Get Mystery Box with random crypto!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የሰርጥ አድራሻ: @yahyanuhe
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.06K
የሰርጥ መግለጫ

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-02-19 15:30:01 "በቅበላ ለምን ዘፈን አስተዋወቃችሁ? ወንድ ከሆናችሁ በረመዷን ለምን አታስተዋውቁም?" የሚል የጅል ፖስት ደግሞ እያየን ነው። በረመዷን አንድ ዘፋኝ ዘፈን ቢያስተዋውቅ የፕሮሞሽን ከመክሰር በዘለለ ምን ይፈይድለታልና ነው የሚለፋው? ዘፋኙኮ ዘፈኑ በየትኛው አጋጣሚ ለማን ቢያስተዋውቅ እንደሚሳካለት ጠንቅቆ ያውቃል። መጀመሪያ ዘፈንን በግልጽ አውግዘህ ከእምነትህ ሰዎች ነጥል፥ አማኝህ ዘፈንን ውግዝ ካለና ከልቡ ከተጸየፈው አንተ ሳትለው አዝማሪው ለገበያው ሲል ሌላ አማራጭ ይፈልጋል። ዝም ባልንበት እየጠራችሁ "ንገሩኝ ባይ" አታስብሉን..!
1.1K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 15:29:48 ሙስሊም ቁጥሩ አናሳ ሁኖ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ላይ "መስጅድ ለምን ተገነባ" ብሎ አይኑ የሚቀላና የሽብርተኝነት ማሳያ አድርጎ በየመድረኩ የሚለፍፍ ሁሉ 100% ሙስሊም በሆነበት የአፋር ህዝብ ውስጥ በቋንቋህ መዝሙር ካልዘመርንልህ የሚሉ ሰዎችን ህዝቡ "አንፈልግም፥ ለማንስ ነው የምትዘምሩት?" ብሎ ስለተናገረ መጥተው ስለመብት ሊያስተምሩት ይሞክራሉ፥ ቀልደኞች..!
1.2K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 14:41:38 አሏህ ﷻ ነብዩ ሙሐመድን "ﷺ" ካረማቸው ጥቂት ጉዳዮች አንዱ የአይነስውሩ የአብዱሏህ ኢብን ኡሙ ሙክቱም رضي الله عنه ታሪክ አንዱ ነው። ታሪኩ በአጭሩ የአሏህ መልዕክተኛ "ﷺ" የቁረይሽ ኩፋሮችን ለማስለም ውይይት እያደረጉ በነበረበት ወቅት አብደሏህ ኢብን ኡሙ ሙኽቱም ጣልቃ ገብቶ ስላቋረጣቸው ውይይቱ በመበተኑ ምክንያት እሳቸው መከፋታቸው ነበር። ታሪኩ ሁሉም ሰው ስለሚያውቀው ዝርዝር ማብራሪያ አያስፈልገውም።

የአሏህ መልዕክተኛ ለነዚያ ሰዎች ቦታ የሰጡበት ዋነኛ ምክንያት ሒዳያቸውን በመመኘት ከቀናነት ነበር። ያም ሁኖ ጌታቸው ዘንድ እንደ ስህተት ሁኖ አረማቸው። አሏህ ﷻ ክስተቱት አታኮ ለኛ የሰጠን ግን ትልቅ የህይወት ትምህርትን ነበር። ይኸውም በየትኛውም መመዘኛ ቢሆን ለኩፋሩ ከሚኖረን ቦታ ይልቅ ኢምንትም ብትሆን ለአንድ ሙስሊም ወንድማችን የሚኖረን ክብር አሏህ ዘንድ ከፍ ያለና የላቀ ነው።

ኡስታዝ ባሳም
1.2K views11:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 16:01:38
የቲክቶቭ ላይቭ ትምህርታችን ዛሬም በፕሮግራሙ መሠረት ይቀጥላል፥ የሰአት ለውጥ ግን አድርገናል። ዛሬ በአሏህ ﷻ ፍቃድ የምንገናኘው ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ ይሆናል። እንደተለመደው ሼር ማድረግ አይዘንጉ..!
418 views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 15:36:41 ሰዎች እስልምናን ሲቀበሉ፦

❐ ሰዎች የሰለሙበትን ኒያ የመፈተሽና የሰውን ልብ የመጠርጠር መብቱ የለንም። እስልምናን ሲቀበሉ የኛ ኃላፊነት በደስታ መቀበል ብቻ ነው፥ የልባቸውን ጉዳይ የምንተወው ለአሏህ ﷻ ብቻ ነው። የኛ ኃላፊነት የምስክርነት ቃሉን አምኖ መቀበል ብቻ ነው።

❐ ታዋቂ ሰዎች ሲሰልሙ ባላቸው ታዋቂነትና ተሰሚነት ልክ ለሰዎች ሰበብ ሒዳያ እንዲሆኑ በማሰብ መደሰታችን ትክክለኛና የሚጠበቅ ነው። ልክ የአሏህ መልዕክተኛ "ﷺ" አንዳንድ በጃሂልያ ህይወታቸው ጥሩ ስም የነበራቸው ሰዎች ወደ እስልምና ሲመጡ እንደተደሰቱት እኛም እንደሰታለን። በሰዎቹ ምክንያት ሌላው ለነሱ መልካም አመለካከት ያለው አካል እስልምናን በበጎ እንደሚረዳው ተስፋ ከማድረግ ጋር ቀናዒ ነን። ከዚያ ውጭ የትኛውም ነፍስ አሏህን በመፍራቱ ካልሆነ በስተቀር የተለየ ደረጃ የለውም፥ በመዳኑ ከመደሰት በዘለለ ሰውየው ሳይቀር የተለየ የበላይነት ስሜት እስከሚሰማው የሚያደርግ ፍንደቃ ግን የለንም። አንድ ሰው ወደ እስልምና በመምጣቱ የሚያስደስተንን ደስታ ያህል ከልባችን እንደሰታለን።

እስልምናን ለተቀበላችሁ ወንድምና እህቶች

❐ እስልምናን በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያ አማካኝነት የምትቀበሉ ወንድምና እህቶች በተቻለ መጠን እስልምናን በመማር ላይ ቅድሚያ ብታተኩሩ መልካም ነው። ወደ ማኅበራዊ ሚዲያ ክርክሮችና ምልልሶች መግባታችሁ ፋይዳው የደበዘዘ ነው። በዚህ ተግባራችሁ አንደኛ እስልምናን የምትማሩበትን ጊዜ ታባክናላችሁ ሲቀጥል ባልተማራችሁትና ባላወቃችሁት አጀንዳ ዙሪያ ነውና ምልልስ የምታደርጉት፥ ተሳስታችሁ ሰው ታሳስታላችሁ። ሲሰልስም የተቀበላችሁት እምነት ውስጥ ያለውን የዒባዳ ውበት እንዳታጣጥሙት በንትርክ ቢዚ ትሆናላችሁ። ስለዚህም እረፍት በመውሰድ ለራስ ጊዜ መስጠታችሁ የተሻለና ጠቃሚ ነገር ነው።
___
የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/Yahyanuhe
1.0K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 15:36:38
999 views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 16:47:29 https://vm.tiktok.com/ZMYrbNdf7/
709 views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 15:29:09
ከባለፈው የቀጠለው የቲክቶክ ላይቭ ትምህርታችን ዛሬም ይቀጥላል። በዛሬው ፕሮግራማችን ጀምረነው የነበረው "የመጽሀፍ ቅዱስ መበረዝ ማሳያዎች" የተሰኘው ንዑስ ክፍል ላይ ውይይት እናደርጋለን። ጠቃሚ ርዕሶች ስለሚነሱ የምትችሉ ብትከታተሉት ታተርፉበታላችሁ። እንደተለመደው ሼር ማድረግ አይዘንጉ..!
1.1K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-12 14:54:21
መልካም ስራዎችን ለመስራት መቻኮል፡-

አነስ ኢብኑ ማሊክ رضي الله عنه እንዳስተላለፉት ረሱል "ﷺ" እንዲህ ብለዋል፡-

"በጎ ሥራ ​​ከመጥፎ አሟሟት፣ ከክፉ ገጠመኝ ከበሽታና ከጥፋት ይጋርዳል። በእርግጥም በቅርቢቱ ሕይወት መልካም የሆኑ ሰዎች በመጨረሻይቱ ዓለምም ከመልካሞቹ ናቸው"

አልባኒ፥ ሰሒህ
874 views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-07 14:44:30
በዛሬው ዕለት ከ10:30 በኃላ በአሏህ ﷻ ፍቃድ ቲክቶክ ላይ የላይቭ ትምህርት ይኖረናል። የውይይታችን አጀንዳም የነብዩ ሙሐመድ "ﷺ" እና የአዒሻን ጋብቻ በተመለከተ የሚነሳው ተለምዷዊ ጥያቄ ላይ ያተኩራል። ከቆዩ ጥያቄዎች ተነስተን አዳዲስ ሙግቶችንም እየቃኘን አያይዘን እንመልሳለን። ተከታተሉት፥ ጥያቄውን ለሚያነሱ ሙስሊም ያልሆኑ ወገኖችም ሼር አድርጓቸው..!
1.7K views11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ