላት ላይ፤ “ተገቢው የህግ ማስከበር እርምጃ” እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን ያሉት የክልል ልዩ ኃይሎችን በሚመለከት በመንግስት የተላለፈውን ውሳኔ በተመለከተ ዛሬ እሁድ ሚያዝያ 1፤ 2015 በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው በተሰራጨ መግለጫቸው ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መግለጫቸው፤ ተቃውሞ ከሚያነሱ አካላት ውስጥ የተወሰኑት ጉዳዩን በደንብ ካለመረዳት የሚያደርጉት መሆኑን ገልጸዋል። ቀሪዎቹ አካላት ግን ሆን ብለው ውሳኔውን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ናቸው ሲሉ ከስሰዋል።

“ ‘የዚህ ወይም የዚያ ክልል ልዩ ኃይል ብቻውን ትጥቅ ሊፈታ ነው፤ የዚህኛው ክልል ይቆይ ተብሏል፤ ይሄን ወይም ያንን ሕዝብ ለመጉዳት የተደረገ ነው’ የሚሉ ውዥንብሮችን የሚነዙ አካላት ገሚሶቹ ባለማወቅ ሲሆን፤ የተቀሩት ዓላማቸው ሕዝብ ከማበጣበጥ የዘለለ አይደለም” ብለዋል አብይ።

“ጥቂት የማይባሉት ‘የክልል ልዩ ኃይል መፍረስ አለበት’ ብለው ሲጽፉና ሲሞግቱ የከረሙ ናቸው፤ ጠለቅ ብለን ብንፈትሻቸው፥ ይሁን ሲሏቸው አይሁን፣ አይሁን ሲሏቸው ይሁን የማለት ልማድ የተጠናወታቸው ሆነው እናገኛቸዋለን” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ተችተዋል። አብይ “የአፍራሽነት ሚና” አላቸው ባሏቸው አካላት መንግስታቸው ሊወስደው ስላሰበው እርምጃም በመግለጫቸው ጥቆማ ሰጥተዋል።

… በመጨረሻም <<ይህ ውሳኔም ለኢትዮጵያ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ለሕዝቡ ሰላም ሲባል ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ ይደረጋል። ሳይገባቸው የሚቃወሙትን ለማስረዳትና ለማሳመን ጥረት እናደርጋለን። ሆን ብለው የአፍራሽነት ሚና በሚጫወቱት ላይ ደግሞ ተገቢው የሕግ ማስከበር እርምጃ ይወሰዳል። ለዚህም በቂ ዝግጅት ተደርጓል። በመሆኑም የሚመለከታቸው ተቋማትና ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይ፣ የውሳኔውን ሃገራዊ ፋይዳና የሚያስገኘውን ዘላቂ ጥቅም ከግምት በማስገባት ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንድታደርጉ በዚሁ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።>> ብለዋል።
3.6K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 22:00:22 ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ድረስ መንገዶች ይዘጋሉ።

" ኢፍጣራችን ለወገናችን " በሚል ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከባምቢስ በመስቀል አደባባይ እስከ ሜክሲኮ አደባባይ ባለው ጉዳና ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም የሚካሄድ ይሆናል፡፡

ፕሮግሙ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ  አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ በሚካሄድበት ወቅት  የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፡-  

- ከቅዱስ ኡራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአራተኛ ክፍለ  ጦር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፣ በለገሃር ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከጎማ ቁጠባ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከአራት ኪሎ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ወደ  መስቀል አደባባይ
- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከሜትሪዎሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከቀኑ 6:00 ሠዓት እስከ ምሽት 2:00 ሠዓት ድረስ ዝግ ይሆናሉ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልእክት አስተላልፏል።
4.0K views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 14:29:44 ነቀምት ከተማ ከንቲባ ታሰሩ

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ በሰው ግድያ የጠረጠራቸውን የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ ቶሌራ ረጋሳን ማሠሩን ከከንቲባው ቤተሰቦች ሰምቻለሁ ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።

ከከንቲባው በተጨማሪ፣ ሌሎች ቁጥራቸው ያልታወቀ የመንግሥት ኃላፊዎችና የመንግሥት ሠራተኞችም መታሠራቸውን ምንጮች መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ከንቲባውና ሌሎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ታሠሩ የተባለው፣ ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በከተማው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ደሳለኝ በኮንጆን ገድለው በተሰወሩ ማግስት ነው።
4.2K views11:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 23:13:58 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " የሕገ ወጥ ቡድኑን የሹመት ይጽደቅልን " ጥያቄ መቼም ቢሆን የማትቀበለው መሆኑን አስታወቀች።

በዛሬ ዕለት በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በሕገ ወጥ መንገድ በተሾሙ የቀድሞ አባቶች መካከል ውይይት ተደርጎ እንደነበር ተሰምቷል።

ውይይቱን በተመለከተ የመንበረ ፓትርያርክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

በመገጫውም ፤ ቅዱስ ሲኖደስ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና በሕገ ወጥ የተሾሙ ግለሰቦች በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ጽ ቤት የይቅርታ ማመልከቻ እንዲያስገቡ ጥሪ አስተላልፎ እንደበር አስታውሷል።

ቢሆንም በይቅርታ ደብዳቤ አስገብተው ከተመለሱት ከአንዱ " አባ " ኃይለ ኢየሱስ ውጭ ሌሎች በይቅርታ ከመመለሰ ይልቅ ለውይይት እና ሕገ ወጥ ድርጊቱም #እንዲጸድቅላቸው መጠየቃቸውን ገልጿል።

" ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ቤት የሰላም ዓደባባይ የንስሓ ሰገነት በመሆኗ ለፍቅር ረጅም ርቀት በመጓዝ ከግለሰቦቹ ጋር በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ እንዲሁም በሌሎች ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት ተወያይታለች " ያለው መምሪያው " ከዚህም አልፎ ቤተ ክርስቲያን የሀገር ሰላም የኢትዮጵያውያን የደኅንነት ኑሮ በእጅጉ ስለሚያሳስባት በብዙ ርቀት ለይቅርታ በሯን ከፍታ ስትጠባበቅ ነበረች " ብሏል።

ይሁን እንጂ በዛሬው ዕለት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የመጡ እና ሁሉንም እንወክላለን ያሉ 6 ግለሰቦች ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ጋር የተወያዩ ሲሆን በውይይቱ ግን የተዘረጋው የቤተ ክርስቲያን የፍቅርና ይቅርታ እጅ በግለሰቦቹ ግን እንደመልካም አልታየም አሳውቋል።

ከዚህ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት ከተደረሱ 10 የስምምነት ነጥቦች መካከል በተራ ቁጥር 6 የሚገኘው ውሳኔ "በሕገ ወጥ መንገድ የተሾሙት "አባቶች" ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው ይመለሳሉ" የሚል ቢሆንም ግለሰቦቹ ግን በመርሕ ደረጃ ስምምነቱን እንቀበለዋለን በአፈጻጸም ደረጃ ግን ቅዱስ ሲኖዶስ ሹመታችንን ያጽድቅልን" የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን መምሪያው በመግለጫው አስረድቷል።

ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሕገ ወጦቹን በተመለከተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተለውን ውሳኔ መወሰኗን መምሪያው አሳውቋል ፦

1ኛ. በየትኛውም መንገድ የጋራ ውይይት አይኖርም፤

2ኛ. ለይቅርታ የሚመጡ ከሆነ በቡድን ተሰባስቦ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እንዲሆን፤

3ኛ. የይቅርታ ማመልከቻውን እያንዳንዳቸው ለመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዚህና በሌሎች መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ 21/07/2015 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ ጠርቷል።
1.6K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 23:13:11
የህውሃት መስራች አቶ ስብሃት ነጋ አሜሪካ ገብተዋል።
በሌላ በኩል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ለህክምና ወደ ውጭ እንዳይሄዱ ተከልክለዋል!
1.5K views20:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ