Get Mystery Box with random crypto!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የቴሌግራም ቻናል አርማ yahya5 — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የቴሌግራም ቻናል አርማ yahya5 — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የሰርጥ አድራሻ: @yahya5
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.26K
የሰርጥ መግለጫ

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-18 20:47:30
በዛሬው እለት አዲስ የተመረጠውን መጅሊስ በተመለከተ የተወሰነ ነገር ማለት አስፈላጊ ነውና ከዚህ በታች የሚሰማኝን ለመግለጽ ልሞክር፦
..
1/ አዲሱ መጅሊስ የተቀበለው "ሥልጣን" የሚመስለው ሰው ካለ ትልቅ ስህተት ነው። የተቀበለው ከባድ ሸክምና ኃላፊነት ነው። ያውም ብዙ ውስብስብ ጥያቄዎች ያሉበትን ህዝብ የመምራት ኃላፊነት..! ይህ ህዝብ መሠረታዊ መብቶቹን እንኳን ለመጠየቅ ለዘመናት መከራውን ከማየቱ ብዛት እጅግ የተሰላቸ በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ችላ ማለት የሚችልበት ጊዜ ላይ አይደለም። ይህንን የማኅበረሰቡን አውድ አዲሱ ተመራጭ አካል በደንብ መረዳት ይኖርበታል ብየ አስባለሁ።
..
2/ ነጮቹ "The most dangerous place in your carer is the comfort zone" ይላሉ። ምቾት አጉል የሚያደርግ የስራ ጸር ነው። ምቾትን ተማምኖ መተኛት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል። ከነገዋ ቀን ጀምሮ ስልጣናቸውን እስከሚያስረክቡባት ቀን ድረስ ያለችው እያንዳንዱ ሰአት እጅግ ወሳኝ የሆኑ ታሪኮችን ሰርተው የሚያልፉባቸው ጊዜያት ናቸው። ከመሠረታዊ የተቋም ስራ ውጭ ባሉ የቸልታና የድግስ ጊዜያት እድሎች የሚያልፉ ከሆነ ግን በአሏህ ፊት ከዚያም በታች በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አያድንም።
..
እነዚህን ከላይ ያሉ ነጥቦች ያነሳሁት የተመረጡ ሰዎች ይጠፋቸዋል በሚል አይደለም፤ ማስታወስ ግን መልካም ነው። ነገ ተስፋ እንዳደረግነው ከተሰራ ማመስገናችን፣ ማገዛችንና ዱዓ ማድረጋችን አይቀርም። በተቃራኒው ከሆነ ደግሞ መጠየቃችን መተቸታችንና ተጠያቂነት እንዲሰፍን መታገላችን ግን የሚቀር አይደለም። ብዙ ተስፋ አድርገናልና ፈጽሞ እንደማናፍር ሙሉ እምነታችን ነው። አሏህ ﷻ በልፋታቸው በውሳኔያቸው ሁሉ ከጎናቸው እንዲሆንም ዱዓችን ነው..!
---------------------
T.me/Yahya5
1.3K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 12:59:05
ጎንደር ለንጹሀን ፍትሀት አደረገች..?! ትላንት ጾመኛ ሙስሊሞች በግፍ የተገደሉባት ጎንደር በሌላ ቦታ የሚኖሩ ንጹሀን መገደላቸው ይበልጥ ልቧን ነክቶት ሀዘኗን እየገለጸች ነው..! በሌላ ቦታ የተገደሉ ሰዎች ከከተማ ገጽታ አንፃር ጎንደርን አያሰጋትምና ሀዘኗ እጥፍ ድርብ ሁኗል..! አሳዛኝ ጊዜ
2.0K views09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 16:34:33 የማኅበሩን ሰዎች በአለማዊ የልሒቅነት ከባ ለማምጣት የሚውተረተረው የኔታ ቲዩብ ፈንታሁን ዋቄን አይነት ሰው "ወርቃማ ሀሳብ" አለው ብሎ ሊቀልድብን ይሞክራል። የሞዓ ግብረ ኅይል አደራጅ የሆነው መምህር ፈንታሁን ዋቄ የሲኖዶሱ መንበር አራት ኪሎ ቤተ መንግስት እንዲሆንለት የሚተጋ ፖለቲካና እምነት ድንበሩ የተቀባዠረበት ሰው ነው።
..
ምንም ሳያፍር ነገስታቱ በካህናት ተቀብተው መሪ ሊሆኑ እንደሚገባ የሚደሰኩር ብዝሀነትን የተጸየፈ ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ በየኔታ ቲዩብ ላይ ግን "ወርቃማ ሀሳብ" አለው ተብሎ በተከታታይ በጀትና ሰአት ተመድቦለት ይቀርባል። አብዛኛው የሚያወራው ነገር ለቂል ሰዎች ሳቢ የሆኑ የኮንስፓይሬሲ ትንተናዎችን ሲሆን በዚያ ንግግሩ አስታኮ ግን ሀገሪቱ ያለችበተ የሴኩላሪዝም መርህን በመቃወም ሀገራት "ሀይማኖታዊ/ ኦርቶዶክሳዊ መንግስት" ቢኖራቸው ምን ያክል "መልካም" እንደሆነ ሊያሳምነን ይታገላል።
..
በዚህ መድረክ ላይ ባላንስ ለመስራት በሚል ከፕሮቴስታንት ዶ/ር ወዳጄነህ እንዲቀርብ ተደርጓል። የሚገርመው ነገር ዶ/ር ወዳጄነህ አሁን ላይ እራሱን እንደ ፕሮቴስታንት የማይቆጥር ይህንንም በይፋ የሚናገር ከመሆኑ በተጨማሪ ስለማርያም በጻፈው መጽሀፉ በኦርቶዶክሱ ዘንድ ትልቅ ቦታን ያገኘ ሰው ነው። አስቡት እንግዲህ ከኦርቶዶክሱ በኩል ፈንታሁንን ለሚያክል ግለሰብ ባላንስ እንኳን እንዲሆን የተመረጠው ሰው አሁንም የሌላ እምነት ውስጥ ያለ ሰው ይምሰል እንጅ ለኦርቶዶክስ Affilation ያለው ሰው ነው።
..
ሰዎቹ በተጠና መንገድ እንሰራዋለን ብለው የሚያስቡት ስራ ህዝቡን ስለሚንቁ የማይነቃባቸው ይመስላቸዋል። እውነታው ግን አንድን አጀንዳ ቀርጸው ሲሰሩና በዚያ ሀሳብ ዙሪያ ባለሙያ ሲመድቡ ሁሉ ዋነኛ አላማቸው የጽንፈኞቹ የሀይማኖታዊ ዝንባሌ ያለው መንግስት እንዲኖር የሚያልመውን አካል አለዝቦና አጣፍጦ የማቅረብ ስራ ነው።
---------------------
T.me/Yahya5
2.6K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 16:34:25
2.3K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:08:08
በየኔታ ቲዩብ የጋዜጠኛ እጥረት ካለ ያለምንም መቸገር ከማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ መዋስ ካስፈለገም የውስጥ ዝውውር ማድረግ ይችላሉ። የቤተ ክርስቲያኗ ቲቪ ላይ ብቻ መስራት ሀገሪቱን የተመለከቱ ተሳትፎዎች ላይ ይገድባል ብሎ የሚያምን ጋዜጠኛ ካለም ምንም መቸገር አይጠበቅበትም። ለዚሁ አላማ ተብሎ የተዘጋጀው ይህ የኔታ የተሰኘ ሚዲያ ውስጥ ሲቪውን አስገብቶ በጥሩ ደሞዝ መስራት ይችላል። እንዳልኳችሁ ፋይናንሱ ጠንካራ ከመሆኑ አንፃር የሚከፍሉት ደሞዝም ለመጥራት እራሱ የሚያሳቅቅ ነው። ከተቀጣሪዎች የሚጠበቀው የሚዲያውን አላማ ለማሳካት ወጥሮ መልፋት ብቻ ነው።
..
ከታች በምስሉ ላይ ያለው ሙሉዬ ምስጋናው የተሰኘ ጋዜጠኛ ምናልባት ብዙ ሰው የሚያውቀው ማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ ላይ ለብዙ ጊዜያት በመስራቱ ነው። ነገር ግን ጋዜጠኛው ከማኅበረ ቅዱሳን በር እግሩ እንደወጣ ደግሞ ሀይማኖታዊ ካባውን ጣል አድርጎ የኔታ ቲዩብ ላይ ሚዲያው የሚሰጠውን ስራ ተቀብሎ ይሰራል። በዚህ መልኩ ተመጋጋቢ ሁኖና ቅድም እንዳልኳችሁ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ፖለቲካን ላነገቡ አካላት እንቅስቃሴያቸውን ኖርማላይዝ በማድረግ በኩል ለውጭው አካል በማሳየት ተልዕኳቸውን ይፈጽማሉ።
..
---------------------
T.me/Yahya5
2.8K views14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 17:07:46
በየኔታ ሚዲያ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን ኢንተርቪው ሲያደርግ የምትመለከቱት ይህ ግለሰብ እጅግ በጣም ጽንፈኛ የኦርቶዶክስ አማኝ ሲሆን በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እስልምናንና ፕሮቴስታንትን አስመልክቶ ሲያወራ ጥላቻውና ቢያዙን መደበቅ እንኳን የማይችል Incompetent ግለሰብ ነው። ግለሰቡን ጋዜጠኛ ማለት በጣም የሚከብድ ሲሆን አጀንዳ ከሚያደርጋቸው ኢሹዎች ጀምሮ እንግዳዎቹን አቅርቦ እስከሚጠይቃቸው ጥያቄዎች ድረስ በሚያስቅ ሁኔታ ምን እንዲመለስለት ፈልጎ እንደጠየቀ የሚያሳብቁ ጆላጅል ጥያቄዎች ናቸው።
..
በዋናነት የኔታ የተሰኘውን የፌስቡክ ፔጅ በትኩረት ለተከታተለ ሰውም ከኦፊሺያል የሚዲያ ገጽነት ይልቅ የግለሰቡ ሀሳቦች ማራገፊያ እንደሆነ ይረዳል። የኔታ ላይ ሙስሊም ጠል ጹሁፎች ከሳቅ ኢሞጂዎች ጋር ከተመለከታችሁ ብዙም መገረም አይጠበቅባችሁም። ቅድም እንዳልኳችሁ ሚዲያው እንዲሆን ተፈልጎ የተሰራበት ዋነኛው ቅርጽ ይኸው አላማ ነው። ስለፕሮቴስታንቱ ሰባኪ ፓስተር ዮናታን ከሰሞኑ የለጠፉት ተራ ላግጣ ኮሜንት ላይ አስቀምጨላችኃለው።
---------------------
T.me/Yahya5
2.4K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 13:59:39
የኔታ ቲዩብ የተሰኘው ሚዲያ ከ1.8 ሚሊየን በላይ ተከታታዮች ያሉትና ሰፊ ፋይናንስ የሚያንቀሳቅስ የሚዲያ ተቋም ነው። ሚዲያውን ስፖንሰር በማፈላለግና የሚዲያ ቁሳቁስ በማሟላት የሚያግዘው አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን አለ። በዋናነት ሚዲያው የተቋቋመውና አላማ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው በሀይማኖት ረገድ ሙስሊሙንና ፕሮቴስታንቱን ለማጠልሽት ነው። በሁለቱ እምነቶች በኩል የሚፈጠሩ አዲስ አጀንዳዎች ካሉ ከማንም ቀድሞ የሚያራግውበና አንዳንዴም ያለምንም ሀፍረት ያፈጠጡ ጥላቻዎችን የሚያሰራጨው ይህ ሚዲያ ነው።
..
በሚዲያው ውስጥ እየቃመና እየሰከረ የሚቀርብ ስዩም ተሾመ የተሰኘ ግለሰብ አለ። ይህ ግለሰብ በሀገሪቱ ውስጥ ከጠቅላይ ሚንስትሩና ጥቂት ግለሰቦች ውጭ ያሻውን ሰው መርጦ እንዲሳደብና ስም እንዲያጠፋ ፍቃድ ተሰጥቶታል። በዚህ ሚዲያ ስሙ የጠፋ የትኛውም አካል ስዩምን መክሰስ አይችልም። የፈለገ ትልቅ ባለስልጣን እንኳን ቢሆን ስዩምን ለመክሰስ ካመለከተ በተለያዩ ሰበቦች ክሱን እንዲያቆም ይነገረዋል። ሚዲያው አላማው ዘርፈ ብዙ ቢሆንም በሀይማኖት ረገድ ግን የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከአጥሯ አውጥቶ በፖለቲካው ረገድ የሚኖራትን ተሳትፎ ኖርማላይዝ ማድረግ ነው።
..
ስለ የኔታ መነገር ስላለበት ከነጋዜጠኞች ማንነት ሳይቀር በደንብ ስለማቃቸው እየዘረዘርኩ እቀጥላለሁ
---------------------
T.me/Yahya5
4.0K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:34:16
ወንድማችን አብዱልጀሊል ፌስቡክ ተደጋጋሚ እገዳዎች እየጣለበት ለመጻፍ ተቸግሯል። በዚህ የቴሌግራም አድራሻው ተከታተሉት፦
..
https://t.me/abduljelilshekhalikassa
3.7K views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 20:47:04
ነብዩሏህ ኑህ عليه السلام እንስሳትን አንድ ጊዜ ብቻ ወደ መርከቡ ሲጠሯቸው ተከትለውት ተሳፈሩ። ለ950 ዓመታት ሰዎችን ወደ አሏህ ﷻ ሲጠሩ ግን አብዛኞቹ በመንገዱ ለመሳፈር ፈቃደኛ አልሆኑም ነበር።
..
አንዳንዴ በደመ ነፍስ የሚኖረው እንስሳ በባዶው ከሚራቀቅ ምሁር የተሻለ ነው።
..
---------------------
T.me/Yahya5
3.5K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 13:59:30
በዲን ስራ ውስጥ ኢኽላስን ከሚያሳጡ ጉዳዮች አንዱ ከአላህ ﷻ ውጭ ሌላ ነገርን ስንቀላቅልበት ነው። በዲን ስራ ውስጥ መሰባሰባችን ሁሉ መሠረቱ አኼራ እንጅ ዱንያዊ ግብ ሊኖረው አይገባም። በዚያ መልኩ የገነባነው ነገር ፍሬው ያነሰና ግቡም የተዛባ መሆኑ አይቀርም።
..
ይህንን በተመለከተ ኡስታዝ ማሕሙድ በአፍሪካ ቲቪ ካቀረበው ትምህርት ውስጥ ጠቃሚ ነው ብየ ያመንኩትን ክፍል በሚከተለው መልኩ አጋርቻችኃለው።
9.1K views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ