2023-03-15 19:38:40
ገሀዱን በጩኸት ለመሸፈን የሚደረግ ጥረት
...
ከሰሞኑ በሀላባ ሊዲያ ተብላ በምትጠራው ተማሪ እስር ጉዳይ በባለፈው ያገኘሁትን መረጃ ከሰጠሁ በኃላ በተለይ በቲክቶክ በኩል በርካታ የተንጋደዱ መረጃዎች የሰራሁት ቪዲዮ ኮሜንት ላይ ሲጻፉ አይቻለሁ። ኮሜንቶቹ ከስድብ ጋር ተቀላቅለው በርካታ በመሆናቸው ሁሉንም ማየት ባልችልም የተወሰኑት ላይ ግን ከዚህ በታች እርምት ለመስጠት እሞክራለሁ፥ መጨረሻ ላይም በሒደቱ የታዘብኩትን አስቀምጣለሁ፦
1/ የወደቀችው መስሊም ልጅ "ኢየሱስ ጌታ ነው" ብላለች በሚል የተገለጸው ስህተት ነው። ልጆቹ ከወደቁ በኃላ ይህንን የተናገረችው ሊዲያ እንጅ ሙስሊም ተማሪዎች አይደሉም። በዚህ በኩል የተሰራጨው መረጃ አሳሳችና ሙስሊሙ ስለ ኢየሱስ እንዲመሰክር አድርጋለች የሚል አግናኝ ትርክት ለመፍጠር የተሰራጨ ቅጥፈት ነው። ለነገሩ በዚ በኩል የራሳቸው ሰዎችም ስህተት መሆኑንና ይህንን የተናገረችው ሊዲያ እንደነበረች ሲገልጹ ነበር።
...
2/ በማረሚያ ቤት ተገኝተው እሷን የጠየቁ ሰዎች በምን አግባብ ስልክ ይዘው ገብተው ፎቶ እንዳነሱ በግሌ ግርምትን ፈጥሮብኛል? የሀላባ ማረሚያ ቤት መሠል ህገወጥ ስራ ሲሰራ መረጃው አልነበረውም? ስለ ህግ ሲሟገቱ የነበሩ ሰዎችስ መሠል ህገወጥ ስራ ላይ ሲሰማሩ ማየት አያስተዛዝብም? እውነት ውግንናቸው ለህግ ቢሆን ህግን የመጣስ እብሪት ውስጥ መግባታቸው ስለማንነታቸው የሚጠቁመን ነገር የለም?
...
3/ እርቃኗን ተደርጋ ተመርምራለች የሚለውን በተመለከተም ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ የዞኑን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ታረቀኝ ጉራቻ ባነጋገረችበት ወቅት "ፍጹም ሀሰት" መሆኑን ገልጸውላታል። ሆን ተብሎ የሀላባን ስም ለማጥፋት የተፈጠረ ትርክት መሆኑንም ነግረዋታል።
...
4/ ልጅቷ እድሜዋ ለእስር አይበቃም በሚል የሚደረገውን ክርክር በተመለከተም የህግ ባለሙያዎችን ሲያከራክር የቆየ ጉዳይ ስለሆነ በሱ ጉዳይ ዝርዝር ማብራሪያ አልሰጥም። ልጅቷ 10ኛ ክፍል ከመሆኗ አንጻር በትንሹ እድሜዋ 15 እና ከዚያ በላይ መሆኑ ግልጽ ነው። ይህ ሲሆን ደግሞ ህጉ ምን ይላል? ብለን ከጠየቅን 18 አመት ባይሞላትም ከ15 አመት በላይ ከሆነች በመደበኛው የህግ ሂደት ጉዳዮ እንደሚታይ የሀገሪቱ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ይገልጻል (አንቀጹ ከታች ተያይዟል)
5/ እነዚህ ሰዎች ካለ እድሜዋ ታሰረች በሚል እውነት በሰብአዊነት ከነበረ ትግላቸው ከወራት በፊት መሠል ተማሪዎች ጉራጌ ዞን ጉንችሬ ላይ በሒጃብ ምክንያት ተማሪዎቹ ለበርካታ ቀናት ሲታሰሩ የት ነበሩ? በእርግጥ የጥያቄያቸው ሞቲቭ ሰብአዊነት ስላልሆነ ጥያቄየ ቀሽም ሊሆን ይችላል። ግን እውነታው መታወቅ አለበት።
❐ የግል አስተያየቴ
በዚህ ዙሪያ የታዘብኩትን እውነታ ያለምንም ማሽሞንሞን ማስቀመጥ እፈልጋለሁ። ይኸውም አብዛኛው ሰው ሀላባን እየሰደበና እየወቀሰ ያለው እንዲሁ በዚህ ክስተት ብቻ አይደለም። የተጠና ተግባር ነው እየተፈጸመ ያለው። ሀላባ የሙስሊም ሀገር ናት ተብሎ ስለሚታሰብ ማንነታቸውን ያማከለ ውግዘት ነው እየተሰነዘረ ያለው። የአንዳንዶቹ ግልብ ፍርጃ ቆርቁሮን የምንናገረው ሀላባ ሁነን አልያም ስለ ጉዳዩ ከሚታወቀው እውነታ የዘለለ የተለየ እውቀትና መገንዘብ ኑሮን አይደለም። መጨነቁ ስለ ህግ ሳይሆን የሀላባ ህዝብ እሴት አድርገው እስልምና ላይ ዘመቻ የመክፈት ሴረኝነት እንደሆነ ስለገባን ነው። ጉዳዩን ከህግ አንፃር እንዲፈታ ነጻ ሁነው ቢጠይቁ ማንም ተቃውሞም ትችትም ባላቀረበ ነበር። የአብዛኛው ፍርጃ ግን "ሀላባ የሸሪዓ ዞን ናት" የሚል ሆንተብሎ እስልምናን የማጠየም ስትራቴጂ ስለሆነ ነው። ይህንን ደግሞ ሀላባም ላይ ሆነ ሌላ የትም ቦታ ስተገብሩት ሽታው ስለሚታወቀን ያለምንም ማመንታት ስለዲኑ ስንል ቆሻሻውን ነጥሎ ለመለየት አብረናቸው እንቆማለን።
...
___ የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/Yahyanuhe
925 views16:38