Get Mystery Box with random crypto!

ቀን 6/11/2014 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወ | Addis Ababa Education Bureau

ቀን 6/11/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው እለት ሀምሌ 01/ 2014 የወጣውን የ 20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡


በመግለጫውም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፤ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ግዛው ፤ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት የአጣሪ ቡድን መሪ አቶ በሀይሉ አዱኛ መግለጫውን በጋራ ሰጥተዋል፡፡


በዚህ መግለጫ የከተማ አስተዳደሩ ከኢንሳ፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፤ እንዲሁም ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አጣሪ ቡድን እንዲቋቋም ተደርጎ ወደ ማጣራት ስራ በመግባት ሲጣራ ቆይቶ በዛሬው እለት በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡


ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ያነሷቸው ነጥቦች ከዚህ እንደሚከተሉት ናቸው፡-


በጋዜጣዊ መግለጫው ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የጋራ መኖርያ ቤት እጣ በማውጣት ሂደት ባጋጠመን ችግር ህዝቡንም ከተማ አስተዳደሩንም ያሳዘነ ድርጊት መፈፀሙን አንስተዋል፡፡

በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ህብረተሰቡ በትእግስት በመጠበቅ እንዲሁም የጀመርነውን ጥረት ከጎናችን በመቆም ላሳየው ጥረት ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡

ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለህዝባችን ቃል በገባነው መሰረት ችግር ቢያጋጥም እንኳን በቀጥታ ኦዲት እናደርጋለን ብለን በገለፅነው መሰረት ጥቆማ ስለደረሰ ጊዜ ሳንሰጥ በሚመለከታቸው አካላት የማጣራት ስራ እንዲጀመር አስደርገናል፡፡

የቴክኖሎጂ ውንብድና አጋጥሞናል፡ አመራር የመራው ውንብዳ ነው፡፡ በዚህ ሂደት የቤት ስርቆት ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ጭምር መግለፅ ይቻላል ብለዋል፡፡