Get Mystery Box with random crypto!

ድንቃ-ድንቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ denkadenq — ድንቃ-ድንቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ denkadenq — ድንቃ-ድንቅ
የሰርጥ አድራሻ: @denkadenq
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 530
የሰርጥ መግለጫ

እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ አነቃቂ እና አዝናኝ እንዲሁም ከየትም የማይገኙ መረጃዎችን ይኮምኩሙ።

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-19 13:40:45
አሁን ደግሞ ሰለዚህ ሰውዬ እናጣራለን 2015 ላይ ኑሮ 2018 የአለም ዋንጫ ዘሎ እንዴት የ 2022 የአለም ዋንጫን አርጀቲና ከሚሲ ጋር ሁና ትበላለች ብሎ እንደፖሰት ይንገረን አልያም የጊዜ ተጓዥ(time travler) መሆኑን ይመንልን .....ጭራሽ ከ7 ዓመት በዋላ ታያላቹ ብሎ ፎኩሯል
115 views10:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-17 13:14:43 እጅግ ብዙ አስደናቂ እና ሰምተንም አይተንም የማናውቃቸው ድንቃ ድንቅ መረጃዎችን እዚህ https://t.me/denkadenq ቻናል ላይ ታገኛላችሁ። ግን ብዙዎቻችን ቻናሉን #Mute አድርገነዋል። Shareም እያደረግን አይደለም። ይቀጥል የምትሉ እስቲ አድርጉ እና አበረታቱኝ
255 views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 18:44:10 ኀብረ ቀለማትን አይተው መለየት የሚችሉት አጥቢ ፍጥረታት ሰውና ዝንጀሮ ብቻ ናቸው፡፡

የፍቅር ጓደኛቸውን ቀጠሮ አስይዘው የግብረ ሥጋ ግንኙነት በኘሮግራም የሚፈፅሙ ፍጥረታት ሰው አና ዶልፊን ብቻ ናቸው፡፡

ሙዚቃ ከሰዎች አልፎ እንስሳትን እና እፅዋትን ያስደስታል፡፡ ለምሳሌ የምትታለብ ላም ማራኪ ዜማ ከተከፈተላት መጠኑ በዛ ያለ ወተት ታመነጫለች፡፡ ፈረሶች ለስላሳ ሙዚቃ ያዝናናቸዋል፡፡ እንዲሁም ሙዚቃ የአበቦችን እድገትና ልምላሜ ያፋጥናል፡፡ ተሰብሮ ሊቀነጠስ የደረሰ አበባ ለስላሳ ሙዚቃ ከተከፈተለት እንደገና የመጠገን እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ስቃይ ሲዛባቸው ራሳቸውን በራሳቸው የሚገድሉ እንስሳት ሰው እና ጊንጥ ብቻ ናቸው፡፡
358 views15:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 16:15:20 ሰው፣ ጎሬላ፣ ዝንጀሮ ምን ያመሳስላቸዋል? . ምን ያለያያቸዋል?

ከት...ከት...ከት...! ብሎ መሣቅ የሚችል እና ሲስቅም የሚያምርበት ብቸኛ ፍጥረት ሰው ነው፡፥ ስለዚህ ሰው በመሆናችን ከልብ ልንደሰት ይገባል፡፡ አንዳንድ የሚስቁ የእንስሳት አይነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ እንደ ጀብ ና ዝንጀሮ ይጠቀሳሉ፡፡ ዳሩ ግን ሲስቁ የተናደዱ እንጂ የተደሰቱ አይመስሉም፡፡

ሳቅ በሽታን የመቋቋም አቅምን ይጨምራል፡፡ ካንሰርን ጨምሮ!!!

ሳቅ የሰው ልጆች ሚስጢራዊ የህመም ማስታገሻ ነው፡፡

ሲጣሉ እርስ በእርሳቸው የሚሰዳደቡ ፍጥረታት ጎሬላ አና ሰዎች ብቻ ናቸው።

የጎሬላ እና የሰው ልጅ ዘረ መል ወይም ዲ.ኤን.ኤ በ98 ፐርሰንት ደረጃ ይመሳሰላል፡፡

መሳርያ በመጠቀም አደን ላይ የሚሰማሩ ፍጥረታት ሰው እና ቺምፓ'ንዚ ብቻ ናቸው::

እርስ በርስ ቅማል በመቀማመል፣ አንዱ የሌላውን ፀጉር በማበጠር እና አንዱ ሌላውን በመኳኳል በጋራ የሚዋዋቡ ፍጥረታት ሰው፣ ዝንጀሮ እና ቺምፓንዚ ናቸው፡፡

በጀርባው መተኛት የሚችል ብቸኛው ፍጥረት ሰው ነው፡፡ ሰው በጀርባው ተኝቶ ሰርካታ ስራዎችንም መስራት ይችላል፡፡

ራሳቸውን በመስታወት አይተው መልካቸውን መለየት የሚችሉ ፍጥረታት ሰው እና ቺምፓንዚ ብቻ ናቸው፡፡
556 views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-15 19:53:02 #ሕይወትን እንደ ንሥር አሞራ ኑር

ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው ፍጡር ነው።

ሌሎች ቁራዎችና ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሆነው ከበው ሲጮሁበት ወደ ፀሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል። ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ፀሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋባቸዋል!!

- ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል፣
- ንስር ከ 2.30-3 ሜ ይረዝማል፣
- ንስር ከ5-7 ኪሎሜትር ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣
- ንስር ለአደን እስከ 120 ኪሎሜትር አካሎ ይበራል፣
- ንስር መጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሆኖ ኃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በመምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣

- ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣
- ንስር ሲታመም ፀሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣
- ንስር 340° ማየት ይችላል። ከ360° በአንድ እይታ 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣
- ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ። ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል።

የመጀመሪያው ፤ ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል፣
ሁለተኛው ፤ አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ (መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል፣
ሶስተኛው፤ ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።

እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?

የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።
ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።
፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።
፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡
፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል። ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡

ወዳጄ ሆይ:
ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ...ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡ... አትበል ፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የተሻለ ነገር ለመስራት ተነሳ!
338 views16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 07:58:33 #ጉጉት
- ጉጉት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ጥርት አድርጋ ማየት ትችላለች።
- ጉጉት አንገትዋን 270 ድግሪ ማዞር ትችላለች።
- ጉጉት አይኖቿን በፍጹም ማንቀሳቀስ አትችልም።
- ጉጉት ለ እለት ጉርሱ ሌሎች ትናንሽ ወፎችን ከነነፍሳቸው ይውጣል። ከ ጥቂት ሰዓታት በኋላ ግን ላባቸውን እንደ ኩስ አድበልብሎ ይተፋል ።
ጉጉቶች በተጨማሪ አይጦችን፣ አሳዎችን እና ነፍሳቶችን ይመገባሉ
- የ ጉጉቶች ክንፍ ለየት ያለ የላባ አቀማመጥ ስላለው የሚያድኑትን እንስሳ ለመያዝ ሲበሩ ክንፋቸው ምንም ድምፅ አያሰማም።
- የሰው ልጅ ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ የሚችሉ የጉጉት ዝርያዎች አሉ። ለምሳሌ:- በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ " January 2013" አንድ እስኮትላንዳዊ ወጣት 50 ሴንቲሜትር ርዝመት ባለው ጉጉት ጥቃት ደርሶበት አንድ አይኑን ሊያጣ ችሏል
- ዓለማችን ላይ 225 የጉጉት ዝርያዎች አሉ።
ትነሹ የ ጉጉት ዝርያ " elf owl" የሚባል ሲሆን ክብደቱ 31 ግራም ቁመቱ ደግሞ 13.5 ሴንቲሜትር ብቻ ነው።
ትልቁ የ ጉጉት ዝርያ ደግሞ " eagle owl" የሚባል ሲሆን ክብደቱ 4.2 ኪሎግራም ቁመቱ ደግሞ 190 ሴንቲሜትር ይደርሳል።
ምንጭ:- Wikipedia እና የዕውቀት ማህደር
463 views04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 20:04:02 ይህንን ያውቁ ኖሯል

➟ የአለም ጊነስ ቡክ ላይ በሪከርድነት ለመመዝገብ ሲባል ብቻ በ24 ሰአታት ውስጥ 23,069 ደቡብ አፍሪካውያን ፀጉራቸውን በምላጭ ተላጭተዋል፡፡

➟ ኔዘርላንድ(ሆላንድ) በወንጀለኞች እጥረት ምክንያት 8 እስር ቤቶችን ዘግታለች፡፡

➟ "ትምህርት ቤት(𝐒𝐂𝐇𝐎𝐎𝐋)" የሚለው ቃል"𝐒𝐊𝐇𝐎𝐋𝐄" ከሚለው ጥንታዊ የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ነፃ ጊዜ ወይም ትርፍ ሰአት ማለት ነው፡፡
672 views17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 19:58:31 ይህንን ያውቁ ኖሯል

➟ የሰውነታችን አካል የሆነው ሳንባችን 83% ያህሉ ውሀ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደረቅ የሚመስለው አጥንታችን ደግሞ 31% ያህሉ ውሀ ነው፡፡

➟ በሀገረ አሜሪካ በህክምና ስህተት ምክንያት በየአመቱ ከ250,000 በላይ ሰዎች ይሞታሉ፡፡

➟ የVaseline ፈጣሪ Robert Chesebrough ይባላል፡፡ Robert Chesebrough ፈጠራውን ከመውደዱ የተነሳ በየቀኑ አንድ ማንኪያ ቫስሊን ይበላ ነበር፡፡
608 views16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 20:01:43
746 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 19:59:09 ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤት ማየት ላልቻላችሁ ከስር ባለው comment መስጫ ይጻፉልን ወዲያው inbox እንልካለን።
717 views16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ