Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የቴሌግራም ቻናል አርማ wwwaddisababaeducationbureau — Addis Ababa Education Bureau
የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 108.77K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 87

2022-07-13 21:43:18
ቀን 6/11/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡


በመግለጫውም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል፡፡


በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡


ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ነጥቦች ከዚህ እንደሚከተሉት ናቸው፡-


በጋዜጣዊ መግለጫው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡

በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፡፡

የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፡ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል ብለዋል፡፡
7.9K viewsAbebe Chernet, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:20:22
ቀን 5/11/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2014 የትምህርት ዘመን እቅድ አፈፃፀም እና በ2015 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር የጋራ ውይይት አደረገ፡፡


በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ2014 ዓ.ም ትምህርት ዘመን እቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2015 ትምርት ዘመን እቅድን አቅርበዋል፡፡


በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ደኛው ገብሩ የ2015 የትምህርት ዘመን እቅድ በየደረጃው ባሉ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ታይቶ እና ተገምግሞ የሚፀድቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸዉ ሁሉም ባለሙያ እቅዱ ላይ ያለውን አስተያየት በመሰንዘር የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው በዕቅዱ ላይ መስተካከልና መጨመር ያለባቸዉ ጉዳዮች ካሉ አስፈላጊዉን ማሰተካከያ በማድረግ የተሟላ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et
11.2K viewsAbebe Chernet, 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:28:00
ቀን 4/11/2014 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ400 በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡

የቻይናው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲ ሴፍ ፒ ኤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፊሊጶስ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ከ400 በላይ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ ከቻይናው በጎ አድራጎት ድርጅት ሲ ሴፍ ፒ ኤ የተገኘ ሲሆን የቦርሳና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው፡፡

ድጋፉንም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የቻይናው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኮንሱላር ያንግ ዪ ሃንግ ማስረከባቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ተማሪዎችን ማገዝ የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ መቅረፅ ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ እንደገለጹት የትውልድ ግንባታ ስራ የሆነውን ትምህርትን መደገፍ የሁሉም ኃላፊነት በመሆኑ በጋራ ተባብረን የነገ ሀገር ተረካቢ ልጆችን ማገዝ ይገባል ብለዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
12.0K viewsAbebe Chernet, 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:32:42 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/


ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
16.4K viewsAbebe Chernet, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:32:17
ቀን 1/11/2014 ዓ.ም

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው ዓመት ሒጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ፡፡


በሀገራችን ከምናከብራቸዉ ታላለቅ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ ታላቁ የኢድ አል አድሃ በዓል በመሆኑ እንኳን ለበአሉ በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡


በዓሉን ስናከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተቸገሩትን በመርዳት ፣ በመደጋገፍና በመተሳስብ ከሁሉም በላይ አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል፡፡


በዓሉ የህዝባችን የአንድነትና የአብሮነት መገለጫ እሴት ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያዊነት ማሳያ እና መገለጫ በመሆኑ በዓሉን ስናከብር የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ የሆነችዉ ሀገራችን የውበት ማሳያ የእንድነታችን ቀንዲል መሆናን አጉልተን የምናሳይበት ታላቅ እለት መሆኑን በማሰብ ሊሆን ይገባል፡፡



ከዚህም ባለፍ ሀይማኖታዊ ወንድማማችነት እና እህታማችነታችንን የምናጠናክርበት አንተ አንቺ ትብሽ የምንባባልበት ታላቅ እና የሀገራችንን እና የህዝባችንን ከፍታ ወደ ላቀ ደረጃ የምናሻግርበት እለት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡



በድጋሜ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም ፣ በፍቅር ፣ በጤናና በአንድነት አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡


ዒድ ሙባረክ !


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አቶ ዘላለም ሙላቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
14.7K viewsAbebe Chernet, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:22:22
ቀን 1/11/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ቡድን የ2014 በጀት አመት የትምህርት ተቋማት የቢ ኤስ ሲ ስኮር ካርድ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን በተመለከተ ከክፍለ ከተማ የምዘና አስተባባሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ውይይቱ በዋናነት የምዘና ስርዓቱ በሚመራበት አግባብ ላይ በመወያየት የጋራ አቅጣጫ መያዝን መሰረት አድርጎ መካሄዱን የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ቡድን መሪ ወይዘሮ እጸገነት አብዱ ገልጸዋል፡፡

ቡድን መሪዋ አክለውም በውይይቱ ከተነሱ ሀሳቦች መካከል የመመዘኛ መስፈርቱ፤የመዛኞች ምልመላ በተመለከተ እንዲሁም ምዘናው የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳን የተመለከቱ ሀሳቦች መነሳታቸውን ጠቁመው ምዘናው ከሀምሌ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በ11ዱ ክፍለከተሞችና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንደሚካሄድ አስታቀውቀዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/


ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
16.9K viewsAbebe Chernet, 09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:02:10
ቀን 30/10/2014 ዓ.ም

የተማሪዎች አሻራ በየካ ሚሊኒየም ፓርክ በፎቶ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube:



Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: - aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/


ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!
13.6K viewsAbebe Chernet, 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ