Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 1/11/2014 ዓ.ም ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው ዓመት ሒጅ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 1/11/2014 ዓ.ም

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው ዓመት ሒጅራ የኢድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ፡፡


በሀገራችን ከምናከብራቸዉ ታላለቅ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ ታላቁ የኢድ አል አድሃ በዓል በመሆኑ እንኳን ለበአሉ በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡


በዓሉን ስናከብር እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ የተቸገሩትን በመርዳት ፣ በመደጋገፍና በመተሳስብ ከሁሉም በላይ አብሮነታችንን በማጠናከር ሊሆን ይገባል፡፡


በዓሉ የህዝባችን የአንድነትና የአብሮነት መገለጫ እሴት ከመሆኑም ባሻገር የኢትዮጵያዊነት ማሳያ እና መገለጫ በመሆኑ በዓሉን ስናከብር የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ የሆነችዉ ሀገራችን የውበት ማሳያ የእንድነታችን ቀንዲል መሆናን አጉልተን የምናሳይበት ታላቅ እለት መሆኑን በማሰብ ሊሆን ይገባል፡፡



ከዚህም ባለፍ ሀይማኖታዊ ወንድማማችነት እና እህታማችነታችንን የምናጠናክርበት አንተ አንቺ ትብሽ የምንባባልበት ታላቅ እና የሀገራችንን እና የህዝባችንን ከፍታ ወደ ላቀ ደረጃ የምናሻግርበት እለት እንዲሆን እመኛለሁ፡፡



በድጋሜ እንኳን ለ1ሺህ 443ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም ፣ በፍቅር ፣ በጤናና በአንድነት አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡


ዒድ ሙባረክ !


ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አቶ ዘላለም ሙላቱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ