Get Mystery Box with random crypto!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የሰርጥ አድራሻ: @yahyanuhe
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.06K
የሰርጥ መግለጫ

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 16

2022-11-01 10:25:24
ለኡስታዝ አቡ ሐይደር የታሰበውን መኪና በተመለከተ
...
ባለፉት ቀናት የተለያዩ ወንድሞች ኡስታዝ አቡ ሐይደር ለገጠር የዳዕዋ ስራዎቹ ለሚያስፈለገው የመስክ መኪና ግዥ በሚያደርጉት ማስተባበር ውስጥ እንድሳተፍ ጠይቃችሁኛል። ይህንን በማስመልከት ቀጥታ ኡስታዝ ጋ ደውየ ዛሬ አውርቸዋለሁ። የደወልኩበት ምክንያት ተግባሩን ሳልወደው ቀርቸ አይደለም፥ መደወልና ማወያየት የሚያስፈልገው ሁኖም አልነበረም። ምክንያቴ ግን ሌላ ነው። ኡስታዝ ሳውቀው በጣም የተለየና ዱንያ ፈጽሞ ግድ የማይሰጠው ሰው ነው። ይህንን በተመለከተ መሠል ጉዳይ እንደማያስደስተው ስለማውቅና ከዛሬ ሶስት አመት በፊት እንዲሁ እኔና አቡ ዩስራ ባለንበት ከብዙ ወንድምና እህቶች ጋር አስተባብረን መኪና ለመግዛት ሞክረን በነበረበት ወቅት ደስተኛ አለመሆኑን ገልጾ ስላስቆመን ነበር።
...
አሁን ስደውልለት እንደነገረኝ ሰውን ማስቸገር እንደማይፈልግ ቢገልጽም በቀና ወንድሞች ጉትጎታ በስተመጨረሻ ለዳዕዋው እስከመጠቀመ ድረስ መገዛቱ መልካም ነው በሚለው መስማማቱን ገልጾልኛል። አልሐምዱሊላህ በጣም የሚያስደስት ነው። ስለዚህም ካሁኗ ደቂቃ ጀምሮ በዚህ የማኅበራዊ ሚዲያ ማስተባበር ውስጥ መኪናው እስከሚገዛባት ቅጽበት ድረስ በአሏህ ﷻ ፍቃድ ከጎናችሁ ነኝ።
...
SADIK MOHAMMED AHMED
COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000329226712
0911 10 32 31
4.1K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 21:23:14
ሁሴን የተሰኘ ወንድም "ንጽጽር ለማጥናት ምን ማድረግ ይኖርብኛል?" ሲል ጠይቆኛል። ይህንን በተመለከተ ከዚህ በፊት ለተወሰኑ ወንድሞች ያብራራሁበትን መሠረታዊ መመሪያዎች አስመልክቶ ለሁላችሁም እንዲጠቅም እንደሚከተለው አጋርቻችኃለው። ጠቃሚ ሁኖ ካገኙት፥ ሼር ያድርጉት..!
..


4.1K views18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 20:02:22
ይህ ጹሁፍ በትላንትናው እለት እህታችን ሳራ ጋ አንድ ወንድም የጻፈላት መልዕክት ነው። ኃላ ላይ በነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከተወያየ በኃላ በስተመጨረሻ ተስማምቶ እስልምናን ተቀብሏል፥ አልሐምዱሊላህ። ለእስልምና ጥሩ አመለካከት ያለው ሲሆን በዚህ ፍጥነት ቁርአን ለመቅራት ትምህርት ጀምሯል። በአካል ዒባዳ ለመፈጸም ሰዎች እንዳያዩትና ለቤተሰብ እንዳይናገሩበት ቢጨነቅም ዲኑን ለመማር ግን የኦንላይን አማራጩ ጭንቀቱን አቃሎለታል።
..
መከራዎች ሁሉ ፊትለፊት እየታዩ እስልምናን ማስቀደምና ስቃዩን ለመቀበል መቁረጥ ትልቅ ኢማን ይጠይቃል። የፊርአውን ደጋሚዎች በሰለሙ ጊዜ "እቆራርጣችኃለው" ብሎ ፊርአውን ሲዝትባቸው "የፈለግከውን አድርገን ስልጣንህ ዱንያ ላይ ነው" ሲሉ ቁርጠኝነታቸውን ፊቱ ላይ ነገሩት፥ የሰጡት መልስ የኢማን ጥንካሬ ወሰንን የሚገልጽ ነበር። በተለያዩ አጋጣሚዎች ሰዎች ሲሰልሙ በርካታ ስቃይ ሲገጥማቸውና አልበገር ብለው ኢማናቸውን ሲያስቀድሙ አስተውያለሁ። አንተና እኔ አሏህን ﷻ ለማምለክ እንኳን በእጃችን ያለውን የነጻነት ኒዕማ አስተውለነው እናውቃለን? አሏህ ሁላችንንም ጽናቱን ይወፍቀን..!
4.2K views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ