Get Mystery Box with random crypto!

በዛሬው እለት አዲስ የተመረጠውን መጅሊስ በተመለከተ የተወሰነ ነገር ማለት አስፈላጊ ነውና ከዚህ በ | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

በዛሬው እለት አዲስ የተመረጠውን መጅሊስ በተመለከተ የተወሰነ ነገር ማለት አስፈላጊ ነውና ከዚህ በታች የሚሰማኝን ለመግለጽ ልሞክር፦
..
1/ አዲሱ መጅሊስ የተቀበለው "ሥልጣን" የሚመስለው ሰው ካለ ትልቅ ስህተት ነው። የተቀበለው ከባድ ሸክምና ኃላፊነት ነው። ያውም ብዙ ውስብስብ ጥያቄዎች ያሉበትን ህዝብ የመምራት ኃላፊነት..! ይህ ህዝብ መሠረታዊ መብቶቹን እንኳን ለመጠየቅ ለዘመናት መከራውን ከማየቱ ብዛት እጅግ የተሰላቸ በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚታዩ ክፍተቶችን ችላ ማለት የሚችልበት ጊዜ ላይ አይደለም። ይህንን የማኅበረሰቡን አውድ አዲሱ ተመራጭ አካል በደንብ መረዳት ይኖርበታል ብየ አስባለሁ።
..
2/ ነጮቹ "The most dangerous place in your carer is the comfort zone" ይላሉ። ምቾት አጉል የሚያደርግ የስራ ጸር ነው። ምቾትን ተማምኖ መተኛት ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል። ከነገዋ ቀን ጀምሮ ስልጣናቸውን እስከሚያስረክቡባት ቀን ድረስ ያለችው እያንዳንዱ ሰአት እጅግ ወሳኝ የሆኑ ታሪኮችን ሰርተው የሚያልፉባቸው ጊዜያት ናቸው። ከመሠረታዊ የተቋም ስራ ውጭ ባሉ የቸልታና የድግስ ጊዜያት እድሎች የሚያልፉ ከሆነ ግን በአሏህ ፊት ከዚያም በታች በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን አያድንም።
..
እነዚህን ከላይ ያሉ ነጥቦች ያነሳሁት የተመረጡ ሰዎች ይጠፋቸዋል በሚል አይደለም፤ ማስታወስ ግን መልካም ነው። ነገ ተስፋ እንዳደረግነው ከተሰራ ማመስገናችን፣ ማገዛችንና ዱዓ ማድረጋችን አይቀርም። በተቃራኒው ከሆነ ደግሞ መጠየቃችን መተቸታችንና ተጠያቂነት እንዲሰፍን መታገላችን ግን የሚቀር አይደለም። ብዙ ተስፋ አድርገናልና ፈጽሞ እንደማናፍር ሙሉ እምነታችን ነው። አሏህ ﷻ በልፋታቸው በውሳኔያቸው ሁሉ ከጎናቸው እንዲሆንም ዱዓችን ነው..!
---------------------
T.me/Yahya5