Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-06-10 21:43:40
ሰኞ ፍርድ ቤት ይቀርባል !

* ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውታል

#Ethiopia | የጉማ አዋርድ መሥራችና አዘጋጅ ፤ ዳይሬክተር ዮናስ ብርሃነ መዋ ትናንት " በ9ኛው የጉማ አዋርድ ዝግጅት ተጠናቆ ሳለ ፤ ... ለጥያቄ እፈልገዋለን " በማለት ቦሌ ትራፊክ መምሪያ በተለምዶ ስሙ "አንበሳ ጋራዥ" አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታሰሮ ነበር።

ዛሬ ፣ ከቀኑ 5:00 ሰዓት ላይ 24 (ኮከብ አዳራሽ) በሚገኘው ፍርድ ቤት ቀርቦ ነበር። ፍ/ቤቱ በ 5,000 (በአምስት ሺህ ብር) ዋስትና ለቆት ነበር።

ይሁን እንጂ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ከፖሊስ ጣቢያ እንደወጣ ፤ "ለዳግም ጥያቄ ትፈልጋለህ?" ተብሎ ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን እንዲሁም ሰኞ ፍ/ቤት እንደሚቀረብ ከቤተሰቡ ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል፡፡

@topMereja
1.6K views18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 21:25:25
እጅግ አሳዛኝ

የመከላከያ አባላት ሁለት ግለሰቦችን ሲረሽኑ የሚያሳይ ቪድዮ።

@topMereja
14.8K viewsedited  18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 10:26:10
ዘመነ ካሴ ከእስር ተፈታ

ዘመነ ካሴ በአሁኑ ሰአት ከሰባታሚት ማረሚያ ቤት ወጥቷል።

ከመስከረም ወር ጀምሮ በባህር ዳር ሰባታሚት ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የቆየው ዘመነ ካሴ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድቤት አርብ ዕለት በዋለው ችሎት ዘመነ ከተጠረጠረበት ወንጀል ነፃ መባሉን ተከትሎ ዛሬ ከማረሚያ ቤት ወጥቷል።

@topMereja
15.6K views07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 20:36:08 ሰበር መረጃ

" እናንተ እድለኞች ናችሁ ፣ በሰው ሀገር በሰላም እየኖራችሁ ነው ! ሀገር ቤት ያለው ህዝብ መከራ ላይ ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዱባይ ያልተጠበቀ ንግግር አደረጉ

ሙሉ ቪድዮን ለማየት





14.8K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 18:52:06
#AddisAbaba

ዛሬ በአዲስ አበባ ፤ " አንዋር መስጂድ " ከጁመአ ስግደት መጠናቀቅ በኃላ የፀጥታ ኃይሎች በተከፈቱት ተኩስ የሰው ህይወት ስለማለፉና ጉዳት ስለመድረሱ በአካባቢው የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

በአሁን ሰዓት የተጎዱ ሰዎች እርዳታ እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በመስጂዱ በነበረው ሁኔታ የአደጋ ጊዜ አዛን መሰማቱ ተነግሯል።

ከዚሁ ጋር በተያየ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ፤ " በታላቁ አንዋር መስጂድ የጁምዓ ሰላቱን ለመስገድ ከቤቱ የወጣን እና በመስጂድ ያለን ንፁሃን ህዝበ ሙስሊም ላይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የሀይል እርምጃ መውሰድ ኢ ሰብዓዊ ተግባር ነው " ብለዋል።

" ባዶ እጁን ለሰላት በወጡ ንፁሀን ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ የፀጥታ ኃይሎች ያቆሙ ዘንድ አሳስባለሁ " ያሉቱ ኡስታዝ አቡበከር " በመስጂዱ ተጠልለው የሚገኙ እና ያለህራሄ በጥይት ተመትተው በመስጂዱ ውስጥ እና ዙሪያውን ወድቀው የሚገኙት ወንድሞቻችን በአስቸኳይ ወደ ህክምና ቦታ ይወሰዱ ዘንድ አምቡላንስ ወደ ቦታው እንዲገባ መንገዱን ክፍት ልታደርጉ ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ስለ ዛሬው የአንዋር መስጂድ ሁኔታ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እንዲሁም የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሚሰጡት መረጃ / መግለጫ ካለ ተከታትለን እናሳውቃለን።

በተመሳሳይ በመንግስት / በከተማው አስተዳደር በኩል የሚሰጥ ማብራሪያ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።

ባለፈው ሳምንት ጁመአ በአንዋር መስጂድ በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለው የመስጂዶች ፈረሳ ተግባር በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ በቀረበበት ወቅት በተወሰደ እርምጃ የሰዎች ህይወት ማለፉ የሚዘነጋ አይደለም።

ጥቆማ ፦ አምቡላንስ ለማግኘት 907 ወይም በ0115150608 ላይ ይደውሉ።

@topMereja
15.8K views15:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-02 14:57:56
እግዚኦ አሳዛኝ ቪዲዮ ከአንዋር መስጅድ | ሙሉ ቪዲይ በዩትዩባችን ተለቋል ሊንኩን በመንካት ይመልከቱ





12.9K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 20:39:33
ፓርቲው ከመርህ ውጪ አካሄዱን ካስተካከለ ወደ ፊት አብረው ሊሰሩ የሚችሉበት መንገድ ሊኖር እንደሚችል ከኢዜማ የለቀቁ አባላት ገለፁ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ከኢትዮጵያ ለማህበራዊ ፍትሀ /ኢዜማ/ ፓርቲ የለቀቁ አባላት በቀጣይ ምን ለማድረግ ነው ያሰባችሁት ሲል አሐዱ ያነጋገራቸው የቀድሞ የኢዜማ ከፍተኛ አመራር እና በቅርቡ ፓርቲውን ከለቀቁ አባላት አንዱ አቶ የሺዋስ አሰፋ ፓርቲው ሲቋቋም ይዞ የተነሳው መርህ በመኖሩ፣ ከፓርቲው መርህ ውጪ የወጣው አካል ነው ወደ አባላቱ እና ህዝብ መመለስ ያለበት ብለዋል፡፡

ፓርቲው ከመርህ ውጪ መሄዱን እና አካሄዱን የሚያስተካክል ከሆነ እና ወደ ህዝብ ከተመለሰ ከአባላቱ ከደጋፊው ህዝብ ጋር ከታረቀ፣ ከባልደረቦቻቸው ጋር ተማክረው አብረው ለመስራት የሚችሉበት አጋጣሚ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎች ገና ባለመመለሳቸው፣ እነዚህን ጥያቄዎች ለመፍታት በግለሰብም ሆነ በቡድን መታገል ግዴታ ነው ያሉት አቶ የሺዋስ፡ እውነተኛ ሀገራዊ ስብስብ እና ሰላማዊ አማራጭ በሚያስፈልግብት በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ህዝቡን አንተወውም ብለዋል፡፡ይህ በእንዲህ እንዳለም ተጨማሪ 41 የሚደርሱ የፓርቲው የምርጫ ወረዳ አመራርና መደበኛ አባላት ድርጅቱን ለቀው መውጣታቸውም እየተነገረ ይገኛል፡፡

@topMereja
13.5K views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 17:09:10
ሰበር ዜና
የታገተችዉ ወጣት
ነጻ ወጥታለች
ወ/ሪት ጸጋ ከታገተችበት ነጻ ወጥታ በፖሊስ  ወደ ሀዋሳ መግባቱዋ ታውቋል። ተጠርጣሪው ግለሰብ ተበዳይዋን ጥሎ ወደ ጫካ በመግባቱ በከፍተኛ ክትትል ውስጥ ይገኛል። ተጨማሪ መረጃዎችን ከደቂቃዎች በኋላ እንደደረሰን እናቀርባለን።
@topmereja
14.7K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-01 16:18:46
ኮ/ል መንግቱ ኃይለማርያም ከአንድ የደቡብ ሱዳን የጦር ሀላፊ ጋር በሐረሬ ሲጨዋወቱ!

@topmereja
12.2K views13:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 18:00:31
በሰሜን ኢትዮጵያው የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ለመወያየት፤ የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ባለፈው ጥቅምት ወር በተፈራረሙት የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ለመነጋገር፤ የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር በድጋሚ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው። ሐመር ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር በአዲስ አበባ፤ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ደግሞ በመቐለ ከተማ በመጪዎቹ ቀናት እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።

ማይክ ሐመር ከዛሬ ረቡዕ ግንቦት 23፤ 2015 ጀምሮ ለሰባት ቀናት በአፍሪካ ቀንድ የሚያደርጉት ቆይታ፤ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ጅቡቲንም ያካተተ መሆኑን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቃባይ ጽህፈት ቤት ገልጿል። አምባሳደር ሐመር ወደ ጀቡቲ የሚጓዙት ሀገሪቱ በምታስተናግደው የምስራቅ አፍሪካ የጸጥታ ፎረም ስብሰባ ላይ ለመገኘት መሆኑን የቃል አቃባይ ጽህፈት ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫው አመልክቷል።

@topMereja
13.0K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ