Get Mystery Box with random crypto!

ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች doro erbta be Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ doro7589 — ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች doro erbta be Ethiopia
የቴሌግራም ቻናል አርማ doro7589 — ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች doro erbta be Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @doro7589
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.59K
የሰርጥ መግለጫ

ዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች , ዶሮ እርባታ በኢትዮጵያ pdf, ዶሮ እርባታ pdf, ዶሮ እርባታ, ዶሮ እርባታ ዘዴ, ዶሮ እርባታ ፕሮፖዛል, ዶሮ እርባታ በኢትዮጵያ, የ ዶሮ እርባታ
poultry farming ,poultry business plan,how to start poultry farming for beginnings ,yedoro erbataejemariwoch

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-22 08:02:50 ሁሌ እናተ ብቻ ናቹ እንዴ ጥያቄ ምጠይቁት
እስቲ እኔም ልጠይቃችሁ

ከምጠይቃችሁ ጥያቄ ምንያህሉን ትመልሳላችሁ

ምን ታስባላችሁ ልጠይቅ እንዴ? እስቲ ሀሳባችሁን
276 views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, edited  05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:56:04 ከእንስሳት የሚኙ አካል ገንቢ ንጥረ-ምግቦች
የተፈጨ ደም
• የተፈጨ ደም መኖ የሚዘጋጀው ደም ከደረቀ በኋላ በመፍጨት ነው፡፡ ተረፈ ምርቱ እስከ 8ዐ% የገንቢ ንጥረ መኖ
ይዘት አለው፡፡ በዶሮ መኖ ቀመር ውስጥ ከ2–4% ያልበለጠ ቢቀላቀል ጥሩ ውጤት ሊኝ ይችላል፡፡
የተፈጨ ሥጋ
• የተፈጨ ሥጋ መኖ የሚዘጋጀው የእንስሳት ሥጋ ተረፈ ምርት አድርቆ በመፍጨት ነው፡፡ ይህ መኖ ሲዘጋጅ የእንሰሳው
ፀጉር፣ሸኮና፣ቀንድ፣ፍግ፣ፈረስና የመሳሰሉት መቀላቀል የለባቸውም፡፡ የተፈጨ ሥጋ ከፍተኛ /55%/ የአካል ገኒቢ ንጥረ
ምግብ ይዘት አለው በካልሲየም እና ፎስፈረስ የበለፀገ ነው፡፡ እርጥበት አዘል የአየር ፀባይና ሙቀት ባለበት ቦታ ተረፈ
ምርተ ቆሎ የመበላሸት ባህርይ ስላለው በደረቅና ቀዝቃዛ ቦታ መቀመጥ አለበት፡፡
የተፈጨ ሥጋና አጥንት
• ከተፈጨ ሥጋ ጋር ተመሣሣይ ሲሆን የሚለየው ከፍተኛ የሆነ የአጥንት ይዘት ስላለው ነው፡፡ ስለሆነም ተረፈ ምርቱ
በፎስፈረስ እና በካልሲየም ይዘቱ በጣም የበለፀገ ነው፡፡ የፎስፈረስ ይዘቱ ከ4% በላይ ሲሆን፣5ዐ% የሚሆን የገንቢ
ንጥረ መኖ ይዘት አለው፡፡
የተፈጨ አጥንት
• ከተፈጨ አጥንት መኖ የሚዘጋጀው መጀመሪያ አጥንቱን በትንት ሃይል በመቀቀል ከበቂ በላይ የሆነውን ስብና ሥጋ
ማስወገድና የተቀቀለውንና ተሰባሪ የሆነውን አጥንት በመፍጨት ነው፡፡ ይህ ተረፈ ምርት የካልሲየምና ፎስፈረስ
ምንጭ በመሆን ያገለግላላ፡፡ የአጥንት መኖ ከ30–35% ካልሲየምና 15% የፎትፈረስ ይዘት አለው፡፡

የተፈጨ አሳ (የአሳ ተረፈ-ምርት)
• የተፈጨ አሳ ከሙሉ አሳ ወይም ከተረፈ ምርት/ኦፋል/ ሊዘጋጅ ይችላል፡፡ የተፈጨ አሳ ከ0–4 ሣምንት እድሜ
ላላቸው የሥጋ ዶሮዎች እስከ 1ዐ% በድብልቁ ውስጥ የሚቀላቀል ሲሆን፣ለእንቁላላ ጣይ ዶሮዎች ደግሞ ከ3–5%
መቀላቀል ይችላል፡፡ ተረፈ ምርቱ ጥሩ የማዕድን ይዘት ሊኖረው፣ለዶሮዎቹ የተሻለ የተበይነት ባህርይም አለው፡፡
የተፈጨ የአሳ ተረፈ ምርት በገንቢ ንጥረ መኖ ይዘቱ በጣም የበለፀገ ስለሆነ ለዶሮዎቹ እድገት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡
ይህ ምርት በጣና ሐይቅ አካባቢ በከፍተኛ ስለሚመረት በአግባቡ መጠቀም ይቻላላ፡፡ አዘገጃጀቱን በተመለከተ የራሱ
701 views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, edited  10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:54:04 የስንዴ ፉርሽካ
• ይህ የዱቄት ማምረቻ ፋብሪካዎች ስንዴን ለዱቄት ሲባል በሚፈጩበት ጊዜ በተረፈ ምርትነት የሚወጣ ሲሆን ሸካራ
የሆነውን የውጭውን ስንዴ ሽፋን የያዘ ነው፡፡ ፉርሽካ የሃይል ሰጪ ንጥረ-ምግብ ይዘቱ አነስተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም
የቃጫ ይዘቱ ከፍተኛ ስለሆነ በመኖው ውስጥ የሚጨመረው መጠን አነስተኛ ነው፡፡

የስንዴ ፉርሽኬሎ
ይህም የዱቄት ማምረቻ ፋብሪካዎች ስንዴን ለዱቄት ሲባል በሚፈጩበት ጊዜ በተረፈ ምርትነት የሚወጣ ሌላው
ተረፈ-ምርት ነው፡፡ ፉርሽኬሎ ከፉርሽካ ቀጥሎ የሚመጣ ሲሆን በውስጡም ደቃቅ ፉርሽካ እና አነስተኛ የዱቄት
መጠን የያዘ ነው፡፡ ፉርሽካ የሃይል ሰጪ ንጥረ-ምግብ ይዘቱ ከፉርሽካ የተሻለ ነው፡፡ በተጨማሪም የቃጫ ይዘቱ
ከፉረሽካ የተሻለ ስለሆነ በመኖው ውስጥ የሚጨመረው መጠን ትንሽ ከፍ ያለ ነው፡፡
የስንዴ ሚድሊንግ
ይህ በይዘቱ ከፉርሽካ እና ከፍሩሽኬሎ መካከል የሚኝ ተረፈ ምርት በመሆኑ በማንኛውም ንጥረ ምግብ ይዘቱ በሁለቱ
ውጤቶች መካከል ይገኛል፡፡ የቃጫ ይዘቱ ከፍሩሽካ ያነሰ በመሆኑ ለዶሮዎች መኖነት ከፍሩሽካ በበለጠ መጠን
ሊደባለቅ ይችላል፡፡
686 views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, edited  10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:49:35
655 views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, 10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 13:48:21 5000 followers ስንገባ የ1000 ሺህ ዶሮ ወራዊ ትርፍ ፅፍለው
641 views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:50:00 ዒድ ሙባረክ!
1.1K views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 20:39:58 የኪሳራ ጥሩ የለውም!!! ወንድማችን ከላይ ከተፃፈው ውስጥ የተቃወመው ነው

የግል ሀሳቤ ነው
ዶሮ እርባታ ውስጥ ኪሳራ የማይደርስበት ዶሮ አርቢ የለም ብዙ ልምድና እውቀትን ያካበቱ የዶሮ አርቢዎች ለእኔም አርያ ሊሆኑ የሚችሉ ሰዋችን አውቃለሁ

ብዙ የኪሳራ አይነቶች አሉ እኔ ላይ የደረሱም በሰዎችም ያየሁት ዘርዝራቸው ይጠቅማሉ አላችሁኝ ከልምድ አካፍላለሁ


እኔን ሰው ያደረገኝ ከፈጣሪ በታች ኪሳራ ነው
ኪሳራ ትምርትነው
ኪሳራ ፅናት ነው
ድፍረት ነው
ልምድ ይሆናል
ባጠቃላይ ሁላችንም ላለመክሰር እንሰራለን የሆነ ወቅት ላይ ግን ኪሳራ ይመጣል መጠኑ ቢለያይም በእናንተ ጥፋትም ላይሆን ይችላል

ኪሳራ መፍራት ማማረር መጥፎ ብሎ ማሰብ የቀረ ይመስለኛል በርቱ
ስለሰጠኸኝ አስተያየት እያመሰገንኩ
1.1K views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, edited  17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:15:35
1.1K views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, 13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 16:12:40 በጥያቄያቹ መሰረት የጫጬቶችን አስተዳደግ እንመለከታለን

መሠረታዊ የጫጬት አያያዝ ግብዓቶች
ዝርያ ቦቫንስ
እድሜ የ1ቀን
ብዛት 3000
ጫጬቶች ወደ እርባታ ከመግባታቸው በፊት

የቤቱ ጣሪያ ግድግዳ ወለል በደረቁ ከተጠረገ በውኋላ
በንፁህ ውሀ መጠብ
ፀረ ጀርም መርጨት
ከደረቀ በውኋላ ጭድ መጎዝጎዝ
የጫጬት መመገቢያ መጠጫ:መከለያ መድኀኒት መርጨት
በንፁህ ውሀ ማጠብ
ማሞቂያ ይጋጠማሉ መስራቱም ይረጋገጣል
በመከለያው ዙሪያ በቂ መጠጫ መኖር አለበት
ጫጬትቶች ከመግባታቸው በፊት ማሞቂያ ይለኮሳል
የሙቀት አሰጣጡም በክረምት 24ሰዓት በበጋ 6በቂነው
crumble feed ማዘጋጀት
ጫጬቶች ከገቡ ከ1 በውኃላ ቢመገቡ ይመረጣል
2%የሚሆኑትን ጫጬቶች መመዘን
አንቲባዮቲክ
የጫጬት አመጋገብ 0-21 starter feed
22-38 rearing feed
መኖ የ15 ቀን ብቻ ይገዛል
መጠጫ በቀን 3 ጊዜ ይታጠባል
መመገቢያ በሳምንት 2 ጊዜ ይታጠባል
የጫጬት መኖ የጥራት ደረጃ 22%cp
3100 kcal

ጥንቃቄ የመጀመሪያዎቹን 3 ቀናት ከፍተኛ መደራረብ ይኖራል
ወረርሽኝ ከድርጅቶቹ ሊመጣ ስለሚችል ለዛም መዘጋጀት
ልምድን የሚጠይቅ በመሆኑ ልምድ ወይም ስልጠና ብትወስዱ
ጥሩ ትርፍ አለው ጥሩ ኪሳራም አለው
ቦታ አመራረጥ ላይ ትኩረት ይፈልጋል
የጫጬት ወረፋ መረሳት የለበትም ለሱም ቀድማችሁ ተመዝገቡ

እናመሰግናለን በቀጣይ ስለ ምን እንስራ ፃፉ

ድጋፍችሁ ያስፈልገናል

የዶሮ እርባታ ለጀማሪዎች የቴሌግራም ችናል doro7589
1.1K views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, edited  13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 14:38:37 ቀጣይ ስለምን ይሰራ? ለሁሉም ይጠቅማል ያስተምራል የምትሉትን ለይክ አድርጉ
1.3K views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, edited  11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ