Get Mystery Box with random crypto!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የሰርጥ አድራሻ: @yahyanuhe
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.06K
የሰርጥ መግለጫ

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-23 12:37:42 Live stream finished (1 hour)
09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-23 11:16:17 Live stream started
08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-22 16:56:27 https://hidayacomparative.org/?p=975
1.4K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 18:52:35
ሚሽነሪውና መጅሊሱ
...
የሚሽነሪውን እንቅስቃሴና የኛን ሚና በተመለከተ አንድ የዘነጋሁት ነገር ስላለ እሱን ለመጨመር ልሞክር። በሚሽነሪ እንቅስቃሴ ዙሪያ በግለሰብ ደረጃ አልያም በቡድን ደረጃ ለሚሰሩ የኩፋሩ መንደር ስራዎች የንጽጽር ወንድሞች በግልም በቡድንም እስከማቀው የቻሉትን ስራ እየሰሩ ነው። በተቋም ደረጃ ሚሽነሪው ለሚሰራው ስራ ግን በምካቴ ስራው በኩል ትልቅ ኃላፊነት ያለበት አካል መጅሊሱ ነው። ይህ ግልጽ መሆን አለበት። በተቋም ደረጃ ለሚሰሯቸው ስራዎች በግለሰብና በቡድን ደረጃ የሚሰጥ ግብረ መልስ ያልተመጣጠነ ብቻ ሳይሆን ከሚሰራው ስራ አንጻር እዚህ ግባ የሚባልም አይደለም። እውነት ለመናገር በዚህ በኩል መጅሊሱ ምን እየሰራ እንዳለ መረጃው የለኝም።
...
በገጠሩ አካባቢ ለሚሰሩ የዳዕዋ ስራዎች ዳዒዎችን የማዘጋጀት፣ የማሰልጠንና አቅጣጫ የመስጠት ስራ የሚመለከተው በዋናነት የህዝበ ሙስሊሙን ተቋም ነው። በዚህ በኩል እስከማቀው ድረስ የትኛውም ንጽጽር ላይ የሚሰራ ዱዓት በመጅሊሰ በኩል እገዛ ተጠይቆም "ምን መሰራት ይኖርበታል?" በሚል ተጠይቆም አያውቅም። ስልጠና የሚሰጠውም ሆነ ስራዎችን የሚሰራው በግል አልያም በቡድን በሚደረጉ መሰባሰቦች ጥረት ብቻ ነው። ከዚህ በኃላ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች መጅሊሱ ይህንን ክፍተት የሚደፍን እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ።
2.0K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 17:33:42
ምንድን ነው የሚሻለው? መልሱ ቀላል ነው። በየአካባቢው ያለው ሙስሊም ራሱን ማደራጀት፣ ልጆቹን ዲን ማስተማር፣ ማንቃትና በዙሪያው በኩፍር ውስጥ ያለውን ህዝብ ስለማስለም መወያየት ነው። አሁን ላይ "ሊያከፍሩን ነው" በሚል ስለመከላከል የሚታሰብበት ሰአት አይደለም። "ሀላባን እናከፍራለን" ሲሉ መልሳችንና እቅዳችን መሆን ያለበት "ለከንባታና ሀድያ ዳዕዋን እንዴት በቅጡ እናድርስላቸው?" የሚል ነው። እነሱ "ትልቅ ስራ እየሰሩ ነው" ለሚለው አዎ እየሰሩ ነው። ታዲያ የኛ ግብረ መልስ ምንድን ነው? የነሱን ስራ እየታዘብን መተከዝ? በፍጹም..! "ሀቅ አለን" "በልፋታችን ጀነትን እንመነዳለን" ብሎ የሚያምን ሙስሊም ጥረቱ ከኩፋሩ ሊበልጥ እንጅ ፈጽሞ ሊያንስ አይገባም። ሁላችንም በየፊናችን አካባቢያችን ላይ እንስራ፤ ኢንሻአላህ በኒያችንና በልፋታችን ልክ ደግሞ አሏህ ይረዳናል።
2.1K views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 18:46:36 Live stream finished (1 hour)
15:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 17:19:28 Live stream started
14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 14:51:29
ከዚህ በፊት በተለያዩ ምዕራፎች ስንመልሳቸው የነበሩ ጥያቄዎች በ37 ላይቭ ፕሮግራም ተጠናቀዋል። አሁን ደግሞ የሴቶች መብት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን የምንመልስበት ምዕራፍ ጀምሯል። በዛሬው እለት በአሏህ ﷻ ፍቃድ ሁለቱን ጥያቄዎች አስመልክቶ ማብራሪያ እንሰጣለን። እንደተለመደው በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ እንዲሁም ባልገባችሁ ነጥብ ዙሪያ መወያየት ትችላላችሁ።
...
የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን፦ https://bit.ly/3r7DhoY
2.1K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 16:14:13 የሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል አባል እና የዳዕዋው አካል ለመሆን፦

https://bit.ly/3r7DhoY
2.1K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-19 16:14:08 ለማስታወስ ያክል፦
...
እዚህ ፔጅ ላይ የሚለጠፉ የንጽጽር ትምህርቶች አንዳንድ ወገኖቻችን ከምታስቡት በተቃራኒ ነው። ትምህርቶቹ ማንንም የማስከፋት አላማ ኑሯቸው የሚለቀቁ አይደሉም። በሚለጠፉ ትምህርቶች ተመርኩዘው ጥቂትም ቢሆን ሰዎች እውነታውን እንዲረዱ፣ ስለእምነታቸው መጠየቅ እንዲጀመሩና እንዲያጠኑ በማሰብ የሚቀርብ ቀና ጥቆማ ብቻ ነው። በዚህ ሒደት ሳትረዱ የምትሳደቡ ሰዎችንም ከሌሎች ትምህርቶች ላለማገድ ብሎክ አላደርጋችሁም። አላማ ብላችሁ በየሁሉም ፖስት በመሳደብ የተሳዳቢነት መለያን ለራሳቸው ከሰጣችሁ ሰዎች በቀር በጥቂት ስድቦቻችሁ ማባረር አልፈልግም። አሁንም ኮንቴንቶችን በቀናነት አይታችሁ በቀረቡበት ጨዋ ደንብ መሠረት ለመሞገት፣ ካላወቃችሁም ለመጠየቅ ሞክሩ። ከዚያ በዘለለ ይህንን አይነት ትምህርት የሚቀርበው ሆን ተብሎ ለማስቀየምና ለብሽሽቅ መስሏችሁ ሀሳቡን በትኩረት እንዳትረዱ ሆናችሁ አእምሯችሁን እንዳትደፍኑ በቀናነት አደራ እላችኃለው።
2.0K views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ