Get Mystery Box with random crypto!

የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የቴሌግራም ቻናል አርማ yahyanuhe — የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe
የሰርጥ አድራሻ: @yahyanuhe
ምድቦች: እንስሳት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.06K
የሰርጥ መግለጫ

﷽ | Muslim | Theology | Comparative Religion | Philosophy | Student | Teacher |

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-02-05 14:51:45
ከመንግስት አካል ጋር ያለውን ጠብ በተቻለ መጠን በራሳችሁ መንገድ እዚያው ለመፍታት ሞክሩ። በዚህ መሀል መስሊሙ ምንም የሚያገባው ነገር የለም። በጉዳዩ ውስጥ ደም ለማፍሰስ አይደለም ጎራ ለይቶ አስተያየት ለመስጠትም አያስፈልገውም። በግድ ጠላት የማብዛት ስትራቴጂም ለምን እንደምትከተሉ አይገባኝም፥ በቂ ጠላት አላችሁ የማይመለከተውን ሁሉ እየጎተታችሁ ሚስኪን ስለመግደል አትዘባበቱ። ይህ ዛቻ የት አካባቢ እንደሚፈጸም ከልምድ ስለምናውቀው ትንሽም ቢሆን ማስጠንቀቅ ይኖርብናል። ከ300 ሺ በላይ ተከታታይ ያለው፣ ከፓትርያርኩ ጀምሮ የፈለገው ሊቃነ ጳጳሳት ጋ በቀላሉ በስልክ ማነጋገር የሚችል አልፎም አንዳንዴ መልዕክት በደብዳቤ የሚቀበልና የሚያደርስ ሲያሻውም ሙልጭ አድርጎ በዱርየ ቃላት የሚሳደባቸውና "ጎሽ" የሚሉ በርካታ መንጋዎች ያሉት ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነው። በቅስቀሳው ብዙ ምዕመን ዘንድ የሚደርስ ግለሰብም ጭምር ነውና በሱ ሳቢያ ሙስሊሙ ላይ የሚፈጠሩ ግፎች አብዝተው ያሰጉኛል።
_______________
የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/Yahyanuhe
1.4K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 15:47:22 በሀድያ ዞን እየተካሔደ ባለው የዳዕዋ ፕሮግራም ከ20 በላይ ሰዎች እስልምናን ተቀብለዋል፥ አልሐምዱሊላህ
2.0K views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 15:58:39 በዛሬው እለት የነበረን መደበኛ የቲክቶክ ላይቭ ውይይት ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ከይቅርታ ጋር ለማክሰኞ ተዛውሯል።
624 views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 20:26:55
በምንከተለው የትኛውም የፖለቲካ ቃና ሳቢያም ይሁን በጠላታችን በደረሰበን በደል ሳቢያ በተፈጠረብን ቂም ምክንያት - ብቻ በየትኛውም ምክንያት ይሁን፥ የአሏህ ﷻ ዲን ሲካድና አሏህ ﷻ ላይ አደገኛ የቅጥፈት ኩፍር ሲነገር በየትኛውም ቋንቋ ሲነገር መስማት አንፈልግም፥ ቢያንስ ለዚህ "መብት" አንታገልም። አይደለም ያንን ቃል እንዲናገሩት ልንታገል ይቅርና በሰማንበት ቦታ ሁሉ በቻልነው ልክ ኩፍሩን እንታገለዋለን።
...
«ከእርሱ (ከንግግራቸው) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ለአርረሕማን ልጅ አልለው ስለአሉ፡፡» (መርየም 90–91)
...
ይህ ቃል አይደለም በአንደበት በሚነገር ቃል ይቅርና በምልክት ቋንቋ እንኳን መስማት የማይችሉ ወገኖቻችን እንዲሰሙት የማንፈልገው አሏህ ﷻ ላይ የተደረተ ጸያፍ ቃል ነው። ይህም ጀነትን ለወገኖቻችን ስለምንመኝላቸውና በኩፍሩ ሳቢያ የጀነቱን ኒዕማ እንዳያጡት ከመጨነቅ ነው። ይኸው ነው..!
_______________
የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/Yahyanuhe
550 views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 16:17:50
ዛሬ አንድ ወንድሜ የቁርአን 19፥71 አንቀጽን አስመልክቶ የሚነሳውን ትችት በተመለከተ በግል ጠይቆኝ ነበር። ጥያቄውን ከሰሞኑ ቲክቶክ ላይ በብዛት አይቸው ስለነበር ምላሽ ልሰጥበት እያሰብኩ የነበረ ቢሆንም ከኔ በፊት በዝርዝር እንደተመለሰ ሳስተውል የመልሱን ሊንኮች ሰጠሁት። ጥያቄው እናንተም ጋር ደርሶ ሊሆን ይችላልና በአጀንዳው ዙሪያ ዝርዝር ማብራሪያ ከፈለጉ በሚከተሉት ሁለት ሊንኮች ገብተው ማንበብ ይችላሉ፦

https://hidayacomparative.org/?p=817

ተጨማሪ

https://hidayacomparative.org/?p=818
1.0K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 12:16:15

1.6K views09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 10:45:38 ከወር በፊት በዲሴምበር 24 የሆነ የማላቀው አካል ፌስቡኬን ሀክ ማድረጉን በኢሜል ደረሰኝ። በወቅቱ በኛ ሀገር ሌሊት ስለነበር ጉዳዩን ያወቅኩት በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ወደፌስቡክ ልገባ ስል ነበር። አካውንቱ ላይ መጠባበቂያ ቁጥሬን ሳይቀር ሪሙቭ አድርገው በሌላ የኢትዮጵያ ቁጥር ተክተውት ስለነበር ያለኝ ብቸኛ አማራጭ በኢሜሌ አማካኝነት December 25 ላይ አካውንቱን ሪከቨር አድርጌ ቁጥሩን ማስወገድ ነበር። በወቅቱ አካውንቱን ከመለስኩት በኃላ ጉዳዩ ትልቅ ነገር ስላልመሠለኝ ለጀመዓ ሹራ ግሩፖች ብቻ ነግሬ ቀለል አድርጌ ትቸው ነበር።
...
በዛች ቅጽበት በርካታ ነገር መደረጉ የገባኝ ግን ዛሬ አቡ ዩስራ ሲደውልልኝ ነው። በነዛ ጊዜያት ግሩፕ ላይ አብረውኝ የነበሩ ወንድሞችን ኡስታዝ Sadiq Mohammed Ahmed ጨምሮ ሁሉንም በኔ አካውንት በገቡበት ወቅት ሪሙቭ አድርገዋቸዋል። የግሩፑን ክሬተር (ሱመያ የሚል አካውንት) ሪሙቭ ማድረግ ስለማይቻልና ጠዋት አጋጣሚ እኔም አካውንቱን ማስመለስ ባልችል ኑኖ ግሩፑን ሙሉ ለሙሉ ወስደውት ነበር። ይህ ሁሉ መሆኑን ግን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አሏህ ﷻ ምስክሬ ነው ምንም የማቀው ነገር የለም። አቡ ዩስራ ከግሩፑ ሪሙቭ መደረጉንና ምክንያቱን ሲጠይቀኝ ግሩፑ ከነ አካቴው ጠፍቶ ካልሆነ በስተቀር ማንም በጤናው አቡ ዩስራን ሪሙቭ ሊያደርገው እንደማይችል ስለማውቅ "ሁላችንም የለንም በለኛ" እያልኩት ወደ ግሩፑ ገባህ። ስገባ ግን ደነገጥኩ እሱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም አድሚኖች የሉም። ያለሁት እኔ ብቻ ነኝ..!
...
በዚህም ምክንያት ጉዳዩን ለአቡ ዩስራ በግርምት ስነግረው በአጋጣሚ ስክሪን ሹት አድርግሎኝ ብሎኝ ከታች ያለውን ላኩለት። አልሐምዱሊላህ አቡ ዩስራ በጣም አስታዋሽ ነውና ቴሌግራም የኡስታዞች ግሩፕ ላይ አካውንቴ ሀክ ተደርጎ እንደነበር የተናገርኩበትን ቀን ሪፕላይ አድርጎ በዚያ ቀን መሆኑን ነገረኝ። ሀቂቃ ይህንን ጉዳይ ሌላ ሰው ቢሆን በጣም ያስከፋና ያበሳጭ ነበር። ወንድሞቼ ግን ሙሉ ለሙሉ የሚያውቁኝና እንደዚህ አይነት ስህተት እንደማልፈጽሞ የሚተማመኑብኝ ቢሆንም ትንሽም ቢሆን የተከፋ ወንድምና እህት ካለ አሏህ ﷻ በሚያውቀው ፈጽሞ ይህ ተግባር የኔ እንዳልሆነና ከታች እንደምታዩት አካውንቱም በእጄ እንዳልነበረ በቀናነት እንድትረዱት በማሰብ ለማብራራት ተገድጃለሁ። በዚህ አጋጣሚ ካወቅነው ከዚህ ተግባር ሌላም ክስተት አብሬያችሁ በምሰራበት ፔጅም ሆነ ግሩፕ በሌሎቻችሁም ተፈጽሞ ከሆነ እንደምታዩት ፈጽሞ የማላቀው ነገር እንደሆነ እንድትረዱልኝ ነው። ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ።
___
የሕያ ኢብኑ ኑህ
1.4K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 10:45:36
1.3K views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-29 15:59:55 ቁርአን ስለ "መጽሀፍ ቅዱስ" ያለው አስተምህሮ ምንድን ነው? በሚል ርዕስ ውይይት ስናደርግበት የነበረው አጀንዳ በ 4 ክፍል አጠናቀናል። በዚህ ትምህርት ቁርአን ስለቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍ ያለውን አስተምህሮና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎችን በዝርዝር ዳሰናል። የትምህርቱ የመጨረሻ ሊንክ ከታች ተቀምጧል።
...
በቀጣይ የምንዳስሰው ክፍል "ቁርአን ቀደምት መለኮታዊ መጽሀፍ ተበርዘዋል ያለው ከምን አንጻር ነው? ማስረጃዎቹስ ምንድን ናቸው?" የሚለውን አስመልክቶ መጽሀፍቶቹን በመዳሰስ ዝርዝር ማሳያዎችንና ማስረጃዎችን መጽሀፍ ቅዱስን ብቻ በመጠቀም በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል። ይከታተሉን፥ ሼርም ያድርጉት..!



1.9K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 14:43:54
አንድ ሰው የማያቀው ሰው በሥህተት ብር ሲያስገባለት ወደ ባንክ ሂዶ ቸክ ካደረገ በኃላ ስህተት መሆኑን ካወቀ ለባለቤቱ በታማኝነት ይመልሳል። ከዚያ በዘለለ ይህንን ስህተት እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የራሱ ያልሆነን ገንዘብ ካስቀረ ግን ይህ ሰው መንፈሳዊ ሰው ሳይሆን "ሌባ" ሰው ነው። ይህንን ለመረዳት ጥልቅ የሀይማኖት አዋቂ መሆን አያስፈልግም። ይህ ግለሰብ ግን መሠል ጉዳዮችን ሳይቀር "ተዓምር" ናቸው ብሎ መንጋውን ሲያታልል ይውላል። ሙስሊሞችን አከፈርን ብለው ድራማ ሲሰሩ የሚውሉ ሰዎች በዚህ ደረጃ የሰውን ንቃተ ህሊና የሚንቁ ናቸው..!
___
የሕያ ኢብኑ ኑህ
https://t.me/Yahyanuhe
2.3K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ