Get Mystery Box with random crypto!

የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም አመታዊ የትምህርት መጽ | Addis Ababa Education Bureau

የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም አመታዊ የትምህርት መጽሔትን አስገመገመ።

(ሰኔ 9/2016 ዓ.ም) መጽሔቱ ጉዳዩ በሚመለከታቸው የቢሮውና ክፍለ ከተማ ባለሙያዎች የተገመገመ ሲሆን የግምገማው ተሳታፊዎች በቡድን እና በጋራ በመሆን ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳና ክፍለ ከተማ ደረጃ ተጠናቅረው በአመታዊ መጽሄቱ የተካተቱ አጠቃላይ የትምህርት መረጃዎችን የማጥራትና የመገምገም ስራ ሰርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም ቢሮው ከሚያከናውናቸው ቁልፍ ተግባራት መካከል አንዱ አመታዊ የትምህርት መጽሔት በማሳተም ለተገልጋዩ የሚፈለገውን መረጃ ተደራሽ በማድረግ ለመማር ማስተማር ስራው ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማበርከት መሆኑን አስታውቀዋል።

ቡድን መሪው አክለውም በአመታዊ መጽሔቱ የተካተቱ የተማሪዎችና የመምህራን አጠቃላይ መረጃዎች፣የትምህርት ተቋማት መረጃዎች እንዲሁም አራቱ የትምህርት አመላካቾችን ጨምሮ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎች በአግባቡ መካተታቸው በባለሙያዎቹ መገምገሙን ጠቁመው በቀጣይ በግምገማ ሂደቱ የተሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦች ተካተው መጽሔቱን ወደ ማ ሳተም ሂደት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ባለሙያው አቶ አለምነህ መላኩ በአመታዊ መጽሔቱ የተካተቱ መረጃዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።