Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 4ኛውን ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 4ኛውን ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት ውድድር አሸናፊ ሆነ፡፡

(ግንቦት 26/2016 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) 4ኛውን ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሰብአዊ መብቶች ምስለ-ችሎት ፍጻሜ ውድድር ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አካሄዳል፡፡

ውድድሩ ከየካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክልል እና ሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በ12 ክልሎች እና በ2 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ 81 ትምህርት ቤቶች እና 162 ተወዳዳሪ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል።

የውድድሩ አላማ ተማሪዎች የሰብዓዊ መብትን ማክበርና ሰለ ሰብዓዊመብቶች መቆርቆርን ግንዛቤ እንዲያዳብሩ ፤ ተማሪዎች በሰዎች ፊት የምግለጽ ክህሎታቸዉን እንዲያጎለብቱ ፤ አድማሳዊ ዕታዎችን የሚሳፍና ችግር ፈችነትን እየተለማማዱ እንዲመጡ የሚያግዝ ነዉ፡፡

በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ በተካሄደው የምስለ ችሎት ውድድር ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ 8 ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመምጣት የሩብ እና የግማሽ ፍጻሜ ሀገር አቀፍ የቃል ክርክር ውድድር ከግንቦት 19 እስከ 24 ቀን 2016 ዓ.ም ሲያደርጉ ቆይተው የፍጻሜ ውድድር አድርገዋል፡፡