Get Mystery Box with random crypto!

በየኔታ ቲዩብ የጋዜጠኛ እጥረት ካለ ያለምንም መቸገር ከማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ መዋስ ካስፈለገም የውስ | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

በየኔታ ቲዩብ የጋዜጠኛ እጥረት ካለ ያለምንም መቸገር ከማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ መዋስ ካስፈለገም የውስጥ ዝውውር ማድረግ ይችላሉ። የቤተ ክርስቲያኗ ቲቪ ላይ ብቻ መስራት ሀገሪቱን የተመለከቱ ተሳትፎዎች ላይ ይገድባል ብሎ የሚያምን ጋዜጠኛ ካለም ምንም መቸገር አይጠበቅበትም። ለዚሁ አላማ ተብሎ የተዘጋጀው ይህ የኔታ የተሰኘ ሚዲያ ውስጥ ሲቪውን አስገብቶ በጥሩ ደሞዝ መስራት ይችላል። እንዳልኳችሁ ፋይናንሱ ጠንካራ ከመሆኑ አንፃር የሚከፍሉት ደሞዝም ለመጥራት እራሱ የሚያሳቅቅ ነው። ከተቀጣሪዎች የሚጠበቀው የሚዲያውን አላማ ለማሳካት ወጥሮ መልፋት ብቻ ነው።
..
ከታች በምስሉ ላይ ያለው ሙሉዬ ምስጋናው የተሰኘ ጋዜጠኛ ምናልባት ብዙ ሰው የሚያውቀው ማኅበረ ቅዱሳን ቲቪ ላይ ለብዙ ጊዜያት በመስራቱ ነው። ነገር ግን ጋዜጠኛው ከማኅበረ ቅዱሳን በር እግሩ እንደወጣ ደግሞ ሀይማኖታዊ ካባውን ጣል አድርጎ የኔታ ቲዩብ ላይ ሚዲያው የሚሰጠውን ስራ ተቀብሎ ይሰራል። በዚህ መልኩ ተመጋጋቢ ሁኖና ቅድም እንዳልኳችሁ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ ፖለቲካን ላነገቡ አካላት እንቅስቃሴያቸውን ኖርማላይዝ በማድረግ በኩል ለውጭው አካል በማሳየት ተልዕኳቸውን ይፈጽማሉ።
..
---------------------
T.me/Yahya5