2023-03-26 22:53:36
የሚሽነሪው እንቅስቃሴ መልኩን እየቀያየረ አሁንም ድረስ ቀጥሏል። ህዝባችን በተለይም በገጠር አካባቢ የሚገኘው ለዚህ የኩፍር እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ለመኾኑ አያጠያይቅም።
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ይህንን እንቅስቃሴ ከመመከት አንጻር የራሱን አስተዋጽኦ ለማበርከት በንጽጽር ሃይማኖት ዘርፍ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ወንድምና እህቶች ትብብር የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው።
ተቋሙ በገጠሪቱ አካባቢዎች በተለይም ለአክፍሮቱ ኀይላት ተጋላጭ በኹኑ ስፍራዎች ላይ ለዱዓቶች የተለያዩ ጠቃሚ ስልጠናዎችን በመስጠትና በዚህ መስክ ትኩረት ያደረጉ ዳኢዎችን በመላክ ማኅበረሰቡን የማስተማር ስራዎችን ሰርቷል፥ ወደፊትም በኢትዮጵያ 16 ቦታዎች ላይ መሰል ስራዎችን ለመስራት አቅዷል።
የንጽጽር ሃይማኖት ስርአተ-ትምህርት ተቀርጾለት በቅጡ እንዲሰጥና ፍላጎት ያላቸው በአግባቡ የሰለጠኑ ተተኪዎች እንዲኖሩት ሰፊ እቅዶችን አዘጋጅቷል፤
ተቋሙ በንጽጽር የሀይማኖት ላይ መሠረታዊ ስራዎችን በመስራት በመጽሀፍት፣ በኦዲዮቪዥዋልና በድረ ገጽ በኩል ወቅቱን የጠበቀና አስፈላጊ ትምህርቶችን እየሰጠ ይገኛል፥ ለወደፊትም በሰፊው ለመስራት አቅዷል።
.
.
.
ተቋሙ እነዚህንና ሌሎችንም በርካታ ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት ከመሬት ለማውረድ ዕቅድ ነድፎ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ይሕንን ስራ ከመሬት ለማውረድ ደግሞ የናንተ ድጋፍ ወሳኝነት አለው። ከዚህም አኳያ ሰኞ ማለትም መጋቢት 18/ March 28 በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ተጋባዥ እንግዶችና ኡስታዞች በተገኙበት ፈንድሬይዚንግ ይደርጋል። በዚህ ፈንድሬይዚንግ መሰናዶ ተሳታፊ በመሆን የአቅምዎትን በማድረግ የዚህ መልካም ስራ ባለ አሻራ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበንልዎታል። መሰናዶው በሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል ኦፊሺያል የቲክቶክ አድራሻ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር 4:30 ጀምሮ ከተራዊህ በኃላ የሚካሔድ ይሆናል።
ቲክቶክ ለሌላችሁ በቴሌግራም ሊንክ ጆይን ማለት ትችላላችሁ፦
https://t.me/+Dy1d7s3_31s4NmQ0
ቲክቶክ ሊንክ፦ https://bit.ly/3BZerNy
ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል
779 viewsedited 19:53