Get Mystery Box with random crypto!

የማኅበሩን ሰዎች በአለማዊ የልሒቅነት ከባ ለማምጣት የሚውተረተረው የኔታ ቲዩብ ፈንታሁን ዋቄን አይ | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የማኅበሩን ሰዎች በአለማዊ የልሒቅነት ከባ ለማምጣት የሚውተረተረው የኔታ ቲዩብ ፈንታሁን ዋቄን አይነት ሰው "ወርቃማ ሀሳብ" አለው ብሎ ሊቀልድብን ይሞክራል። የሞዓ ግብረ ኅይል አደራጅ የሆነው መምህር ፈንታሁን ዋቄ የሲኖዶሱ መንበር አራት ኪሎ ቤተ መንግስት እንዲሆንለት የሚተጋ ፖለቲካና እምነት ድንበሩ የተቀባዠረበት ሰው ነው።
..
ምንም ሳያፍር ነገስታቱ በካህናት ተቀብተው መሪ ሊሆኑ እንደሚገባ የሚደሰኩር ብዝሀነትን የተጸየፈ ግለሰብ ነው። ይህ ግለሰብ በየኔታ ቲዩብ ላይ ግን "ወርቃማ ሀሳብ" አለው ተብሎ በተከታታይ በጀትና ሰአት ተመድቦለት ይቀርባል። አብዛኛው የሚያወራው ነገር ለቂል ሰዎች ሳቢ የሆኑ የኮንስፓይሬሲ ትንተናዎችን ሲሆን በዚያ ንግግሩ አስታኮ ግን ሀገሪቱ ያለችበተ የሴኩላሪዝም መርህን በመቃወም ሀገራት "ሀይማኖታዊ/ ኦርቶዶክሳዊ መንግስት" ቢኖራቸው ምን ያክል "መልካም" እንደሆነ ሊያሳምነን ይታገላል።
..
በዚህ መድረክ ላይ ባላንስ ለመስራት በሚል ከፕሮቴስታንት ዶ/ር ወዳጄነህ እንዲቀርብ ተደርጓል። የሚገርመው ነገር ዶ/ር ወዳጄነህ አሁን ላይ እራሱን እንደ ፕሮቴስታንት የማይቆጥር ይህንንም በይፋ የሚናገር ከመሆኑ በተጨማሪ ስለማርያም በጻፈው መጽሀፉ በኦርቶዶክሱ ዘንድ ትልቅ ቦታን ያገኘ ሰው ነው። አስቡት እንግዲህ ከኦርቶዶክሱ በኩል ፈንታሁንን ለሚያክል ግለሰብ ባላንስ እንኳን እንዲሆን የተመረጠው ሰው አሁንም የሌላ እምነት ውስጥ ያለ ሰው ይምሰል እንጅ ለኦርቶዶክስ Affilation ያለው ሰው ነው።
..
ሰዎቹ በተጠና መንገድ እንሰራዋለን ብለው የሚያስቡት ስራ ህዝቡን ስለሚንቁ የማይነቃባቸው ይመስላቸዋል። እውነታው ግን አንድን አጀንዳ ቀርጸው ሲሰሩና በዚያ ሀሳብ ዙሪያ ባለሙያ ሲመድቡ ሁሉ ዋነኛ አላማቸው የጽንፈኞቹ የሀይማኖታዊ ዝንባሌ ያለው መንግስት እንዲኖር የሚያልመውን አካል አለዝቦና አጣፍጦ የማቅረብ ስራ ነው።
---------------------
T.me/Yahya5