Get Mystery Box with random crypto!

Top Mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja T
የቴሌግራም ቻናል አርማ topmereja — Top Mereja
የሰርጥ አድራሻ: @topmereja
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.48K
የሰርጥ መግለጫ

-ማስታወቂያ ለማሰራት እና ለአስታየት :- @NatnaelAbreham1
የ Twitter አድራሻ : http://twitter.com/BoleMereja?t=watBbei5PnmgrUd80qQrnw&s=09
ዩቲዩብ : https://youtube.com/channel/UCXcMdhLzUAPeRAxW48JFClQ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-01-14 17:45:05
የኢቢኤስ ቤት በሀዘን ተውጧል !

የአንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ባልደረቦች በስቱዲዮ ተገኝተው ሐዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

ነፍስ ይማር!

@BoleMereja
13.4K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-12 21:11:39 ሰበር ዜና

አሽንፈነዋል ! የፋኖ ጦር መሪ እና አስተባባሪ አርበኛ ዘመነ ካሴ በአሁኑ ሰዓት  መግለጫ እየሰጠ ነው። ሙሉ መግለጫውን ይመልከቱ



13.2K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-26 21:25:17
መረጃ !


የኤርትራ መንግስት በኢትዮጵያ ድንበር ላሰማራው ሰራዊት ከፍተኛ የሆነ ስንቅና ትጥቅ አቅርቦት እያካሄደ መሆኑ ተሰማ:: የኤርትራ መከላከያ ሀላፊ ጀነራል ፊልጶስ ወልደ ዮሀንስ የመሩት የጦር አዛዦች ቡድን በኢትዮጵያ ድንበሮች ላይ ቅኝት ሲያካሂዱ መቆየታቸው ታውቋል::

ቀይ ባህርን ምክንያት በማድረግ የሚድያ ፕሮፓጋንዳ ሲያደርግ የሰነበተው የብልፅግና መንግስት ባንፃሩ እዚህ ግባ የሚባል እንቅስቃሴ እያደረገ አለመሆኑ አስገራሚ ሆኗል::

@topMereja
15.8K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-17 20:21:04
የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድን ወጣት አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ!

አጋችና ታጋች የአንድ ወር ጓደኛሞች እንደነበሩም ፖሊስ አሳውቋል።የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ይባላል፡፡ወጣቱ በማህበራዊ መገናኛ አውታር (ማህበራዊ ሚዲያ)አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡ ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን  ያግቱታል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዩን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ እንዳወጣው አሳውቋል።

ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5ሺ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።ፖሊስ፤በልዩ ልዩ ምክንያት የምንቀርባቸው ግለሰቦች ማንነታቸውን ጊዜ ወስደን ማረጋገጥ አለብን ብሏል።በተለይ ሙሉ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነትና ለምን እንደተከራዩ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል። ይህን ሳያደርጉ በሚፈጠር ችግር የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።

@topMereja
12.9K viewsedited  17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-11 23:00:02
ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ::

እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!

Via Taye Dendea

@topMereja
12.9K views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-05 21:45:39
አትሌት ታምራት ቶላ የኒውዮርክ ማራቶንን በ2:04:58 በመግባት አሸነፈ።

@topMereja
15.4K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-11-02 16:24:03
የልመና ተባባሪ የሚሆኑ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ !

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የካ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተሽከርካሪ መንገዶች ላይ ህገ-ወጥ ግብይትና በልመና ለተሰማሩ ግለሰቦች ተባባሪ በመሆን የትራፊክ ፍሰቱን የሚያጨናንቁ የትራፊክ ህግና ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች ላይ የመንገድ ትራንስፖርት ደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት በማድረግ የእርምት እርምጃ ወሰደ፡፡

የትራፊክ ቁጥጥር የተደረገዉ በሾላ ሴፍቲ መብራት ህገወጥ ግብይትና ልማና ላይ ለተሰማሩ ግለሰቦች ግብይት በሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ላይ ተከታታይ የሆነ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የእርምት እርምጃ የተወሰደ ሲሆን የትራፊክ ፍሰትንና ደህንነትን ለማረጋገጥ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

ልመና እና ግብይት በሚካሄድባቸው ቦታወች ለአደጋ ተጋላጪ እንዲሁም የትራፊክ ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተፅኖ እና ፍሰቱንም ስለሚያውክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በተመረጡ ቦታወች ላይ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እና ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፇል።

@topMereja
13.0K views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-29 19:26:27
ፓልም ሪል ስቴት ለመቄዶንያ 27 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አፓርታማ ቤት በስጦታ ተበርክቶለታል።

ፓልም ሪል ስቴት ለመቄዶንያ 27 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ አፓርታማ ቤት በስጦታ ተበርክቶለታል። ትናንት በተከናወነ ስነስርዓት ከፓልም ሪል ስቴት የተበረከተውን የቤት ስጦታ የመቄዶንያ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብንያም በለጠ ተረክቧል። ስጦታውንም የፓልም ሪል ስቴት አምባሳደር አርቲስት አለማየሁ ታደሰ አስረክቧል።

@topMereja
13.1K views16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-27 19:19:44
አንጋፋው ፖለቲከኛ እና የሰበአዊ መብት ተማጋች ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ህይወታቸው ያለፈበትን ሶስተኛ አመት አስመልክቶ ታላቅ የመታሠቢያ ፕሮግራም ተዘጋጀ ።

ከመታሠቢያ ዝግጅቱ በተጨማሪ በስማቸው የተመሠረተው ፋውንዴሽን አውደጥናት አንዳዘጋጀ ለማወቅ ችለናል ።
እሁድ ጥቅምት 18 ቀን 2016 አም በኢሊሌ ሆቴል በሚዘጋጀው ኮንፍረንስ ላይ አንጋፋው የሠበአዊ መብት ተከራካሪ በህይወት ዘመናቸው ከታገሉላቸው በርካታ ፖለቲካዊና ማህበረሰባዊ ጉዳዮች መካከል በዚህ አመት በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ እና የመብት ጥሰት በሚፈፅሙ ሰዎች የህግ ተጠያቂነት ላይ ያተኮሩ የጥናት ወረቀቶች በምሁራን ይቀርባሉ ተብላል ።

ይህ ዝግጅት በኢሊሌ ሆቴል እንደሚቀርብም ለእንግዶች የተላከው የጥሪ ካርድ ይገልፃል ።

@topMereja
13.4K viewsedited  16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-24 20:58:40 የፋብሪካ ምርት እንደሆነ በማስመሰል የምግብ ዱቄት ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሀረር ከተማ የፋብሪካ ምርት እንደሆነ በማስመሰል የምግብ ዱቄት ሲሸጡ የነበሩ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል ።

ግለሰቦቹ የጥራት ደረጃው ያልተረጋገጠ እና በህጋዊ የፋብሪካ ቀረጢት አማካኝነት  የምግብ ዱቄት ሲሸጡ መቆየታቸውን በኮሚሽኑ የወንጀል ምርመራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ዑመር አሚር ተናግረዋል ።

ፖሊስ የምግብ ዱቄቱ በገበያ ላይ ሲሸጥ የነበረ አንድ ግለሰብ እና ሌሎች ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

ህጋዊ እውቅና ሳይኖረው ለሽያጭ የቀረበው ዱቄት በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ይህንና መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት ለፖሊስ ማሳወቅ እንደሚገባ አክለዋል ።

@topMereja
13.0K viewsedited  17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ